TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.7K photos
1.49K videos
211 files
4.06K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
አንጋፋው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለመቄዶንያ መስራች አቶ ቢንያም በለጠ እና ለአርቲስት ደበበ እሸቱ ፤ የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ደግሞ ለተወዳጇ ድምፃዊት እጅጋየሁ ሽባባው ( #ጂጂ ) የክብር ዶክትሬት ዲግሪ አበርክተዋል። አንጋፋው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፤ የመቄዶኒያ የበጎ አድራጎት ማህበር መስራች አቶ ቢንያም በለጠ ላከናወኗቸው በጎ ስራዎች የክብር ዶክትሬት አበርክቶላቸዋል። በሰሩት ስራ በሰው ልጆች…
#AAU #DrBinyamBelete😢

ዛሬ ከአንጋፋው አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የክብር ዶክትሬት የተበረከተላቸው የሜቄዶንያ በጎ አድራጎት ማህበር መስራች አቶ ቢንያም በለጠ በመድረኩ ላይ ንግግር አድርገው ነበር።

ያደረጉት ንግግር እጅግ ስሜትን የሚነካ ስለነበር ተመራቂዎች እና ታዳሚያንን #እያለቀሱ ሲያዳምጡ ነበር።

አቶ ቢንያም በለጠ ምን አሉ ?

" ...ለእኔ ብዙ ትልቅ ቦታ አትስጡኝ ፤ እኔ የማልረባ ሰው ነኝ ፤ ቅድም ስለእኔ ስትገልፁ ከብዶኛል።

እውነቴን ነው እግዚአብሔር ይሰራል እሱን አልክድም ሜቄዶንያ ላይ ፤ ምክንያቱም ካለምንም እርዳታ ይሄን ሁሉ ሺህ ሰው በሀገር ውስጥ በየቀኑ አንድ ሚሊዮን የእግዚአብሔርን ስራ መሆኑ ግልፅ ነው በጣም።

እኔኮ በሽተኛ ነኝ ሲጀምር ብዙ ጊዜ ተኝቼ ነው የምውለው ፤ ስራ ያቆምኩ ሰው ነኝ እኔ እንደውም የህብረተሰብ ሸክም መሆን ያለብኝ ሰው ነኝ እውነት ለመናገር።

እንደ እኔ አይነት ሰው ዝም ብላችሁ ብታስቡት እንኳን እንደዚህ ለማድረግ ይቅርና እራሴንም ለመቻል ወይ አግብቶ ወልዶ ለመኖር ሰው ለመርዳት ቀርቶ ለመለመን እንኳን አንድ ሰው ጤነኛ መሆን አለበት ፤ ለመለመን ወጣ ብሎ አንድ ቦታ መቀመጥ አለበት እኔ መቀመጥም አልችልም።

ለመኖር እራሱ የማይገባኝ ሰው ነኝ ፤ በእግዚአብሔር ኃይል ነው ያለሁት ፤ እውነቴን ነው የምነግራችሁ ቀልዴን አይደለም። አንድ ሰው ለመለመን መንገድ ላይ ቁጭ ብሎ ሰው መጠየቅ አለበት አይደል እንደዛ እንኳን የምችል ሰው አይደለሁም። ስለዚህ እግዚአብሔር ነው የሚሰራው።

አንድ የህብረተሰብ ሸክም የሆነ ሰው ፤ እግዚአብሔር ምን ያህል ሃጥያተኛ ሰዎችን በመንፈስም በስጋም ደካማ የሆኑ ሰዎችን እንዴት መርዳት እንደሚችል አንዳንድ ሰዎች በቤተሰብ፣  በትዳር፣ ወይ ሰው አስቀይሟችሁ እንደው እግዚአብሔርን የለም ብላችሁ/ እግዚአብሔር ረሳኝ ብላችሁ ከሆነ እግዚአብሔር እንደዚህ ይሰራል። በማይረቡ ሰዎች፣ በተራ በጣም በወንጀለኛ ሰዎች መስራቱን ስታዩ ሁሉንም ሰው እግዚአብሔር እንደሚረዳ የሚያሳይ ነገር ነው።

ክብር ዶክትሬት ተብሏል ፤ እኔ ትንሽ ከብዶኛል በጣም ምክንያቱም እናተ ሸልማችሁኛል ፤ የእግዚአብሔር ፍርድ ደግሞ ከባድ ነው እውነት የእግዚአብሔር ፍርድ በጣም አስፈሪ ነውና ከሲኦል እንድድን እግዚአብሔር ከዚያ እንዲያወጣኝ ፀሎት አድርጉልኝ የእውነት። ይሄ በጣም ከባድ ነገር ስለሆነ ነው። ቀልድ አይደለም እግዚአብሔር ዝም ብለን ሃጥያት ስንሰራ ዝም የሚለን አምላክ አይደለም። የእግዚአብሔር ፍርድ ከባድ ነውና እኔ የምፈራው እሱን ነው እንኳን ልሸለም ለፍርድ እንዲቀልልኝ የማስብ ሰው ነኝ።

ሜቄዶንያ ላይ ብዙ ሰው አስተዋጽኦ ያደርጋል። እኔ የተለየ አስተዋጽኦ የለኝም ከዛ ያነሰ ነው የእኔ አስተዋፅኦ። በሽተኛ ስለሆንኩኝ ስራም ስለሌለኝ አንደኛው ተደጓሚ ነኝ እራሴ በመቄዶንያ ነገር ግን መቄዶንያ ባልፉት ዓመታት እዚህ ለመድረስ ብዙ አስተዋፅኦ ያደረጋችሁ ሰዎች አላችሁ ምስጋናም ክብርም የሚገባው ለእናተ ነው።

ተማሪዎች፣ ወጣቶች ፣በጎፍቃደኞች፣ የመንግሥት ኃላፊዎች፤ የሚኒስትር መስሪያ ቤቶች ፣ ሚኒስትሮች ፣ ኮሚሽነሮች፣ የመንግስት የልማት ድርጅቶች፣ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጀምሮ ሁሉም ሜቄዶንያን አግዘዋል በየቢሮው ያስተናግዱናል፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር፣ የክልል መስተዳደሮች በሙሉ፣ ለሜቄዶንያ እዚህ መድረስ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አድርገዋል። "

(የክብር ዶክተር ቢንያም በለጠ ሙሉ ንግግር ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia