TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.7K photos
1.49K videos
211 files
4.06K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#ትምራን ትምራን ከኢትዮጵያ ሴቶች ማህበራት ቅንጅት (NEWA) ጋር በመተባበር ነገ ሀሙስ " የሴቶች የሰላም የእግር ጉዞ " ይካሂዳሉ። በዚህም ወቅት ለመጪው አዲስ አመት የሰላም ምኞቶ የሚተላለፍበት እንዲሁም ግጭቱ እንዲቆምና ሴቶች በሰላም ግንባታ ተግባራት ውስጥ እንዲሳተፋ የሚጠየቅበት መርሀግብር ይኖረናል ተብሏል። የእግር ጉዞው ከጠዋቱ 1 ሰዓት ላይ በካዛንቺ ሴቶች አደባባይ ጀምሮ መስቀል አደባባይ…
ፎቶ ፦ ትምራን ከኢትዮጵያ ሴቶች ማህበራት ቅንጅት (NEWA) ጋር በመተባበር ያዘጋጁት " የሴቶች የሰላም የእግር ጉዞ " ዛሬ ሀሙስ በአዲስ አበባ ተካሂዷል።

የእግር ጉዞ ተሳያፊዎቹ ለመጪው አዲስ አመት የሰላም ምኞታቸውን ያስተላለፉ ሲሆን በሀገራችን ግጭቱ እንዲቆምና ሴቶች በሰላም ግንባታ ተግባራት ውስጥ እንዲሳተፋ ጠይቀዋል።

በዕለቱ ከተላለፉ መልዕክቶች መካከል ፦

🪧 #በቃን መደፈር !
🪧 የሀገር ሰላም የሴቶችም ሰላም እና ደህንነት ነው !
🪧 የሴቶች ሰውነት የጦር ሜዳ አይደለም !
🪧 ጦርነት የሞት፣ የረሃብ፣ የስደት እና የጥፋት መንስኤ እንጂ የልማት መሳሪያ አይደለም !
🪧 በጦርነት የትኛውም አይነት አለመግባባት መፍትሄ አግኝቶ አያውቅም። እኛ የኢትዮጵያ ሴቶች ሰላማዊ የግጭት መፍቻ ዘዴዎችን እንደግፋለን የሚሉት ይገኙበታል።

የፎቶ ባለቤት ፦ የኢትዮጵያ ሴት የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋቾች ጥምረት

@tikvahethiopia
#AI2022 #ኢትዮጵያ🇪🇹

ሀገራችን ኢትዮጵያ የመጀመሪየውን የፓን አፍሪካን የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) ኮንፈረንስ ልታካሂድ ነው።

ኮንፈረንሱ ከጥቅምት 4 እስከ 5 (2022) ድረስ ነው የሚካሄደው።

ይኸው የመጀመሪያ የሆነው ኮንፈረንስ የሚካሄደው በአዲሱ የሥነ ጥበብ እና ሳይንስ ሙዚየም መሆኑ ታውቋል።

ኮንፈረንሱን ለመታደም ለመመዝገብ : panafriconai.org

Via Billene Seyoum (ቢልለኔ ስዩም)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update ሩቶ እ.ኤ.አ. መስከረም 13 አምስተኛው የኬንያ ፕሬዜዳንት ሆነው ቃለ መሃላ ይፈፅማሉ። በዛሬው ዕለት የጎረቤት ሀገር ኬንያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የዊሊያም ሩቶን ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ማሸነፍ አፅንቷል። ፍርድ ቤቱ የነሀሴ 9 (እኤአ) ድምጽ ውጤት እንዲሰረዝ ለማድረግ የቀረቡ ሁሉንም ክሶች ውድቅ አድርጓል። ሩቶ በመጪው መስከረም 13 (እኤአ) የኬንያ አምስተኛው ፕሬዝዳንት ሆነው ቃለ መሃላ…
የሩቶ በዓለ ሲመት ማክሰኞ ይካሄዳል።

የተመራጩ የኬንያ ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ በዓለ ሲመታቸዉ ማክሰኞ በኬንያ መዲና ናይሮቢ የሚካሄድ ሲሆን ለዚሁ በዓለ #ኢትዮጵያን 🇪🇹 ጋብዘዋል።

የኬንያ 5ኛው ፕሬዝዳንት በመሆን የተመረጡት ሩቶ መንበረ ሥልጣኑን ከፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ በሚረከቡበት በዚህ ቀን ከኢትዮጵያ መሪ በተጨማሪ ከ40 በላይ የሃገራት መንግሥታት እና የመንግሥታት ተጠሪዎችን መጋበዛቸው ተሰምቷል።

በሥነ-ስርዓቱ ላይ እንዲገኙ ከተጋበዙት መካከል፤ የግብጽ፤ ዩጋንዳ፤ ናይጀሪያ፤ ጋና እና የደቡብ አፍሪቃ መሪዎች ይገኙበታል።

የአውሮፓ ህብረት፣ የአፍሪቃ ህብረትና መንግሥታዊ የልማት ጉዳይ ባለሥልጣናት ተወካዮች በሥነ-ስርዓቱ ላይ ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።

መረጃውን ዴይሊ ኔሽንን ዋቢ አድርጎ የዘገበው ዶቼ ቨለ ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ንግስት ኤልዛቤት ዳግማዊት ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ። የ96 ዓመቷ ዩናይትድ ኪንግደም እና የኮመን ዌልዝ አገራት ንግሥት ኤልዛቤት ዳግማዊት  በ96 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል። የንግስቷን ህልፈት ባኪንግሃም ቤተ-መንግሥት አሳውቋል። @tikvahethiopia
የንግስት ኤልዛቤት ዳግማዊት ህልፈትን ተከትሎ የዓለም ሀገራት መሪዎች እና ተቋማት ሀዘናቸውን እየገለፁ ይገኛሉ።

የኢትዮጵያ መሪ ጠ/ሚ ዶክተር ዐቢይ አህመድም በንግስቷ ህልፈት የተሰማቸውን ሀዘን በኢትዮጵያ መንግስት እና ህዝብ ስም ገልጸዋል።

ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በተረጋገጠ የትዊተር ገፃቸው ባሰራጩት የሀዘን መልዕት ፤ " በመንግስት እና በኢትዮጵያ ህዝብ ስም የተሰማኝን ሀዘን ለንጉሳውያን ቤተሰብ (The Royal Family) ፣ ለብሪታኒያ መንግስትና ህዝብ መግለፅ እወዳለሁ " ብለዋል።

ዩናይትድ ኪንግደም እና የኮመን ዌልዝ አገራት ንግሥት ኤልዛቤት ዳግማዊት ትላንት ሀሙስ ጳጉሜን 3 በ96 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸው ይታወቃል።

ፎቶ ፦ ፋይል

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
* Update

የአሜሪካው የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ማይክ ሐመር ከኢትዮጵያ ምክትል ጠ/ሚ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን እና ከጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ የብሄራዊ ደህንነት አማካሪ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ጋር መነጋገራቸውን የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት አሳውቋል።

ሐመር በዚሁ ወቅት ጦርነት በአስቸኳይ ቆሞ ፤ በአፍሪካ ህብረት (AU) መሪነት ወደ ሰላም ድርድር ማምራት እንደሚያስፈልግ መወያየታቸውን መስሪያ ቤቱ ገልጿል።

ሐመር ከህወሓት ሊቀመምበር ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል ጋር እንዴት/በምን ተገናኝተው እንደተነጋገሩ ባይገለፅም ለእሳቸውም ጦርነት በአስቸኳይ ቆሞ በአፍሪካ ህብረት መሪነት ወደ ሰላም ድርድር ማምራት እንደሚያስፈልግ እንዳስገነዘቧቸው ተገልጿል።

እንደ አሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መግለጫ በሰሜን ኢትዮጵያ ያለውን ግጭት ለማስቆም እና ወደ ድርድር ለመግባት በመጪዎቹ ቀናት የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ፀሀፊ ሞሊ ፊ ፣ አምባሳደር ማይክ ሀመር እና ሌሎችም የአሜሪካ ዲፕሎማቶች ከአፍሪካ ህብረት እንዲሁም ከቀጠናው ቀልፍ ናቸው ከሚባሉት ተዋናዮች ተመድ ፣ አውሮፓ ህብረት ፣ ከዩናይትድ ኪንግደም ልዑካን ጋር ይመክራሉ።

መስሪያ ቤቱ ፤ የአሜሪካ ዓላማ በኢትዮጵያ መንግስት እና ህወሓት መካከል ያለው ግጭት በአስቸኳይ እንዲቆም ፤ ኤርትራም ወደ ድንበሯ እንድትመለስ ዴፕሎማሲያዊ ግፊት ማድረግ ነው ብሏል።

ለግጭቱ ምንም አይነት ወታደራዊ መፍትሄ የለውም ያለው የአሜሪካ መንግስት መፍትሄድ በሁሉም ወገን ዘንድ የሰላም ድርድር ማድረግ ብቻ ነው ብሏል።

አሜሪካ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሯ በኩል ለኢትዮጵያ #አንድነት#ሉዓላዊነት#የግዛት_አንድነት ቁርጠኛ አቋም አለኝ ስትልም በድጋሚ ማረጋገጧን ቪኦኤ ሬድዮ ዘግቧል።

ፎቶ ፦ ፋይል

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
* Update

" መግለጫው ኃላፊነት የጎደለውና ተቀባይነት የሌለው ነው " - ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በተመድ የተቋቋመው ዓለም አቀፉ የሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ባለሙያዎች ኢትዮጵያን በተመለከተ ያወጡትን መግለጫ እንደማይቀበለው ገልጿል።

የኮሚሽኑ ባለሙያዎች መግለጫ " ሃላፊነት የጎደለውና ተቀባይነት የሌለው " ነው ሲል አስታውቋል።

ኮሚሽኑ ህወሓት የሰብአዊ ተኩስ አቁሙን በመጣስ ስለፈጸመው ጠብ አጫሪነት ምንም አለማለቱን የገለፀው ሚኒስቴሩ ፤ ኮሚሽኑ ለሰላምና ለደህንነት ስጋት በሆኑ ጉዳዮች ላይ የመናገርም ሆነ የመወሰን ስልጣን እንደሌለው ገልጿል።

ነገር ግን ኮሚሽኑ የፀጥታው ም/ቤት በኢትዮጵያ ላይ እርምጃ እንዲወስድ ጥሪ ማቅረቡ የኮሚሽኑን ሃላፊነት የጎደለው ባህሪ እንደሚያሳይ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስገንዝቧል።

ይህ ድርጊትም መንግስት የኮሚሽኑ እንቅስቃሴና ስራ ፖለቲካዊ ይዘት አለው በሚል የሚያነሳውን ሃሳብ ያረጋገጠ ሆኗል ብሏል።

ኮሚሽኑ የሰብአዊ መብት ጉዳዮችን የፖለቲካ ጫና ለማሳረፍ እየተጠቀመባቸው እንደሆነ የገለፀው ሚኒስቴሩ ይህ አካሄዱ የኮሚሽኑን እውነተኛ ማንነት ያጋለጠ መሆኑንም ነው ያስታወቀው።

የኮሚሽኑን መግለጫ ውድቅ ያደረገው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መንግስት የሰብአዊ መብቶችን በማክበር እና በማስከበር አጥፊዎችን ለህግ ለማቅረብ ቁርጠኛ መሆኑን አረጋግጧል።

(የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር)

@tikvahethiopia
* መልዕክት

የኢትየጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የ2015 ዓ/ም የአዲስ ዘመን መለወጫ በዓልን ምክንያት በማድረግ መልዕክት አስተላልፋለች።

አባ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ካስተላለፉት መልዕክት ፦

" በአዲሱ ዓመት ለኢትዮጵያውያን ልጆቻችንና ወገኖቻችን ሁሉ በአጽንዖት የምንመክረው ዓቢይ ምክር በግጭት ችግሮቻችንን መፍታት በፍጹም አንችልም፤ በመራራቅም ማደግ አንችልም ፤ በተለያየን ቊጥር ድህነታችንን ከማስቀጠልና ደካሞች ከመሆን በቀር የምናገኘው አንዳች ፋይዳ የለም፤ እውነቱ ይህ ከሆነ ከገባንበት ያላስፈላጊ ግጭት በፍጥነት ወጥተን ዘላቂ መፍትሔ ማምጣት ወደሚያስችል ወደ ምክክርና ውይይት እንግባ፤ አዲሱ ዓመት እውነተኛ አዲስ ዓመት ሊሆን የሚችለው ይህንን ያደረግን እንደሆነ ነው፡፡

አሮጌውን አስተሳሰብ እንዳለ ተሸክመን ለመቀጠል እየዳዳን ከሆነ አዲስ ዓመት ማለቱ የአፍና የጆሮ ቀለብ ከመሆን በቀር የሚሰጠን አንዳች ትርጉም የለም፡፡

ስለሆነም አዲሱን ዓመት አዲስ የሆነ የሰላምና የዕርቅ የስምምነትና የአንድነት የይቅርታና የምሕረት የፍትሕና የእኩልነት መርሕ አንግበን ፍጹም ሰላምን ለማንገሥ በቊርጥ ማሰብና መነሣሣት አለብን፣ ይህንንም ለማሳካት በአንድ አዳራሽ፣ በአንድ ጠረጴዛ ተገናኝተን ችግሮቻችንን በውይይትና በምክክር እንድንፈታ በዚህ አጋጣሚ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡

አዲሱ ዓመት የሰላም የፍቅር የበረከት የዕድገት የሃይማኖትና የልማት ዓመት እንዲሆንልን ወደ እግዚአብሔር በመጸለይና በብሩህ ተስፋ እንድንቀበለው መልእክታችንን በድጋሚ በእግዚአብሔር ስም እናስተላልፋለን፡፡ "

(ሙሉ መልዕክታቸው ከላይ ተያይዟል - ያንብቡ)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
* መልዕክት

የኢትየጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን የ2015 ዓ/ም የአዲስ ዘመን መለወጫ በዓልን ምክንያት በማድረግ መልዕክት አስተላልፋለች።

ብፅዕ ካርዲናል ብርሃነየሱስ የኢትየጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ሊቀጳጳሳት ለመላው ምዕመናን ካስተላለፉት መልዕክት ፦

" የተወደዳችሁ የአገራችን ህዝቦች አገራችን በውስጣዊ ጦርነት ላይ የምትገኝ ቢሆንም ጦርነት ለማንም የማይበጅ አጥፊ ስለሆነ በአዲሱ ዓመት ሁሉም ወገኖች ለሰላምና ለእርቅ ቦታ ሰጥተው ወደ ውይይት እንዲቀርቡና እንዲነጋገሩ አገራቸውንና ሕዝባቸውን ከጥፋት እንዲያድኑ ቤተክርስቲያናችን ትማፀናቸዋለች፡፡ምዕመናንም እግዚአብሔር ሰላሙን እንዲሰጠን በጸሎት እንዲተጉ አደራ እንላለን፡፡

በዘመን መለወጫ በዓላችን ሁላችንም በምንችለውን ዓይነት በችግርና በመከራ በጭንቀት ላይ የሚገኙትን ወገኖች በማሰብ አቅማችን በሚፈቅደዉ መጠን በመተጋገዝና በመረዳዳት በዓሉን እንድናሳልፍ አደራ ማለት እወዳለሁ።

በመጨረሻም ለመላዉ የአገራችን ሕዝቦች በሙሉ በየሆስፒታሉና በቤታችሁ በህመም ላይ ያላችሁ የእርሱን ምህረትን፣ በየማረሚያ ቤቶች ለምትገኙ የሕግ ታራሚዎች መፈታትን፣ በግጭት ቀጠናዎች ውስጥ ያላችሁ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን እንዲሁም የመንፈስ ልጆቻችን እግዚአብሔር ሰላሙን እንዲያወርድላችሁ፣ በተለያየ ምክንያት በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገራት በስደት ላይ የምትገኙ ወገኖቻችን ለአገራችሁና ለአካባቢያችሁ  እንዲያበቃችሁ እየተመኘሁ ለሁላችንም አዲሱ ዓመት የሰላም፣ የጤና፣ የፍቅርና የበረከት፣ የመደማመጥ፣ የመወያየት፣ የመተዛዘንና የመተሳሰብ፣ የማስተዋልና የጥበብ ዘመን ይሁንልን፡፡ "

(ሙሉ መልዕክታቸው ከላይ ተያይዟል - ያንብቡ )

@tikvahethiopia
#WorldBank #Ethiopia

የዓለም ባንክ ግሩፕ ከኢትዮጵያ ጋር ያለውን አጋርነት አጠናክሮ ለማስቀጠል ቁርጠኛ መሆኑን ገልጿል።

የዓለም ባንክ ግሩፕ ባወጣው መግለጫ በኢትዮጵያ ያለው ግጭት በእጅጉ እንደሚያስበው አመልክቷል።

በርካታ ግጭቶች እንዲሁም በታሪክ የታየው አስከፊ ድርቅና ሌሎች ሁኔታዎች ጋር ተዳምረው በሚሊዮን የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያንን ክፉኛ በመጎዳታቸው ሀገሪቱ ባለፉት አመታት ያስመዘገበችውን ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ እድገት አደጋ ላይ ጥሏል ሲል ገልጿል።

የዓለም ባንክ ግሩፕ የኢትዮጵያ ህዝብ የበለጠ የመቋቋም አቅምን ለመደገፍ እና በግጭት ሁኔታዎች ውስጥ ድጋፉን ለመቀጠል ካለው ስትራቴጂ ጋር በሚስማማ መልኩ ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ጥቅም ሲል ከኢትዮጵያ ጋር ያለው አጋርነት አጠናክሮ እንደሚያስቀጥል ቁርጠኝነቱን አረጋግጧል።

በዚህም መሰረት የዓለም ባንክ ቡድን ኢትዮጵያ በመላ ሀገሪቱ የዜጎቿን መሰረታዊ አገልግሎቶች ማለትም የትምህርት፣ የምግብ ዋስትና፣ የጤና፣ የንፁህ መጠጥ ውሃ፣ የሴቶች አቅም በማጎልበት፣  የማህበራዊ እና የአካባቢ ጥበቃን ለማሟላት በምታደርገው ጥረት ድጋፉን እያደረገ መሆኑን አሳውቋል።

የዓለም ባንክ ግሩፕ ልማት ላይ ያተኮረ ድርጅት እንደመሆኑ መጠን በአባል ሀገራቱ የውስጥ አስተዳደር ጉዳዮች ላይ የመሳተፍ ሥልጣን ባይኖረውም የልማት ተራድኦ ቡድን አባል እንደመሆኑ መጠን ደግሞ የሁሉንም ኢትዮጵያውያን መብትና ጥቅም ለማስጠበቅ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር መወያየቱን እንደሚቀጥል ባወጣው መግለጫ ገልጿል።

(ተጨማሪ ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia