TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.7K photos
1.44K videos
207 files
3.98K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update የሜጀር ጀኔራል ክንፈ ዳኛው ወንድም አቶ #ኢሳያስ_ዳኛው በ50 ሺህ ብር ዋስ ከእስር እንዲወጡ ተወስኖላቸዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
አቶ ኢሳያስ ዳኛው‼️

መርማሪ ፖሊስ በአቶ #ኢሳያስ_ዳኛው አዲስ የምርመራ መዝገብ ላይ ይግባኝ ጠየቀ። አቶ ኢሳያስ ኢትዮ-ቴሌኮም የኤን ፒ ጅኦ (NPGO) ኃላፊ ሆነው በሚሰሩበት ወቅት ኢዲኤም(edm) ከተባለው አማካሪ ድርጅት ጋር የስራ ማማከር ውል ያለጨረታ ተዋውለዋል፤ ለ12 አማካሪዎችና ለድርጅቱ ሰራ አስኪያጅ በሰዓት ከ125-150 ዶላር ከ2001 ዓ.ም ጀመሮ እስከ 2005 ዓ.ም ድረስ ለ44 ሰዓት ያለአግባብ ክፍያ እንዲፈጸም አድርገዋል ይላል መርማሪ ፖሊስ።

እንዲሁም ይላል መርማሪ ፖሊስ ከአማካሪ ድርጅቱ ጋር የተደረገው ውል ከህግና መመሪያ ውጭ እንዲሻሻል ተጠርጣሪው አድርገዋል በማለት አዲስ የምርመራ መዝገብ የከፈተባቸው ቢሆንም ፍርድ ቤቱ በ50ሺህ ብር ዋስ እንዲወጡ መፍቀዱ ይታወሳል፡፡

መርማሪ ፖሊስ በዛሬው ችሎት በተጠርጣሪው ላይ በሙስና ወንጀል መሳተፋቸውን ለጥርጣሬ የሚያበቁ የሰውና የሰነድ ማስረጃዎች በአዲሱ የምርመራ መዝገብ ላይ ማያያዙን በማስረዳት በጉዳዩ ላይ በቂ ምርመራ ለማድረግ እና ተጨማሪ የሰውና የሰነድ ማስረጃዎችን ለማሰባሰብ የ14 ቀን ተጨማሪ ጊዜ እንደሚያስፈልገው ለፍርድ ቤቱ አስረድቷል፡፡

የተጠርጣሪው ጠበቆችም በበኩላቸው የደንበኛቸውን የዋስትና መብት ለመከልከል እና አስር ቤት ለማቆየት ካለሆነ በስተቀር እስካሁን ደረስ የቀረበ ክስ አለመኖሩን ለፍርድ ቤቱ ተቃውሟቸውን አሰምተዋል፡፡

የግራ ቀኙን ክርክር የተመለከተው የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ 1ኛ ወንጀል ችሎትም መዝገቡን መርመሮ በጉዳዩ ላይ ተገቢውን ወሳኔ ለመስጠት ለ13/06/2011 ዓ.ም ቀጠሮ መያዙን ከፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ምንጭ፦ ኢ.ፕ.ድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሰበር ዜና‼️

አቶ #ኢሳያስ_ዳኛው ከ 44.5 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር በላይ በሚሆን ከባድ የሙስና ወንጀል ተጠርጥረው #ክስ ተመሰረተባቸው፡፡

ተከሣሽ በኢትዩ ቴሌኮም የኤን.ጂ.ፒ.ኦ. (N.G.P.O.) ዳይሬክተር ሆነው ሲሰሩ የተጣለባቸውን ከፍተኛ የመንግሥት
ኃላፊነት ወደጎን በመተው በተሰጣቸው የሥራ ሥልጣን መሠረት ዜድ.ቲ.ኢ. (ZTE) ከተባለ የቻይና ኩባንያ ጋር የ44‚ 510‚ 971.00 (አርባ አራት ሚሊዩን አምስት መቶ አስር ሺህ ዘጠኝ መቶ ሰባ አንድ) የአሜሪካን ዶላር የግዥ ውል ለጊዜው ስማቸው በክሱ ውስጥ ካልተጠቀሱት (እና ካልተያዙ) ግብረአበራቸው ጋር ቀጥታ ግዥ እንዲፈጸም በማድረግ በስውር ጥቅም በመመሳጠር በመንግሥትና በኮርፖሬሽኑ የተሰጣቸውን ሹመት፣ ሥልጣን ወይም ኃላፊነት በግልጽ ተግባር ወይም በግድፈት ያላግባብ በመገልገል እንዲሁም ከተሰጣቸው ሥልጣን በላይ አልፎ በመስራት የማይገባውን ጥቅም ለማገኘት እንዲሁም ለዜድ.ቲ.ኢ. (ZTE) ለማስገኘት እና በመንግሥትና በኢትዩ ቴሌኮም ኮርፖሬሽን ጥቅም ላይ ጉዳት እንዲደርስ አድርገዋል፡፡

አቅራቢው ኩባንያም ካቀረባቸው ቴክኒካል ሰነዶች ሊገዛ የታሰበውን ዕቃ ወይም አገልግሎት በተጠየቀው ቴክኒካል እስፒሴፊኬሽን መሠረት በግልጽና በተሟል መልኩ ለማቅረብ ወይም ለመሸጥ መስማማቱ ባልተረጋገጠበት ሁኔታ፣ የዕቃውን ወይም የአገልግሎቱን የማቅረቢያ ጊዜ፣ የቅድመ ክፍያ ዋስትና፣ የአከፋፈል ሁኔታን፣ የመልካም ሥራ አፈጻፀም ዋስትና በገምጋሚ ኮሚቴ ባልተገመገመበት ሁኔታ ተከሣሽ ግዥ እንዲፈጸም ፈቅደዋል፡፡

ተከሣሽ ለዩኒቨርሲቲዎች የኔትዎርክ ግንባታ የአገልግሎት ግዥ ውል ኤን.ጂ.ፒ.ኦ. ሊጠቀምበት ይገባ የነበረውን የግዥ ማንዋል ያልተጠቀሙና በኢትዩ ቴሌኮም የግዥ መመሪያ፣ ፖሊሲና የሥነ- ሥርዓት ማንዋል እና በሌሎች አግባብነት ባላቸው የግዥ ሕጎች መሠረት በግልጽ ጨረታ በማወዳደር ከፍተኛ ብቃት ያላቸውን ተወዳዳሪዎች በመጋበዝ ከጊዜ፣ ከሐብትና ከቴክኖሎጂ አኳያ የተሻለውን መግዛት ሲገባው የግዥ ሥራን በማያመች አኳኃን በመምራትና በማስፈፀም #በኢትዩ_ቴሌኮም ላይ ከፍተኛ ጉዳት እንዲደርስ ያደረጉ በመሆናቸው በመላ ሃሳባቸውና በወንጀል ድርጊቱና በውጤቱ በሙሉ ተካፋይ በመሆን በዋና ወንጀል አድራጊነት የመንግሥትን ሥራ በማያመች አኳኃን በመምራት ከባድ የሙስና ወንጀል ተከሰዋል።

በሌላ በኩል መርማሪ ፖሊስ ከዚህ ቀደም አቶ ኢሳያስ ዳኘው ከሌሎች ግብረ አበሮቻቸው ጋር በመሆን ያለውድድርና ጨረታ ‘ኢዲኤም’ የተባለ የውጭ አማካሪ ድርጅት ጋር ውል በመፈጸም መጠርጠራቸውን አዲስ የምርመራ መዝገብ ከፍቶ ክረክር ያደረገ ቢሆንም በተጠረጠሩበት በከባድ የሙስና ወንጀል በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 10ኛ የወንጀል ችሎት ቀርበው ጉዳያቸውን ሲከታተሉ ከቆዩ በኋላ በ50 ሺህ ብር ዋስ እንዲወጡ ተፈቅዶላው የነበረ ሲሆን መርማሪ ፖሊስም ግለሰቡ በዋስ መውጣት የለባቸውም በሚል ለጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ማለቱ ይታወቃል፡፡

ይሁን እንጂ ፍርድ ቤቱ ዛሬ ጠዋት በዋለዉ ችሎት ከዚህ ቀደም በተወሰነው መሰረት ከሃገር እንዳይወጡ በተጣለ እገዳ በ50 ሺህ ዋስ እንዲለቀቁ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ውሳኔውን ያጸና ቢሆንም ዛሬ ከሰዓት ዐቃቤ ህግ #በተከሳሹ ላይ ባቀረበው ከባድ የሙስና ወንጀል ተከስ ተከሳሹ በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 15ኛ ወንጀል ችሎት ቀርበው ክሳቸው ተነቦ እንዲረዱት የተደረገ ሲሆን የክስ መቃወሚያቸውን ይዘው ለመቅረብ ለ19/06/2011 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጥቷል፡፡

ምንጭ፦ የፌዴራል ጠ/አቃቤ ሕግ
@tsegabwolde @tikvahethiopi