TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ሞሮኮ

እጅግ አስደንጋጭ ነው በተባለው የሞሮኮ መሬት መንቀጥቀጥ ከ1 ሺህ በላይ ሰዎች ሞቱ።

በሞሮኮ በመሬት መንቀጥቀጥ እስካሁን  ባለው 1,305 ሰዎች መሞታቸው ታውቋል።

ቢቢሲ ኒውስ ፤ የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴርን ዋቢ አድርጎ እንደዘገበው የተከሰተው 6.8 የተለካ የመሬት መንቀጥቀጥ ሲሆን በዚህም እጅግ በጣም ከፍተኛ ጉዳት ደርሷል።

በዋነኛነት የመሬት መንቀጥቀጡ የተሰማው በአትላስ ተራራ አካባቢ ነው ተብሏል።

ይህም ከማራኬሽ በደቡብ ምዕራብ 71 ኪሎ ሜትር ርቆ ይገኛል። ጥልቀቱም 18.5 ኪሎ ሜትር ነው። በማራኬሽና በሌሎችም ደቡባዊ አካባቢዎች ሰዎች መሞታቸው ተገልጿል።

አል-ሀውዝ፣ ማራኬሽ፣ ኦራዛቴ፣ አዚል፣ ክሪቾዋ እና ታራውዳንት በተባሉት አካባቢዎች በርካታ ሰዎች ሞተዋል።

በመሬት መንቀጥቀጡ ሕንጻዎችና ጎዳናዎች ሲናዱ ታይተዋል።

ሞሮኮ በደረሰው አደጋ የ3 ቀን ሀዘን አውጃለች።

በመሬት መንቀጥቀጡ ምክንያት በደረሰው ጉዳት የኢትዮጵያ መሪን ጨምሮ የሀገራትና ተቋማት መሪዎች ሀዘናቸውን እና ለሞሮኮ ህዝብ ያላቸውን አጋርነት እየገለፁ ይገኛሉ።

NB. የሟቾች ቁጥር አሁን ካለውም ይጨምራል ተብሎ ይጠበቃል።

@tikvahethiopia
#ሊቢያ

በምስራቃዊ ሊቢያ የምትገኘውን " ዴርና " ከተማን በመታው ኃይለኛ አውሎ ንፋስ እና ጎርፍ ምክንያት 2000 የሚደርሱ ሰዎች ሳይሞቱ እንዳልቀረ ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን እየዘገቡ ይገኛሉ።

7000 ሰዎችም የገቡበት አይታወቅም ተብሏል።

በቤንጋዚ የሚገኘው የቀይ ጨረቃ ኃላፊ ካይስ ፋከሪ እንደተናገሩት " ዳንኤል " በተባለው አውሎ ንፋስ በዴርና ከተማ ባደረሰው ጥፋት ቢያንስ 150 ሰዎችን ሞተዋል።

በከተማዋ ሁለት ግድቦች መደርመሳቸውም ተነግሯል።

ከቀናት በፊት በሌላኛዋ የአፍሪካ ሀገር #ሞሮኮ በደረሰ የመሬት መንቀጥቀጥ ከ2000 በላይ ሰዎች ሞተዋል።

@tikvahethiopia