TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.4K photos
1.47K videos
209 files
4.04K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update አዲስ አበባ⬆️

በአዲስ አበባ ከተማ በተለያዩ አካባቢዎች ህገ ወጥ የውጭ #ምንዛሬ ግብይት ሲካሄድባቸው የነበሩ በርካታ የንግድ ቤቶች መታሸጋቸው ተሰማ።

የንግድ ቤቶቹ የታሸጉት በአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ በሚመራ ግብረ ሀይል ሲሆን፥ ፖሊስ ከትናንት ጀምሮ ባካሄደው ድንገተኛ ክትትል እና ፍተሻ መሆኑንም ለማወቅ ተችሏል።

የንግድ ቤቶቹ የታሸጉበት ምክንያት፦

📌በህጋዊ የንግድ ፍቃድ ህገ ወጥ ተግባር በመፈፀማቸው ነው። ተግባሩም ህገ ወጥ መንገድ የውጭ ምንዛሬ በህገ ወጥ መንገድ የውጭ ሀገራት ገንዘብን #መግዛት እና #መሸጥ ድርጊት ነው።

በዚም በአዲስ አበባ ከተማ ቂርቆስ ክፍለከተማ ጋንዲ ሆስፒታል፣ ኢትዮጵያ ሆቴል እና ቴሌ ባር አካባቢ የሚገኙ የንግድ ቤቶች ታሽገዋል።

እንዲሁም በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ አሜሪካ ጊቢ ተብሎ በሚጠራ አካባቢ እና በቦሌ ክፍለ ከተማ ሁለት አካባቢዎች ላይ የሚገኙ የሚገኙ የንግድ ሱቆች ናቸው በተደረገው ፍተሻ ተለይተው ታሽገዋል።

📌በፍተሻው ወቅት በርካታ የውጭ ሀገራት እና የሀገር ውስጥ ገንዘቦችም በቁጥጥር ስር ውለዋል።

©fbc ፎቶ(ካፒታል)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ምንዛሬ

የዛሬው ከሰዓት የግል ባንኮች የምንዛሬ ዋጋ ምን ይመስላል ?

ዶላር እና ዩሮን ጨምሮ ሌሎች የውጭ ምንዛሬዎች በጣም ጨምረዋል።

ለአብነት እንመልከት ፦

➡️ አቢሲንያ ባንክ
💵 ዶላር መግዣው 79.8507 ፤ መሸጫው 82.2462
💶 ዩሮ መግዣው 86.3185 ፤ መሸጫው 88.9081
💷 ፓውንድ ስተርሊንግ መግዣው 97.6361 ፤ መሸጫው 100.5652
🇦🇪UAE ድርሃም መግዣው 19.4589 ፤ መሸጫው 20.0426

➡️ ሲንቄ ባንክ
💵 ዶላር መግዣው 81.2399 ፤ መሸጫው 82.8647
💶 ዩሮ መግዣው 87.5402 ፤ መሸጫው 89.2910
💷 ፓውንድ ስተርሊንግ መግዣው ፤98.3822 ፤ መሸጫው 100.3498
🇦🇪 UAE ድርሃም መግዣው 18.9165 ፤ መሸጫው 19.2948

➡️ ቡና ባንክ
💵 ዶላር መግዣው 80.0203 ፤ መሸጫው 82.8212
💶 ዩሮ መግዣው 83.4588 ፤ መሸጫው 87.1690
💷 ፓውንድ ስተርሊንግ መግዣው 94.4014 ፤ መሸጫው 98.5980
🇦🇪 UAE ድርሃም መግዣው 18.4140 ፤ መሸጫው 19.6508

#Floating_exchange_rate

@tikvahethiopia