TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.2K photos
1.5K videos
211 files
4.1K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ETHIOPIA

ነፍጥ ያነገቡ ሁሉ #ነፍጣቸውን_አስቀምጠው ወደ ምክክር መድረኩ እንዲመጡ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ሰብሳቢ ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ ጥሪ አቀረቡ።

ፕሮፌሰር መስፍን ፤ ጠብመንጃ ጥቅም እንደሌለው ቢያንስ ላለፉት 40 እና 50 ዓመታት አይተናል ያሉ ሲሆን ለሰላም የትኛውንም ዋጋ መክፈል እንደሚገባ ገልፀዋል።

ለሰላም ከሚከፈለው ዋጋ ደግሞ ፤ " መጀመሪያ ላይ ሰላምን መንከባከብ ቢሆን ውጤታማ ነው ፤ ሰላም ከደፈረሰ በኃላ ግን ሰላምን ለማስከበር የሚነሳው ነፍጥ የበለጠ ሰላምን እያደፈረሰው ነው የሚሄደው "  ሲሉ አስረድተዋል።

" የነፍጥን የሰላም ማስከበር ሂደት አይተነዋል ፤ አይጠቅምም ስለዚህም የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን እያለ ያለው ነፍጥ / ጠብመንጃ ይቀመጥ ! እስኪ ለጊዜው ጠብመንጃውን እናስቀምጠውና ወደ ምክክር ጠረጴዛው ተገናኝተን እንወያይ ከተወያየን የማይፈታ ነገር የለም ነው " ሲሉ አክለዋል።

ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ ፤ ነፍጥ ባነገቡ አካላት የህዝቡ ስቃይ እየተባባሰ መሆኑን ገልፀው በሁሉም አቅጣጫ ነፍጥ ያነገቡ ነፍጣቸውን አስቀምጠው ወደ ውይይት እና ምክክር መድረኩ እንዲመጡ ጥሪ አቅርበውላቸዋል።

" የትኛውም የሀገራችን ክፍል ያለው ህዝብ በቅቶታል፣ ተሰላችቷል ብዬ ነው የማስበው " ያሉት የኮሚሽኑ ሰብሳቢ በ2015 ዓ/ም ሁሉም በሰላም ዙሪያ የሚሰባሰብበት ጊዜ እና ኢትዮጵያውያን የእራሳችንን አጀንዳ እራሳችን በመቅረፅ ተወያይተን ምንግባባበት እንደሚሆን ተስፋ እንዳላቸው ገልጸዋል።

ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ ፥ " በምዕራብ ይሁን ሰሜን ይሁን ያሉ ወገኖች በአስቸኳይ ነፍጥ ያስቀምጡና ወደ ውይይቱ መድረክ ይምጡ ፣ በየቦታው ያሉ ፣ ግጭት ውስጥ ያሉ ፣ ጦርነት ውስጥ ያሉ መሪዎች ልቦና ሰጥቷቸው ፤ ለህዝባቸው ተቆርቁረው ህዝባችን ይብቃው ሰቆቃ በዝቶበታል ስለዚህ ያለን አማራጭ በዚህ ባቋቋምነው ኮሚሽን በተቻለ መጠን ወደ ቀላሉና ውዱ ነገር የሰላም ፍለጋ መድረክ እንድንገናኝ ነው ጥሪ የማቀርበው " ብለዋል።

@tikvahethiopia