TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.4K photos
1.47K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#የካቲት11

ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ የተመሰረተበት የየካቲት 11 ክብረ በዓል ላይ ከ150,000 በላይ ታዳሚዎች ይገኛሉ ተብሏል። በበዓሉ ላይ የሚገኙ ታዳሚዎችን ለማስተናገድና በዓሉን በድምቀት ለማክበር የቅድመ ዝግጅት ስራዎች እየተከናወኑ ነው።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#የካቲት11

45ኛው ዓመት የየካቲት 11 በዓል በትግራይ ክልል የተለያዩ ከተሞች በተለያዩ ስነ ስርዓቶች እመከበሩን ቀጥሏል። ተጨማሪ ዝርዝር መረጃዎችን ተከታትለን እናጋራለን።

[PHOTO : TPLF]
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#የካቲት11

ህወሓት የተመሰረተበት 45ኛው ዓመት የካቲት 11 በዓል ምክንያት በማድረግ በዛሬው ዕለት 08/06/12 ዓ/ም ከተለያዩ የሀገሪቱ ህብረተሰብ ክፍሎችና አደረጃጀቶች የነፃነት ችቦ የተለኮሰባትን ደደቢት መጎብኘታቸውን ህወሓት በይፋዊ የፌስቡክ ገፁ ገልጿል።

በጉብኝቱ የፌደራሊስት ሓይሎች ተወካዮች ፣ የምሁራን ፎረም ፣ የወጣቶች ፎረም ፣ ያገር ሽማግሌዎች፣ እንዲሁም ከ 9 የአገራችን ክልሎች የተውጣጡ የማህበረሰብ ተወካዮች እንዲሁም የኢህአዴግ ነባር አመራሮች በድምር ከ300 ሰው በላይ ላይ ተሳትፈዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#የካቲት11

45ኛው ዓመት ህወሓት የተመሰረተበት የየካቲት 11 በዓል የተለያዩ ህብረ ብሄራዊ ፌደራሊስት ኃይሎች፣ የፌደራልና የክልል መንግስት አመራሮች፣ ነባር ታጋዮች እና ምራሁራን በተገኙበት የፓናል ውይይት በዛሬው ዕለት ተካሂዷል።

በሌላ መረጃ፦

45 ተኛው ዓመት የትግራይ ህዝብ የትጥቅ ትግል የጀመረበት የካቲት 11 በዓል ምክንያት በማድረግ ከጎረቤት ሀገር ሱዳን የመጡ እንግዶች ጋር የፓነል ዉይይት ተካሂዷል፡፡

#ትግራይቴሌቪዥን
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#የካቲት11

የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ /ህወሓት/ 45ኛ ዓመት የምስረታ በዓል በመቐለ ትግራይ ስታዲየም በመከበር ላይ ይገኛል። ማለዳ ላይ በዓሉን በማስመልከት በሰማዕታት ሀውልት የክልሉ ከፍተኛ ባለስልጣናት እና ነባር ታጋዮች የአበባ ጉንጉን አኑረዋል።

በአሁኑ ሰዓት የከተማዋ ነዋሪዎች በተገኙበት በትግራይ ስታዲየም እየተከበረ ሲሆን፥ የትግራይ ክልል ምክትል ርእሰ መስተዳድር ዶክተር ደብረፅዮን ገብረሚካኤልን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች እና ነባር ታጋዮች በተገኙበት ነው እየተከበረ የሚገኘው።

#TIGRAYCOMMUNICATION #FBC
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ፎቶዎች ከትግራይ ስታዲየም መቐለ...

#የካቲት11 - የትግራይ ህዝብ የደርግ ስርዓትን ለመገርሰሰ የትጥቅ ትግል የጀመረበት 45ኛው ዓመት የየካቲት 11 በዓል "በመስመራችን ጸንተን ለመመከት" በሚል መሪ ቃል በትግራይ ስታዲየም በድምቀት ተክብሯል።

#TPLF
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#የካቲት11 #ሚሊንየምአዳራሽ #ህወሓት

የህወሀት 45ኛ ዓመት የምስረታ በአል የማጠቃለያ ዝግጅት በድርጅቱ ደጋፊዎችና አዲስ አበባ የሚገኙ የክልሉ ተወላጆች በሚለኒየም አዳራሽ በደማቅ ሁኔታ መከበሩን ቀጥሏል።

በበዓሉ ላይም በርካታ የድርጅቱ ከፍተኛ አመራሮች ፣ ደጋፊዎች፣ አባላትና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

በአሁኑ ሰዓት በትግሉ ወቅት የነበሩ ማነቃቂያ ሙዚቃዎችና ሙዚቃዊ ድራማዎች በበዓሉ ለተገኙ ታዳሚዎች እየቀረበ ይገኛል። የይህም ትግራይ ህዝብ የደርግ ስርዓትን ለመገርሰስ የከፈለውን መስዋዕትነት እየተዘከረ ያለበት መድረክ ነው።

#TikvahFamily

የቲክቫህ ቤተሰቦች ከሚሊኒየም አዳራሽ!

PHOTO : የትግራይ ኮሚኒኬሽን
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia