TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Tigray

የህፃናት አድን ድርጅት / Save the Children / በትግራይ ክልል ትምህርት ቤቶችን ከስጋት ነፃ ለማድረግ በተሰራ ስራ 1 ሺህ 231 ያልመከኑ ፈንጂዎች መገኘታቸው ገለፀ።

አሀዱ ሬድዮ ፤ የህጻናት አደን ድርጅት በኢትዮጵያ / Save the Children /  የትግራይ ክልል አስተተባባሪ የሆኑትን አቶ አታክልቲ ገብረ ዮሓንስን ዋቢ በማድረግ ባሰራጨው መረጃ ፤ ከሰላም ስምምነቱ በኃላ 1 ሺህ 218 ት/ ቤቶች የተከፈቱ ሲሆን  722ቱ የሚሆኑት በደረሰባቸው ከባድ ጉዳት አገልግሎት አልጀመሩም።

ተማሪዎች 3 ዓመት የትምህርት ገበታቸው ላይ አለመገኘታቸውን ያነሱት አስተባባሪው አሁን ላይ ለ39 ሺህ መምህራን የ3 ወር  ደሞዝ መከፈሉን አሳውቀዋል።

ት/ቤቶችን ከስጋት ነጻ ለማድረግና የተማሪዎቹ ደህንነት እንዲጠበቅ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር የተለያዩ ስራዎች መሰራታቸውን እና ከክልሉ ትምህርት ቢሮ ጋር በተሰራው ስራ በ1 ሺ 544 ትምህርት ቤቶች ውስጥ 1 ሺህ 231  #ያልመከኑ ፈንጂዎች መገኘታቸውን  ጠቁመዋል።

ድርጅቱ የተሸከርካሪ እና ሌሎችም ድጋፎችን በማድረግ በጋራ በተሰራው ስራ ትምህርት ቤቶችን ከስጋት ነጻ ማድረግ እንደተቻለ ተናግረዋል፡፡

ለ40 ሺህ ተማሪዎች በ59 ትምህርት ቤቶች ላይ የህጻናት አደን ድርጅት በኢትዮጵያ የተለያዩ ድጋፎችን ማድረጉን አቶ አታክልቲ ገብረ ዮሓንስ ለአሐዱ ገልፀዋል።

#አሐዱ #SavetheChildren

@tikvahethiopia