TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
212 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ሰላም

" አሁንም ችግሮች በሰላማዊ መንገድ እንዲፈቱ እና በዘላቂነት ሰላም እንዲሰፍን ሁሉም ኢትዮጵያዊ ለሰላም በጋራ ሊቆም ይገባል " - ሊቀ አእላፍ ቀሲስ በላይ መኮንን

ዛሬ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ አባ ገዳዎችና አዴ ስንቄዎች በጠቅላይ ቤተክህነት ጽ/ቤት የጋራ የሰላም ጥሪ ማስተላለፋቸውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ህዝብ ግንኙነት አሳውቋል።

አገራችን ኢትዮጵያ የበርካታ ብሔሮችና ሃይማኖቶች መገኛ መሆኗን የገለጹት የሃይማኖት መሪዎቹና አባ ገዳዎቹ ሁሉም ኢትዩጵያዊ ዘርና ሃይማኖት ሳይለይ ለአገር አንድነትና ሰላም በአንድነት እንዲቆም ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።

አባ ገዳዎቹ ችግሮች ሁሉ በሰላምና በስምምነት መፈታት እንደሚገባው ገልፀዋል።

አገራችን ኢትዮጵያ እስከ አሁን ድረስ ለሰላም ቅድሚያ በመስጠት ያደረገችውና እያደረገች ያለችው ጥረት የሚደነቅ መሆኑን ገልጸው አሁንም ችግሮች ሁሉ በሰላምና በሰላም ብቻ መፍትሔ እንዲያገኙ የምታደርገውን ጥረት አጠናክራ መቀጠሏ ተገቢ ነው ብለዋል።

ይህ የሰላም ጥረት ፍሬ ያፈራ ዘንድ ሁሉም ኢትዮጵያዊ የሚደረገውን የሰላም ጥረት በአንድነት በመቆም ዘርና ሃይማኖት ሳይለዩ ሊደግፉት ይገባል ብለዋል።

የጠቅላይ ቤተክህነት ም/ዋና ሥራ አስኪያጅ ሊቀ አእላፍ ቀሲስ በላይ መኮንን በበኩላቸው ፤ " ባለፉት 5 ወራት መንግስት ለሰላም ያደረገው ጥረት ፍሬ አፍርቶ ለማየት በእጅጉ በጉጉት እየጠበቅን ባለንበት ጊዜ ሰላምን የሚያደፈርሱ  ተግባራት መታየታቸው አሳዝኖናል " ብለዋል።

አሁንም ችግሮች ሁሉ በሰላማዊ መንገድ እንዲፈቱና በዘላቂነት ሰላም እንዲሰፍን ሁሉም ኢትዮጵያዊ ለሰላም በጋራ መቆም ይኖርበታል ብለዋል።

(ተጨማሪ የኢኦተቤ ህዝብ ግንኙነት መረጃ ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
" ከረጅም ርቀት በተተኮሰ ከባድ መሳሪያ 2 ህፃናት ልጆቿን ያጣች እናት አለች " - ዶ/ር ሁሴን አደም

የህወሓት ኃይሎች በአፋር ያሎ በኩል በሰነዘሩት የከባድ መሳሪያ ጥቃት በአካባቢው ንፁሃን ነዋሪዎች ላይ ጉዳት መድረሱንና በርካቶች በያሎ አካባቢ በሚገኘው የህክምና ጣቢያ ህክምና እየተከታተሉ መሆኑ ተገልጿል።

ከባድ ጉዳት ከደረሰባቸውም ውስጥ ወደ ዱብቲ ጠቅላላ ሆስፒታል መጥተው ህክምና የተከታተሉ እንዳሉ የሆስፒታሉ ስራ አኪያጅ ዶ/ር ሁሴን አደም ተናግረዋል።

ዶ/ር ሁሴን ለቪኦኤ ሬድዮ ጣቢያ በሰጡት ቃል፥ " ጦርነቱ እንደገና ተነስቶ ዜጎች እኛ ጋር አብሶ ከረጅም ርቀት በሚተኮስ ትልቅ መሳሪያ የተጎዱ ቁስለኞች መጥተዋል፤ አብዛኞቹ ቁስለኞችን ስናያቸው ሲቪሊያን (ሰላማዊ ዜጎች) ናቸው እኛ ጋር የመጡት ለጊዜው እየተደረገ ያለው እዛው አቅራቢያ ህክምና ሚያስፈልጋቸው ዜጎች ህክምና እያገኙ ነው ፤ ከዛ የባሰ ከነሱ በላይ የሆነው ወደኛ ሆስፒታል እየላኩ ይገኛሉ። ጉዳታቸው ከሰው ሰው ይለያያል እዚህ ለመድረስ እድለኛ የሆኑት ህክምና እያገኙ ነው ለጊዜው እዚህ ከመጡ በኃላ ህይወት ያለፈ አልነበረም እስካሁን ድረስ፤ መጥፎውን አላህ ይያዝልን " ብለዋል።

እስካሁን 13 የሚደርሱ በጦርነቱ በከፍተኛ ሁኔታ የተጎዱ ዜጎች ለተሻለ ህክምና ወደሆስፒታሉ እንደገቡ ጠቁመዋል።

ተጎድተው ሆስፒታል ከገቡት ውስጥ 2 ህፃናት ልጆቿን ከረጅም ርቀት በተተኮሰ ከባድ መሳሪያ የተገደሉባት እናት እንደምትገኝ ተገልጿል።

ዶ/ር ሁሴን አደም፤ "አንድ እናት አለች 2 ህፃናት ልጆቿ የሞቱባት ከረጅም ርቀት በተተኮሰ ትልቅ መሳሪያ ቤት ውስጥ ባሉበት ሰዓት ተመተው 2 ህፃኖቿን እዛው ነው ያጣችው እሷ ግን እኛ ጋር መጥታለች የህክምና አገልግሎት እያገኘች ትገኛለች " ሲሉ ለሬድዮ ጣቢያው አስረድተዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ፎቶ : ኮሎኔል አትሌት ደራርቱ ቱሉ በባህርዳር ገቡ። ባህር ዳር ዩንቨርስቲ በነገው እለት በሚያካሂደው የተማሪዎች ምረቃ ወቅት ለብፁዕ አቡነ ኤርምያስ እንዲሁም ለኮሎኔል አትሌት ደራርቱ ቱሉ የክብር ዶክትሬት እንደሚሰጥ ማሳወቁ ይታወሳል። ይህን ተከትሎ አትሌት ደራርቱ ቱሉ ዛሬ በባህርዳር ገብተዋል። ባህር ዳር አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የባህርዳር ዩንቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ፍሬው ተገኘ…
ፎቶ ፦ የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የዓመቱን የክብር ዶክትሬት ዲግሪ ለክቡር ዶክተር ብጹዕ አቡነ ኤርምያስ እና ለክብር ዶክተር ኮማንደር አትሌት ደራርቱ ቱሉ ሰጥቷል።

ብጹዕ አቡነ ኤርምያስ በሃይማኖት አባትነታቸው የተማሩትንና ያስተማሩትን በተግባር የሚኖሩ፤ ሰውን በሰውነቱ ብቻ የሚያከብሩ፤ ታላቅ አባት ናቸው።

ኮማንደር አትሌት ደራርቱ ቱሉ በአትሌቲክ ዘርፍ ከፍተኛ አስተዋጽኦ በማበርከት ለኢትዮጵያ ብሎም ለአፍሪካ ፋና ወጊ አትሌት እና የኢትዮጵያዊነት ተምሳሌት ናቸው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Germany • ጀርመን ከWFP መጋዘን ህወሓት የፈፀመውን በኃይል የነዳጅ ክምችት የመውሰድ ድርጊት " አፀያፊ " ስትል አወገዘች። የጀርመን መንግስት በሰሜን ኢትዮጵያ ለ5 ወራት የዘለቀው የተኩስ አቁም ስምምነት መጣሱና ጦርነቱ እንደገና መጀመሩ በእጅጉ እንዳሳዘነው ገልጿል። በግጭቱ ውስጥ ያሉ ሁሉም አካላት አሁኑኑ መሳሪያቸውን አስቀምጠው ወደ ተኩስ አቁም በፍጥነት መመለስ አለባቸው ብሏል። " ግጭቱ…
#UK

የዓለም ምግብ ፕሮግራም ፤ በመቐለ ያለው ነዳጅ ክምችቱ በኃይል በህወሓት (TPLF) መዘረፉን ካሳወቀ በኃላ ተቋማትና ሀገራት ድርጊቱን ማውገዛቸውን ቀጥለዋል።

ዩናይትድ ኪንግደም ፤ ትግራይ ክልል ከሚገኘው የዓለም ምግብ ፕሮግራም (WFP) ህወሓት በኃይል ነዳጅ መውሰዱ ተቀባይነት የሌለው ነው ብላለች።

በተጨማሪ ድርጊቱ የሚሰሩትን የሰብዓዊ ድጋፍ ስራዎች በእጅጉ እንደሚጎዳው ገልፃለች።

ሁሉም ወገኖች በሰሜን ኢትዮጵያ በከፋ ሁኔታ ውስጥ ሆነው ድጋፍ ለሚጠባበቁ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ድጋፍ መድረሱን ማረጋገጥ አለባቸው ብላለች።

ለሰብዓዊነት ተብሎ ታውጆ የነበረው ተኩስ አቁም በአስቸኳይ ወደቦታው እንዲመለስም ጥሪ አቅርባለች።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Gondar " ውሳኔያችሁን በድጋሜ አጢኑት " - ጎንደር የጎንደር ከተማ አስተዳደር የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ውሳኔን #ተገቢነት_የሌለው ነው አለ ፤ ውሳኔውንም ድጋሜ እንዲያጤነው ጠይቋል። የኢትዮጵያ የእግር ኳስ ፌዴሬሽን በጎንደር ከተማ የፌዱሬሽኑን የምርጫ ጠቅላላ ጉባኤ ለማካሄድ እንደተዘጋጀ ለከተማው አስተዳደር አሳውቆ ነበር። ነገር ግን ፌዴሬሽኑ የጉባኤ ቦታው እንዲቀየር መወሰኑን የገለፀ…
" እኛ ለጎንደር ከተማ እና ለህዝቡ ክብር አለን "  - አቶ ኢሳያስ ጅራ

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በዛሬው ዕለት የምርጫ የጠቅላላ ጉባኤውን በአዲስ አበባ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስብሰባ አዳራሽ በማካሄድ ላይ ይገኛል ።

ምርጫው ከጎንደር ወደ አዲስ አበባ ለምን ተቀየረ ?

" ይሄ አስተዳደራዊ ጉዳይ ነው " ያሉት የወቅቱ የፌዴሬሽኑ ፕሬዝዳንት አቶ ኢሳያስ ጅራ " ጣልቃ ገብነቶች እና ሂደቶችን ስላየን ቦታውን ቀይረናል ፣ ውሳኔውን አስተላልፈን ለስራ አስፈፃሚ አቀረብን ሂደቱን ጠብቀን ነው ያደረግነው " ብለዋል ።

" ሂደቱ የነበረው ይህ ነው ፣ ራስን መፈተሽ አስፈላጊ ነው ፣ ይሄንን ጉባኤ በዚህ መልኩ ነው ማስኬድ ያለብህ ብሎ የመንግስት አካል ትዕዛዝ መስጠት አይችልም።

ቦታ ተቀየረ ተብሎ ጥቃቅን ጉዳይ አንስቶ አጀንዳ ማድረግ አግባብ አይደለም ፣ ደግሞም ቦታ ስንሰጥ የሰጠነው ለክልሉ ሳይሆን ለከተማው ነው።

እኛ ለጎንደር ከተማ ለህዝቡ ክብር አለን ፣ የጦርነት ወላፈን ከነካቸው ቦታዎች አንዱ ነው ሁለት ወር ለኢኮኖሚውም እገዛ ውድድር ሁሉ አድርገን የቆየነው እንጂ የሁለት ቀን ከለከሉ መባል የለብንም " በማለት አቶ ኢሳያስ ጅራ ተናግረዋል።

በዛሬው ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ከፊፋ እና ካፍ ተወክለው የመጡ ታዛቢዎችን ጨምሮ ከፍተኛ የስፖርቱ ባለስልጣናት ታድመዋል ።

ቲክቫህ ስፖርት : https://t.iss.one/+VvwzStMNcNHmhK0x

@tikvahethsport    
TIKVAH-ETHIOPIA
ሲዳማ ክልል በስንት ዞኖች ይዋቀራል ? ከሰሞኑን የሲዳማ ክልል ም/ቤት አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ፋንታዬ ከበደ በሰጡት መግለጫ ሲዳማ ክልል 4 ዞኖች እና 1 ከተማ አስተዳደር ይኖረዋል ብለዋል። የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር፣ የሀዋሳ ከተማ ዙሪያ ዞን እንዲሁም በአቅጣጫቸው የሚሰየሙ መዋቅሮች ይኖሩታል። ይህ የዞን መዋቅር ም/ቤቱ በቅርቡ በሚያካሂደው ጉባኤ ላይ ቀርቦ ምርመራ ተደርጎበት ይፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል።…
#Update

የሲዳማ ክልል የዞን አደረጃጀት ፀደቀ።

የሲዳማ ክልል ምክር ቤት የዞን አስተዳደር እና አደረጃጀትን ለማቋቋም የወጣ አዋጅ ተቀብሎ ክልሉ በ4 ዞኖች እና በ1 ከተማ አስተዳደር እንዲደራጅ ውሳኔ አሳልፏል።

የክልሉ ምክር ቤት ውሳኔውን ያሳለፈው እያካሄደ ባለው መደበኛ ጉባኤ ነው።

የዞኖቹ ስያሜዎች ሰሜን ሲዳማ ዞን፣ ማዕከላዊ ሲዳማ ዞን፣ ደቡብ ሲዳማ ዞን እና ምስራቅ ሲዳማ ዞን በሚል እንደሚጠራ ተገልጿል።

@tikvahethiopia
#ብርሃን_ባንክ

ስለ ብርሃን ስኩልፔይ (school pay) በጥቂቱ ፦

#ለወላጆች ወይም #ለተማሪዎች የትኛውም ቅርንጫፍ መሄድ ሳያስፈልግ የትምህርት ቤቱን መለያ ኮድ በመጠቀም  የትምህርት  ክፍያዎችን  መክፈል፤ የክፍያ ማረጋገጫዎችን፤ የክፍያ ሪፖርቶችን እና ተያያዥ መረጃዎችን በእጅዎ ባለው ስልክዎ በቀላሉ ማግኘት ያስችልዎታል፡፡

ለትምህርት ቤቶች ደግሞ ክፍያ ሲፈጸም ደረሰኝ ይዞ መሄድ ሳያስፈልግ ት/ቤቱ ሁሉንም ክፍያዎች በስኩልፔይ ሲስተም  ማየት እና በቀላሉ መቆጣጠር ከማስቻሉም በላይ ሙሉ የሆነ የተማሪዎችን መረጃ በመያዝ ምቹ አሰራርን ይፈጥራል፡፡

እንደ ስማችን ብርሃን ነው ስራችን!
Facebook: https://www.facebook.com/berhanbanksc
Telegram: https://t.iss.one/berhanbanksc
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update ዛሬ በመቐለ የአየር ድብደባ መፈፀሙን በዚህም በህፃናት መጫወቻ ቦታ ላይ የሰው ህይወት የነጠቀ ጉዳት መድረሱን የመቐለ ዩኒቨርሲቲ አይደር ሪፈራል ሆስፒታል መግለፁ ይታወቃል። በደረሰው ጉዳት ቀን በነበረው መረጃ አጠቃላይ 13 የሚደርሱ ሰዎች ጉዳት ደርሶባቸው ወደ ሆስፒታሉ መግባታቸውን ፤ ከነዚህ ውስጥ አራቱ እንደሞቱ ከአራቱ 2ቱ ህፃናት እንደነበሩ ገልጾ ነበር። ከዚህ ጉዳይ ጋር በተያያዘ …
#Update

- የተመድ ዋና ፀሀፊ ቃል አቀባይ ስቴፋን ዱጃሪች ምንም እንኳን UN ይሄን ለማረጋገጥ (የአየር ጥቃቱ) የሚያስችል ሁኔታ ላይ ባይሆንም በመቐለ የአየር ጥቃት መፈፀሙን የሚገልፁ ሪፖርቶች "እጅግ በጣም አሳሳቢ ናቸው" ብለዋል። በመቐለ ያሉት የተመድ አባላት ደህና ናቸው ፤ ነገር ግን ግንኙነቱ እና ሰራተኞችም ለመንቀሳቀስ ያላቸው አቅም ውስብስብ ነው ብለዋል።

- የተመድ የህፃናት መርጃ ድርጅት (UNICEF) በበኩሉ በመቐለ የአየር ጥቃት መፈፀሙን እና በዚህም ህፃናት መሞታቸውን ሌሎች ትልልቅ ሰዎች ማጎዳታቸውን በማመልክተ ድርጊቱ በፅኑ እንደሚያወግዝ ገልጿል። ሁሉም ወገኖች በፍጥነት ግጭት ይቆም ዘንድ ወደ ስምምነት እንዲመጡም ጠይቋል። አሁንም በሰሜን ኢትዮጵያ እየተባባሰ የመጣው ግጭት ህፃናት ከፍተኛ ዋጋ እንዲከፍሉ እያደረገ ነው ያለው UNICEF በክልሉ የሚኖሩ ልጆችና ቤተሰቦቻቸው ላለፉት 2 ዓመታት ግጭቱ ያመጣውን ስቃይ ተቋቁመዋል አሁን ግን ማብቃት አለበር ብሏል።

- የዩናይትድ ኪንግደም የአፍሪካ ጉዳዮች ሚኒስትር ቪኪ ፎርድ በትግራይ የተፈፀመ የአየር ድብደባን ተከትሎ በሰላማዊ ዜጎች ላይ ጉዳት መድረሱን የሚገልፁ ሪፖርቶች አስደንጋጭ ናቸው ብለዋል። ሁሉም ወገኖች ዓለም አቀፍ የሰብዓዊነት ህግን ማክበር እና ለሲቪሎች ጥበቃ ቅድሚያ መስጠት አለባቸው ብለዋል።

- የአውሮፓ ኅብረት የቀውስ ጉዳዮች ኮሚሽነር ጃኔዝ ሌናርቺክ ትላንት በመቐለ የሲቪል ሰዎችን ሞት ያስከተለ የአየር ጥቃት ተፈፅሞ እንደነበር ገልፀው ጥቃቱን እንደሚያወግዙ ገልፀዋል። ዓለምአቀፍ የሰብዓዊነት ህጎች ሊከበሩ ይገባል ሲቪሎች ዒላማ ሊሆኑ አይገባም ብለዋል። ሌናርቺክ ፤ ሁሉም ወገኖች የሰላም ድርድር እንዲያደርጉና ለተቸገሩ ሰዎች ሰብዓዊ እርዳታ እንዲደርስ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።

@tikvahethiopia