TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.7K photos
1.44K videos
207 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ለሚመለከተው አካል‼️
(በተለይ ለሰሞነኞቹ....)
.
.
ስለማይረዱ #ማንነታቸውን
ከስራቸው ይልቅ ያምናሉ አፋቸውን
.
.
እየቀላቀሉ #ተንኮል እና #ክፋት
እየሸፋፈኑ እውነትን በሀሰት
#የሚደክመውን ሰው ቁጭ ብሎ በማማት
ትልቅ ኩነኔ ነው ላወቀው ሰው በእውነት
.
.
ያቅታል እንጂ ቁምነገር መስራት
በጣም ቀላል ነው ሰውንስ #ማማት
.
.
ስለማይረዱ ማንነታቸውን
#ከስራቸው ይልቅ ያምናሉ #አፋቸውን
.
.
ካልታገሉ በቀር አይሳካም #ምኞት
#ለየብቻ ናቸው መስራት እና ማውራት
እግዜር ከፈጠረው በዚህች ምድር ዓለም
ሆን ብሎ እንደማውራት #ቀላል ነገር የለም።
.
.
ያቅታል እንጂ ቁምነገር መስራት
በጣም ቀላል ነው ሰውንስ ማማት

©ክቡር ዶክተር አርቲስ ጥላሁን ገሰሰ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በአላማጣ ከተማ የተፈጠረው ምንድን ነው ?

በአማራ ክልል በኩል እንደሆኑና የራያ አላማጣ አካባቢ አመራር እንደሆኑ የገለጹ አንድ ስሜ አይጠቀስ ያሉ አመራር ፥ " የሕወሓት ታጣቂዎች አላማጣ በሚገኙ ነዋሪዎች ላይ  የግድያ ጥቃት እየሰነዘሩ ነው " ሲሉ ከሰዋል።

እኚሁ ስሜ አይጠቀስ ያሉ አመራር ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል ፥ " ከሰሞኑን አንድ ወጣት በሕወሓት ታጣቂዎች በግፍ ተገሏል " ብሏል።

በታጣቂዎች የተገደለው ወጣት ስሙ ያሬድ መልካሙ እንደሚባል ፤ የመብራት ሀይል ሰራተኛም እንደነበር ፤ መብራት ለመስራት ወጥቶ ታጣቂዎች በግፍ እንደገደሉት አስረድተዋል።

ከሳምንት በፊትም " የሕወሓት ታጣቂዎች በወረወሩት ቦንብ ሁለት ሰዎች ሞተዋል። ሁለቱ ደግሞ ቆስለዋል " የሚል ቃል ሰጥተዋል። 

የሰሞኑን የአንድ ሰው ግድያ ተከትሎ የአላማጣ ከተማ ነዋሪዎች ለሁለት ቀናት ሰላማዊ ሰልፍ እንደወጡ የቪድዮ ማስረጃ በመላክ ሁኔታውን አስረድተዋል።

አሁን ላይ የአላማጣ ከተማ ከንቲባ እንደሆኑ የገለጹት ዝናቡ ደስታ (ከትግራይ በኩል) ከሁለት ሳምንት በፊት በከተማው ጤና ጣብያ ፊት ለፊት ላይ በሚገኝ መጠጥ ቤት የቦንብ ጥቃት ተፈጽሞ የአንድ እናት ህይወት መጠፉቱን እና ሁለት ሰዎች መቁሰላቸውን አሳውቀዋል።

በሌላ በኩል ፤ በአሁን ሰዓት አላማጣን #በከንቲባነት የሚመራትን አካል በተመለከተ ውዝግቦች የሚስተዋሉ ሲሆን ፤ ቲክቫህ ኢትዮጵያ አሁን ከተማዋን በከንቲባት የሚመራት ማነው ? ሲል የአማራ ክልል ኮሚዩኒኬሽን ቢሮን ጠይቋል።

ቢሮው ምላሹ፣ " እኛ የምናውቀው ከተማው በክልላችን ስር እንዳለ ነው። ስለዚህ ከዚያ ውጪ ያለው ነገር #ምኞት_ብቻ_ነው " ብሏል።

በትግራይ በኩል ያለውን ምላሽ በቀጣይ የምናቀርብ ይሆናል።

በአማራና ትግራይ ክልሎች መካከል የይባኛል ጥያቄ በሚነሳባቸው የራያ አላማጣ አካባቢዎች ከሰላም ስምምነቱ ወዲህም ከወራት በፊት በትግራይና አማራ ሚሊሻዎች በተደጋጋሚ የተኩስ ልውውጥ መደረጉ አይዘነጋም።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia