TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.7K photos
1.44K videos
207 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#AddisAbaba

የፍ/ቤት መጥሪያ ፈርመው ወስደው ሳይቀርቡ ቀርተዋል የተባሉት የአዲስ አበባ ቤቶች ኮርፖሬሽን ኃላፊ አቶ ሽመልስ ታምራት #ታስረው እንዲቀርቡ በፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ 3ኛ የሙስና ጉዳዮች ወንጀል ችሎት አዘዘ።

አቶ ሽመልስ "የኮንዶሚኒየም ቤቶች ዕጣ ተጭበርብሯል" ተብሎ የከባድ ሙስና ወንጀል በቀረበባቸው ተከሳሾች ላይ የዓቃቢህግ 2ኛ ምስክር ሆነው የተቆጠሩ ሲሆን መጥሪያ ፈርመው ተቀብለው ባለመቅረባቸው ምክንያት ነው ታስረው እንዲቀርቡ ፍ/ቤት ያዘዘው።

ሃምሌ 1/2014 ከኮንዶሚኒየም ቤቶች ዕጣ አወጣጥ ጋር ተያይዞ  ዕጣው ተጭበርብሯል ተብሎ የአ/አ የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ሙሉቀን ሀብቱንና ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ አብርሀም ሰርሞሌን ጨምሮ አጠቃላይ በ11 ተከሳሾች ላይ በየደረጃው የከባድ ሙስና ወንጀል ክስ ተመስርቶባቸዋል።

ተከሳሾቹ ወንጀሉን አለመፈጸማቸውንና ጥፋተኛ አለመሆናቸውን ገልጸው የሰጡትን የዕምነት ክህደት ቃል ተከትሎ ዓቃቢህግ ምስክር እንዲሰሙለት ጠይቆ ነበር።

በዚህ መሰረት ዓቃቢህግ ከቤቶቹ ዕጣ አወጣጥ ስርዓት ጋር ተያይዞ እንዲሁም ለምቷል የተባለው ሶፍትዌርን የሚመለከትና የተደረገ የኦዲት ስርዓትን ላይ ያተኮረ ምስክርነት እንዲሰማለት የምስክር ጭብጥ ካስመዘገበ በኋላ በህዳር 22/ 2015 ጀምሮ ፍ/ቤቱ የዓቃቢህግ ምስክር ቃል መሰማት ጀምሮ ነበር።

ፍ/ቤቱ እስካሁን የ8 የዓቃቤ ህግ ምስክሮችን ቃል ያዳመጠ ሲሆን በ2ኛ የዓቃቢህግ ምስክር ሆነው የተቆጠሩት የአ/አ ቤቶች ኮርፖሬሽን ኃላፊ አቶ ሽመልስ ታምራት ግን መጥሪያ ደርሷቸው ፈርመው የወሰዱ ቢሆንም በችሎት ሳይቀርቡ ቀርተዋል።

ፍ/ቤቱም ግለሰቡ በፖሊስ ታስረው በይደር እንዲቀርቡ ትዕዛዝ ሰጥቷል።

ምንጭ፦ጋዜጠኛ ታሪክ አዱኛ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ከ60 በላይ የጤና ባለሙያዎች ፤ " ጤና ሚኒስቴር በሕግ የተወሰነልንን ልዩ አበል አልከፈለንም " አሉ። የጤና ባለሙያዎቹ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ እንደገለፁት፤ የኮቪድ - 19 ወረርሽኝ መጋቢት 8 ቀን 2012 ዓ / ም መከሰቱን ተከትሎ የጤና ማኒስቴር ባወጣው ጥሪ መሠረት የኢፌደሪ ጠቅላይ ሚኒስቴር ጽሕፈት ቤት ግንቦት 18 ቀን 2012 ዓ / ም ባወጣው መመሪያ የሕክምና አገልግሎት ለሚሰጡ ለመላው ሀኪሞች በቀን…
#ጤና_ሚኒስቴር #ክስ

የፍርድ ቤት ውሳኔን በተደጋጋሚ ጣሰ የተባለው " ጤና ሚኒስቴር " ለ70 የጤና ባለሙያዎች የኮቪድ -19 ልዩ አበል እንዲከፍል ፍርድ ቤት በድጋሚ ለንግድ ባንክ ትዕዛዝ አስተላለፈበት።

70 የጤና ባለሙያዎች የኮቪድ ወረርሽኝ #ልዩ_አበል እንዲሰጣቸው በመሰረቱበት ክስ መሠረት ገንዘቡን እንዲከፍል ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሳኔ በተደጋጋሚ ጥሷል የተባለው " ጤና ሚኒስቴር " አሁንም ከንግድ ባንክ አካውንቱ #እየቆረጠ_እንዲከፍል ፍርድ ቤት በድጋሚ ለንግድ ባንክ ትዕዛዝ ማስተላለፉን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከጤና ባለሙያዎቹ ገለጻና ከተጻፈው ደብዳቤ መረዳት ችሏል።

የጤና ባለሙያዎቹ ተወካይ የፍርድ ሂደቱ በተመለከተ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ምን አሉ ?

* ፍርድ ቤት ለባንክ ሲያዝ የአሁኑ ለሁለተኛ ጊዜ ነው።

* የፋይናንስ ክፍሉ ኃላፊ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱን ድክመት ለፍርድ ቤት #ታስረው ቀርበው እንዲያስረዱ ቢታዘዝም ጉዳዩን እንዲያስፈፅም የታዘዘው የፌደራል ፖሊስ መስሪያ ቤቱ ድርስ በመሄድ ቢጠይቅም እረፍት እንደወጡና እስከ ሰኞ (ያለፈው ሳምንት ሰኞ) እንደሚመጡ አሳውቀው ነበር። ከዚያ በኋላም ፍርድ ቤት መጥተው አያውቁም።

* ታስረው እንዲቀርቡም #ከሁለት_ጊዜ_በላይ ነው የታዘዘው።

* ፍርድ ቤት በራሳቸው እንዲፈፅሙ ግን በተደጋጋሚ (ከአምስት ጊዜ በላይ) ትዛዝ ሰቶ ነበር።

* ሰዎቹ በፍፁም ለህግ ተገዢ አለመሆናቸውን እና እምቢተኝነታቸውን በተደጋጋሚ ጊዜ አሳይተውናል።

* ለፍርድ ቤት ውሳኔ ያላቸው ንቀት በቃላት የሚገለፅ አይደለም።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ፤ ይሄንን የጤና ባለሞያዎች መረጃ በማደራጀት ሂደት የጤና ሚኒስቴርን ምላሽ እና ማብራሪያ ለማካከት ብዙ ቢደክምም ምላሽ ሰጪ አላገኘም።

አሁንም #በአካልም ይሁን #በስልክ ምላሽ ሰጣለሁ የሚል የሚኒስቴር መ/ቤቱን አካል ለማስተናገድ ዝግጁ ነው።

ዝርዝሩን ያንብቡ👇
https://telegra.ph/Tikvah-Ethiopia-12-14

የመረጃው ዝግጅት በአዲስ አበባ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ነው።

@tikvahethiopia