TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.7K photos
1.44K videos
207 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#SolianaShimeles #NEBE

የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ኮሚኒኬሽን ኃላፊ ወይዘሪት ሶሊያና ሽመልስ ፥ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የሚሰበስበው የእጩዎች ዝርዝር ላይ ምንም አይነት የሀይማኖት ስብጥር አያሳይም ሲሉ ተናገሩ።

ኃላፊዋ ይህን ያሉት ሀገራዊ ምርጫውን የሚሳተፉ እጩዎችን ቦርዱ በሀይማኖት ለይቶ እንደመዘገበ የሚጠቁም መረጃ ማህበራዊ ሚድያ ላይ እየተነገረ መሆኑን ተከትሎ ስለጉዳዩ እውነትነት ከኢትዮጵያ ቼክ ተጠይቀው በሰጡት ምላሽ ነው።

አንዳንድ አካላት የእጩዎችን የ "ሀይማኖት ስብጥር ዝርዝር" ያሳያል ያሉትን መረጃ ከምርጫ ቦርድ እንዳገኙ በመጥቀስም ሲያሰራጩ ነበር።

ወ/ሪት ሶልያና ፥ "ቦርዱ ሲጀምር በጠቅላላ 9 ሺ የሚሆኑትን የእጩዎች ዝርዝር መረጃን እስካሁን ይፋ አላረገም" ብለዋል።

አክለውም፥ ቦርዱ የሚሰበስበው የእጩዎች ዝርዝር ላይ ምንም አይነት የሀይማኖት ስብጥርን አያሳይም ሲሉ ተናግረዋል።

ኃላፊዋ፥ "እኛ የእጩዎች ሃይማኖት የሚጠይቅ ዶክመንት አንጠይቅም ፣ ስለዚህ ከምርጫ ቦርድ ተገኘ ተብሎ እየተሰራጨ ያለው መረጃ የሀሰት ነው" ሲሉ አስረድተዋል።

#ኢትዮጵያ_ቼክ

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Ethiopia 🇪🇹 #TokyoOlympics2020 በቶኪዮ 2020 (2021) በአትሌቲክሰ ሃገራችንን ከሚወክለው የልኡካን ቡድን መካከል የመጀመሪያ ዙር ተጓዥ የሆኑት የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንትና የቡድኑ ኦፊሻል ኮማንደር አትሌት ደራርቱ ቱሉና የፌዴሬሽኑ አቃቤ ነዋይ እንዲሁም የአትሌቲክስ ቡድኑ መሪ የሆኑት ዶ/ር በዛብህ ወልዴ ትላንት ምሽት ወደ ጃፓን ቶኪዮ መጓዛቸውን ፌዴሬሽኑ አሳውቋል።…
#Tokyo2020 #Ethiopia

ለቶክዮ 2020 ኦሎምፒክ ውድድር ማክሰኞ ወደ ስፍራው ያቀናው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፣ የኦሎምፒክ ኮሚቴ ልዑክ እንዲሁም የዋና ፣ ሳይክል እና ቴክዋንዶ ውድድር ተሳታፊዎች ትላንት ቶክዮ በሚገኘው ኤርፖርት ሲደርሱ መጉላላት እንደደረሰባቸው የአስትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝደንት ኮማንደር አትሌት ደራርቱ ቱሉ ገለፁ።

ኮማንደር አትሌት ደራርቱ ቱሉ ዛሬ ለ #ኢትዮጵያ_ቼክ ድረ ገፅ በሰጡት ቃል ፥ የልኡክ ቡድኑ አመራሮች ለ8 ሰአት ገደማ አየር ማረፊያ ውስጥ የቆዩ ሲሆን ተወዳዳሪዎቹ ደግሞ ከዛም የበዛ ሰአታትን ቆይተው ዛሬ ጠዋት ወደ ሆቴላቸው መድረሳቸውን ገልፀዋል።

"ይህ የሆነው አብረውን ጉዞ አድርገው የነበሩ የሌላ አፍሪካ ሀገራት ሰዎች በኮቪድ ስለተጠረጠሩ ነበር፣ ፎርም መሙላቱ እና ሌሎች ሂደቶች ረጅም ግዜ ወስደዋል፣ የተቀናጀ ነገር አልነበረም" ሲሉ አክለዋል።

ምንጭ፦ ኢትዮጵያ ቼክ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ማብራሪያ የ20/80 እና 40/60 ጉዳይ 👆 የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፦ " ... ከዕጣ አወጣጥ ስነ-ስርዓት በኋላ የተለያዩ ጥቆማዎች በመቅረባቸው የኦዲት ሥራ ስንጀምር በባንክ የተላከውና ለእጣ እንዲውል ወደ ኮምፒዩተር የተጫነው ዳታ ልዩነቶች ተግኝተዋል። በመሆኑም በእስካሁኑ የማጠራት ስራ ላልቆጠቡ ሰዎች እጣ መውጣትን ጨምሮ የተለያዩ የተዓማኒነት ጉድለቶች ታይተዋል፡፡ ከዚህ በመነሳትም…
#AddisAbaba

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና የአዲስ አበባ ካቢኔ አባል የሆኑት ወ/ሮ ያስሚን ወሃብረቢ አልታሰሩም።

ከ20/80 እና 40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ ጋር በተያያዘ በተፈጠረ ችግር የተጠረጠሩ ባለሙያዎች እና አመራር በቁጥጥር ስር እንዲውሉ መደረጉን የአ/አ አስተዳደር መግለፁ ይታወቃል።

ከዚህ ጋር በተያያዘ " ወ/ሮ ያስሚን ወሃቢረቢ በቁጥጥር ስር ዉለዋል " ተብሎ መረጃ ሲሰራጭ ነበር።

ነገር ግን ፤ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ቢሮ ሃላፊ የሆኑት ወ/ሮ ያስሚን ወሃቢረቢ በቁጥጥር ስር ውለዋል ተከባሉት ግለሰቦች መካከል እንዳልሆኑ #ኢትዮጵያ_ቼክ መረጃ ማጣሪያ ድረገፅ ከራሳቸው ከወ/ሮ ያስሚን እንዲሁም ከከተማ አስተዳደሩ ማረጋገጡን አሳውቋል።

ወ/ሮ ያስሚን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የካቢኔ አባል እንዲሁም የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል ሲሆኑ የምክር ቤቱ አባል መሆናቸው በግልፅ ሂደት ካልተነሳ በቀር ያለመከሰስ መብት አላቸው።

@tikvahethiopia