TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ችሎት

#ክርስቲና_መላኩ #ጊዮናዊት_መላኩ

የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ 2ኛ ጊዜ ቀጠሮ ችሎት ፤ የህጻን ግዮናዊት መላኩ እና ህጻን ክርስቲና መላኩን በአሰቃቂ ሁኔታ ህይወታቸው እንዲያልፍ አድርጋለች የተባለችው ተጠርጣሪ ላይ ፖሊስ ተጨማሪ ምርመራ እንዲያደርግ የ14 ቀን ጊዜ ሰጠ።

ተጠርጣሪ ህይወት መኮንን ሀይሉ በነሃሴ 26 ቀን 2014 ዓ/ም ከጠኋቱ 3:30 ላይ በለሚ ኩራ ክ/ከ አራብሳ ኮንዶሚኒዬም ተቀጥራ በምትሰራበት መኖሪያ ቤት ውስጥ ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ የህጻን ግዮናዊት መላኩ አፏን በማፈን በቢላ በማረድ ህይወቷ እንዲያልፍ ማድረጓን እና ህጻን ክርስቲና መላኩን ደግሞ አፏን በማፈን በማነቅ በአጠቃላይ በአሰቃቂ ሁኔታ ህይወታቸው እንዲያልፍ ማድረጓን ፖሊስ ለችሎቱ አስረድቷል።

በዚህ መልኩ ተጠርጣሪዋን በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እያደረገ መሆኑን የገለጸው ፖሊስ የሰው ማስረጃ ለማሰባሰብና የግድያ ወንጀል የተፈጸመበትን ትክክለኛ ምክንያት በማስረጃ ለማረጋገጥ እንዲሁም በተጠርጣሪዋ ዙሪያ ያሉ ግለሰቦች ላይ ማስረጃ ለማሰባሰብና በወንጀሉ ስፍራ የተገኘ ስለታማ ቢላን በፎረንሲክ ለማስመርመር በተጨማሪም የአስከሬን ምርመራ ውጤት ለማምጣት የ14 ቀን ጊዜ እንዲሰጠው ጠይቋል።

በተጠርጣሪዋ በኩል ምንም አስተያየት ያልቀረበም።

የምርመራ መነሻ መዝገብን የተመለከተው የጊዜ ቀጠሮ ችሎቱ ተጠርጣሪዋ ላይ ፖሊስ ተጨማሪ ምርመራ እንዲያደርግ የ14 ቀን ጊዜ ፈቅዷል።

ምንጭ ፦ ጋዜጠኛ ታሪክ አዱኛ

@tikvahethiopia