" የሰላም ንግግር አሁንም ይቻላል " - አምባሳደር ዘነበ ከበደ
በጄኔቫ የኢትዮጵያ ቋሚ መልዕክተኛና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ዘነበ ከበደ በኢትዮጵያ መንግስት እና በህወሓት መካከል የሰላም ንግግር አሁንም ይቻላል ብለዋል።
ነገር ግን ፤ ይህ የሚወሰነው የሰላም ንግግርን ውድቅ አድርጎ ወደ ጦርነት ባመራው ህወሓት /TPLF/ አቋም ነው ሲሉ ገልፀዋል።
የኢትዮጵያ መንግስት ለሰላም ያለውን አቋም በዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ዘንድ ግልፅ አድርጓል ብለዋል።
በሌላ በኩል ፤ ዛሬ ከሰዓት የፌዴራል መንግስት ባወጣው መግለጫ ህወሓት የከፈተውን ወታደራዊ ጥቃት አሁንም አብብሶ ቀጥሏል ብሏል።
ቡድኑ ለሰላም የተዘረጋውን መንገድ ትቶ በሙሉ አቅሙ ለጦርነት ሲዘጋጅ ቆይታል ሲል አስታውሷል።
አሁን ላይ በተለያዩ ግንባሮች የከፈተውን ጥቃት አድማሱን በማስፋት ለፍቶ አዳሪ ንፁሃንን ኢላማ እያደረገ ነው ብሏል።
ህወሓት የሰው ማዕበል የጦርነት ስልት በመከተል በሺዎች የሚቆጠሩ ታዳጊዎችንና ወጣቶችን በገፍ እየማገደ ነው ያለው የፌዴራሉ መንግስት ቡድኑ ኃሉን አሰባስቦ በአፋር እና አማራ አዋሳኝ ቦታዎች እየተንቀሳቀሰ ነው ብሏል።
የሰላም አማራጩ እንዳለ ሆኖ ሀገር መከላከያ ሰራዊት የተከፈተውን መጠነ ሰፊ ጥቃት በተሟላ ሁኔታ እየመከተ ነው ሲል አሳውቋል።
በሰሜን ኢትዮጵያ ዳግም ግጭት ካገረሸ ወዲህ ከቀን ወደ ቀን ሁኔታዎች ከመርገብ ይልቅ የመባባስ ምልክት እያሳዩ ሲሆን እስከዛሬ በዜጎች ላይ ከደረሰው ጉዳት የበለጠ እንዳይደርስ ከየአቅጣጫው የሰላም ጥሪዎች እየቀረቡ ናቸው።
@tikvahethiopia

TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#EU
" የትግራይ ባለስልጣናት የተዘረፈውን ነዳጅ በአስቸኳይ ይመልሱ " ሲሉ የአውሮፓ ኅብረት የቀውስ ጉዳዮች ኮሚሽነር ጃኔዝ ሌናርቺክ ጠይቀዋል።
ሌናርቺክ ፤ ያለ ነዳጅ በትግራይ ውስጥ ምግብ የማድረስ ስራ ሊሰራ አይችልም ብለዋል።
የሚሊዮች ህይወት በዚህ ላይ የተመሰረተ ነው ሲሉ አስገንዝበዋል።

" ድርጊቱን በፅኑ እናወግዛለን " - የአልቾ ውሪሮ ወረዳ አስተዳደር
በስልጤ ዞን የአልቾ ውሪሮ ወረዳ አስተዳደር ፤ በቀን 19/2014 ምሽት ላይ በኦሮሚያ ክልል ሌሙ ከተማ አቅራቢያ በሰላማዊ ዜጎችና ንብረት ላይ ጥቃት መፈፀሙን አሳወቀ።
ወረዳው ጥቃቱን አጥብቆ እንደሚያወግዝ ገልጿል።
ጥቃቱ ሌሙ መግቢያ አቅራቢያ በሚገኝ ስፍራ ላይ መነሻቸውን አልቾ ውሪሮ ወረዳ በማድረግ ወደ አዲስ አበባ በመጓዝ ላይ በነበሩ አሸክርካሪዎች እና ተሽከርካሪዎች የተፈፀመ መሆኑ ተመላክቷል።
ጥቃት አድራሾቹ ለግዜው ማንነታቸው በውል እንደማይታወቅ ነገር ግን የታጠቀ ቡድን እንደሆነ ወረዳው ገልጿል።
ታጣቂ ቡድኑ ከአልቾ ውሪሮ ወረዳ ጎመንና ቅመማ ቅመም በጫኑ 2 የደረቅ ጭነት መኪናዎች (አይሱዙ) እና ለግዜው መነሻቸው ከሌላ ቦታ በሆኑ የጭነትና የህዝብ ማመላለሻ መኪኖች ላይ ጥቃቱን እንደረሰ የተገለፀ ሲሆን በጥቃቱ ምክንያት በሰው ህይወት እና በንብረት ላይ ከባድና ቀላል ጉዳት መድረሱን ተገልጿል።
የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ አማን ከድር " በወረዳችን በተለያዩ ከተሞች በአትክልትና ፍራፍሬ ንግድ ላይ በማህበር ተደራጅተው ምርቱን ከወረዳው ማዕከል በመሰብሰብ ለማዕከላዊ ገበያ በሚያቀርቡ ነጋዴዎች ምርትና ምርቱን በጫኑ አሽከርካሪዎችና የጭነት አይሱዚ ተሽከርካሪዎች ላይ ጥቃት ደርሷል " ሲሉ የነበረውን ሁኔታ ገልፀዋል።
ወረዳው ይህን ተግባር በጽኑ እንደሚየወግዘው ገልፀው በአደጋው የተጎዱ ነጋዴዎችንና አሽከርካሪዎች ፈጥነው ወደ መደበኛ ስራቸው እንዲመለሱ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚደረግ አሳውቀዋል።

" የሰላም ንግግር አሁንም ይቻላል " - አምባሳደር ዘነበ ከበደ በጄኔቫ የኢትዮጵያ ቋሚ መልዕክተኛና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ዘነበ ከበደ በኢትዮጵያ መንግስት እና በህወሓት መካከል የሰላም ንግግር አሁንም ይቻላል ብለዋል። ነገር ግን ፤ ይህ የሚወሰነው የሰላም ንግግርን ውድቅ አድርጎ ወደ ጦርነት ባመራው ህወሓት /TPLF/ አቋም ነው ሲሉ ገልፀዋል። የኢትዮጵያ መንግስት ለሰላም ያለውን አቋም በዓለም…
#KOBO
የኢትዮጵያ መከላከያ " ቆቦ " ን ለቆ መውጣቱን መንግስት ገለፀ።
የኢፌዴሪ መንግስት ኮሚኒኬሽን ማምሻውን ባወጣው መግለጫ ፥ " አሻባሪው ህወሓት የሰው ኃይል ማዕበልን በመጠቀም የቆቦ ከተማን ከውጭ በብዙ አቅጣጫ እያጠቃ ነው " ብሏል።
በሌላ በኩል ደግሞ በከተማ ውስጥ ሠርጎ ገቦችን በማሥረግ የሕዝቡን ደኅንነት አደጋ ውስጥ በሚያስገባ መልኩ የከተማ ውስጥ ውጊያ ለማድረግ የሚያስችል ሁኔታ እየፈጠረ ይገኛል ብሏል።
በዚህም ፤ " የሕዝብን ከፍተኛ ፍጅት ለማስወገድ የመከላከያ ኃይል የቆቦ ከተማን በመልቀቅ እና ወደ ኋላ መጥቶ ለመከላከል የሚስችለውን ወታደራዊ ይዞታዎችን ለመያዝ ተገዷል " ሲል አሳውቋል።
የኢፌዴሪ መንግስት ኮሚኒኬሽን ፥ " አሸባሪው ኃይል የትግራይን ወጣት እየማገደ በሕዝብ ማዕበል ማጥቃቱን ካላቆመ መከላከያ ሕጋዊ ፣ ሞራላዊና ታሪካዊ ግዴታውን ለመወጣት የሚገደድ ይሆናል " ብሏል።
ምንም እንኳን ከተለያየ አቅጣጫ ሰላም እንዲሰፍን እና መሳሪያ ወርዶ ንግግር እንዲጀመር ጥሪዎች ቢቀርቡም በሰሜን ኢትዮጵያ ዳግም ያገረሸው ግጭት ከዕለት ወደ ዕለት እየተባባሰ መጥቷል።

" እኛ ለጎንደር ከተማ እና ለህዝቡ ክብር አለን " - አቶ ኢሳያስ ጅራ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በዛሬው ዕለት የምርጫ የጠቅላላ ጉባኤውን በአዲስ አበባ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስብሰባ አዳራሽ በማካሄድ ላይ ይገኛል ። ምርጫው ከጎንደር ወደ አዲስ አበባ ለምን ተቀየረ ? " ይሄ አስተዳደራዊ ጉዳይ ነው " ያሉት የወቅቱ የፌዴሬሽኑ ፕሬዝዳንት አቶ ኢሳያስ ጅራ " ጣልቃ ገብነቶች እና…
#Update
አቶ ኢሳያስ ጅራ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንን ለቀጣዮቹ አራት ዓመታት ለመምራት በአብላጫ ድምፅ መመረጣቸው ተገልጿል።
አቶ ኢሳያስ ጅራ ለሁለተኛ የስራ ዘመን ፌዴሬሽኑን ለመምራት በሀላፊነት ተመርጠዋል።
ድምፅ ፦
• አቶ ኢሳያስ ጅራ 👉 94
• አቶ መላኩ ፈንታ 👉 27
• አቶ ቶኪቻ አለማየሁ 👉 17
https://t.iss.one/+VvwzStMNcNHmhK0x
More : @tikvahethsport

#KOBO የኢትዮጵያ መከላከያ " ቆቦ " ን ለቆ መውጣቱን መንግስት ገለፀ። የኢፌዴሪ መንግስት ኮሚኒኬሽን ማምሻውን ባወጣው መግለጫ ፥ " አሻባሪው ህወሓት የሰው ኃይል ማዕበልን በመጠቀም የቆቦ ከተማን ከውጭ በብዙ አቅጣጫ እያጠቃ ነው " ብሏል። በሌላ በኩል ደግሞ በከተማ ውስጥ ሠርጎ ገቦችን በማሥረግ የሕዝቡን ደኅንነት አደጋ ውስጥ በሚያስገባ መልኩ የከተማ ውስጥ ውጊያ ለማድረግ የሚያስችል ሁኔታ እየፈጠረ…
#ወልድያ
የወልድያ ሕዝብ ተረጋግቶ አካባቢውን እንዲጠብቅ መልዕክት ተላለፈ።
የወልድያ ከተማ አስተዳደር የከተማው ሕዝብ ተረጋግቶ አካባቢውን እንዲጠብቅ እና ለጥምሩ ጦር ደጀንነቱን አጠናክሮ እንዲቀጥል ዛሬ ጥሪ አቅርቧል።
" የሀገር መከላከያ ሰራዊት፣ የአማራ ልዩ ኃይል፣ ፋኖ እና ሚኒሻው እየተፋለሙ ነው " ያለው የወልድያ ከተማ " የአካባቢው ማኅበረሰብ አካባቢውን ተረጋግቶ በመጠቅ ለጥምር ጦሩ የተለመደ ሁለተናዊ ደጀንነቱን አጠናክሮ ይቀጥል " ሲል ጥሪውን አቅርቧል።
ከተማ አስተዳደሩ " የጦርነቱ የፍልሚያ ቦታ እስከ አሁኗ ሰዓት ድረስ ከራያ ሚዳ አልዘለለም " ያለ ሲሆን ሾልኮ ለማለፍና በወሬ ለመፍታት የተደረገው ስልትም እስካሁን አልሰመረም ብሏል።
የከተማ አስተዳደሩ ዛሬ መልዕክቱን ያሰራጨው የአካባቢውን ተጨባጭ ሁኔታ በአካላዊ እንቅስቅሴ ጭምር በማጣራት መሆኑን አመልክቷል።
ምንም እንኳን አሁንም መሳሪያ ወርዶ ችግሮች በሰላም እንዲፈቱ የሚቀርቡ የሰላም ጥሪዎች ከሀገር ውስጥ እና ከውጭ እየቀረቡ ቢሆንም በሰሜን ኢትዮጵያ ዳግም ያገረሸው ግጭት ከቀን ወደ ቀን እየተባባሰ መጥቷል። ህወሓት ከዚህ ቀደም ለሰብዓዊነት ሲባል ተኩስ አቁም በታወጀበት ወቅት ከነበረበት ቦታ ወደፊት በመምጣት የአማራ ክልል ቦታዎችን እየያዘ ነው።
በትላንትናው ዕለት በኢትዮጵያ መንግስት እንደተገለፀው የኢትዮጵያ መከላከያ ከቆቦ ከተማ ለቆ ወጥቷል፤ በዚህም ቆቦ በህወሓት ስር ይገኛል።
መንግስት ፤ ህወሓት #የህዝብ_ማዕበል ስልት በመጠቀም ጥቃት እያደረሰ መሆኑን በመግለፅ የህዝብ ከፍተኛ ፍጅት ለማስወገድ መከላከያው " ቆቦ " ን መልቀቁን በትለንትናው መግለጫ ማስረዳቱ ይታወሳል።

#UN_ETHIOPIA
በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የኢትዮጵያ ቋሚ መልዕክተኛ የሆኑት አምባሳደር ታዬ አፅቀስላሴ ህወሓት ህፃናትን ለውትድርና እየመለመለና ህፃናትን በህዝብ ማዕበል ስትራቴጂ እየተጠቀመ ነው ሲሉ ገለፁ።
አምባሳደሩ ፥ እንደ ዓለም ጤና ድርጅት (WHO) እና የህፃናት መርጃ ድርጅት (UNICEF) ዓይነት ተቋማትን ጨምሮ ሌሎችንም ፤ " እውነት ስለ ህፃናት ያሳስበናል የምትሉ ይህን ድርጊት አውግዙ " ብለዋል።
የሰሜን ኢትዮጵያው ግጭት ዳግም ካገረሸ ቀናት ተቆጥረዋል። አሁንም በተለያዩ አካባቢዎች ወታደራዊ ግጭቶች መቀጠላቸውን የሚጠቁሙ መረጃዎች አሉ።

ፎቶ : እርቀ ሰላም !
በአዊ እና በመተከል ዞን አዋሳኝ ወረዳዎች በሚኖሩ ህዝቦች መካከል የሚፈጠሩ የግጭት መንስኤዎችን በዘላቂነት ለማስወገድ ዛሬ የእርቀ ሰላም ስነ ስርዓት ተካሂዷል።
በሁለቱ ዞኖች አጎራባች በሆኑ ፓዊና ጃዊ ወረዳዎች በሚኖሩ ህዝቦች የሚፈጠረውን ግጭት በዘላቂነት ለማስወገድ ተስፋ የተጣለበት ይኸው እርቀ ሰላም በጃዊ ወረዳ ወርቅ ሀገር ቀበሌ ነው የተካሄደው።
Photo Credit : መተከል ኮሚኒኬሽን

#ATTENTION
ደባርቅ !
የደባርቅ ከተማ አስተዳደር የፀጥታ ምክር ቤት ከወቅታዊ ፀጥታ ስጋት ጋር በተያያዘ የተለያዩ ውሳኔዎች ማሳለፉን አሳውቋል።
የፀጥታ ምክር ቤቱ በከተማው ውስጥ የሚገኘው የተፈናቃይ መጠለያ ነዋሪ ከ12:00 በሗላ ወደ ውስጥም ሆነ ወደ ከተማ መግባት እንደማይችል ከልክሏል።
የባጃጅ ተሽከርካሪችም ከምሽቱ 1:00 በሗላ መንቀሳቀስ እንደማይችሉ ይህን በሚያደርጉ ላይ እርምጃ እንደሚወሰድ አሳስቧል።
ሌላው፤ የከተማው ባለሆቴሎች እና ባለአልጋ ቤቶች ማንነቱ ያልታወቀ አንጋች በድርጅታቸው ሲጋጥምቻቸው ለህግ አካላት ጥቆማ እንዲሰጡ ምክር ቤቱ አሳስቧል።
የቤት አከራይዎች ቤታቸውን ሲያከራዩ ጥንቃቄ እንዲያደርጉና የሚያከራቱትን ግለሰብ ማንነት ለይታተው እንሲያውቁ በመረጃ ፎርም ሞልተው ለፀጥታ ጽ/ቤት እንዲያሳውቁ ብሏል።
ከዚህ በተጨማሪ ምክር ቤቱ መላው የከተማው ማህበረሰብ በአደረጃጀቶች አካባቢውን እንዲጠብቅ መልዕክት አስተላፍሏል።
የተላለፉትን የውሳኔ ሀሳቦች የሚጥስ ማንኛውም አካል ላይ ህጋዊ እርምጃ እንደሚወስድ አስጠንቅቋል።