TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update #ችሎት የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በጋዜጠኛ ያየሰው ሽመልስ ላይ ተጨማሪ የሰባት ቀናት የምርመራ ጊዜ ፈቀደ። ችሎቱ 7 ቀን የምርመራ ጊዜ የፈቀደው ፖሊስ " በምርመራው የሚያጠናቅቃቸው ነገሮች ካሉ " በሚል ምክንያት መሆኑን ኢትዮጵያ ኢንሳይደር ዘግቧል። @tikvahethiopia
#Update #ችሎት

ጋዜጠኛ ያየሰው ሽመልስ በዋስ እንዲፈታ ታዘዘ።

የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ሁለተኛ ጊዜ ቀጠሮ ችሎት ጋዜጠኛ ያየሰው ሽመልስ በ10 ሺ ብር ዋስ ከእስር እንዲፈታ ዛሬ ትዕዛዝ ሰጥቷል።

ከቀናት በፊት ጋዜጠኛ ሰለሞን ሹምዬ በዋስ ከእስር መፈታቱ ይታወሳል ፤ ጋዜጠኛ መዓዛ መሐመድም በዛሬው ዕለት ከ23 ቀን እስር በኃላ መለቀቋን የምትሰራበት ሮሀ ሚዲያ አረጋግጧል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ችሎት ዛሬ የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ (ባልደራስ) አመራር የሆኑት አቶ ስንታየሁ ቸኮል ከታሰሩ ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ በአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ቀርበዋል። ሕገ መንግሥቱንና ሕገ መንግሥታዊ ስርዓቱን በኃይል ለመናድ ተንቀሳቅሰዋል የሚል ክስ እንደቀረበባቸው ክሱን ያቀረበውም የፌዴራል ፖሊስ መሆኑን የፓርቲው መረጃ ያመለክታል። ፖሊስ አቶ ስንታየሁ ፤ ሕዝብን ለተቃውሞ የሚያነሳሳ ፅሁፍ በፌስቡክ…
#Update #ችሎት

እነ አቶ ስንታየሁ ቸኮል በዋስ እንዲወጡ ታዘዘ።

የአብክመ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዛሬ ሰኔ 23/2014 ዓ/ም በዋለው ችሎት ስንታየሁ ቸኮል ፣ ያለለት ወንድዬ ፣ ዋሴ ቢረሳው እና ደምስ አያሌው የጊዜ ቀጠሮ ጉዳይ ያየ ሲሆን በክርክሩ ፖሊስ ተጨማሪ የጊዜ ቀጠሮ ጠይቋል።

ተጠርጣሪዎች በበኩላቸው ዋስትና እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል።

ፍ/ቤቱ የግራ ቀኙ ክርክር አዳምጦ ተጠርጣሪዎች እያንዳንዳቸው በ30 ሺህ ዋስትና እንዲወጡ አዟል።

መረጃው የአብክመ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ነው።

#Update

በ30ሺ ብር ዋስ ከእስር እንዲወጡ የተፈቀደላቸው የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ አመራር አቶ ስንታየሁ ቸኮል ከማረሚያ ቤቱ ሲወጡ በር ላይ የፌዴራል ፖሊስ አባላት እንደያዟቸው ከፓርቲው የተገኘው መረጃ ያሳያል።

@tikvahethiopia
#ችሎት

የቀድሞ ጠ/ሚ ኃይለማርያም ደሳለኝ እና የኢጋድ ዋና ጸሀፊ ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ እና ሌሎችም በሜ/ጀ ክንፈ ዳኘው የመርከብ ግዢ እና እርሻ መሳሪያ ክስ ላይ የመከላከያ ምስክርነታቸው በአካል ቀርበው እንዲያሰሙ #በድጋሚ ታዘዘ።

ቀደም ሲል በቨርቹዋል ቴክኖሎጂ እንዲመሰክሩ ታዞ የነበረው ትዛዝ ተቀይሮ ነው በአካል ቀርበው እንዲመሰክሩ የታዘዘው።

ከሁለት ወር በፊት የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማርያም ደሳለኝ ሜ/ጀ ክንፈ ዳኘው የእርሻ መሳሪያና የመርከብ ግዢ ሙስና ክስ ላይ በተቆጠሩበት የመከላከያ ምስክርነት በተደጋጋሚ እንዲቀርቡ ትዛዝ ተሰጥቶ ባለመቅረባቸው ምክንያት ታስረው እንዲቀርቡ መታዘዙ ይታወሳል።

" መጥሪያ ሳይደርሰኝ ታስሬ እንደበር የተሰጠው የፍርድ ቤት ትዛዝ ተገቢ አይደለም " ሲሉ ከኢትዮጲያ ውጪ እንደሚገኙና የስራ ጫና እንዳለባቸው አመላክተው በአካል ለመቅረብ እንደሚቸገሩ በመግለጽ ባሉበት ቦታ የምስክርነት አሰማሙ ቨርቹዋል ቴክኖሎጂ እንዲሆንላቸው ጠይቀው ነበር።

ያንብቡ : https://telegra.ph/Tarik-Adugna-07-04

Credit : Journalist Tarik Adugna

@tikvahethiopia
#ችሎት

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በ100 ሺህ ብር ዋስትና ከእስር እንዲለቀቅ በፍርድ ቤት ብይን ተሰጠ።

የ ሳምንታዊው “ ፍትሕ ” መጽሔት ማኔጂንግ ዳይሬክተር ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ የ100 ሺህ ብር ዋስትና በማስያዝ ጉዳዩን በውጭ ሆኖ እንዲከታተል የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ብይን ተሰጥቷል።

ፍርድ ቤቱ ብይኑን በአብላጫ ድምጽ ያስተላለፈው በዐቃቤ ህግ በኩል የቀረበውን መቃወሚያ ውድቅ በማድረግ መሆኑን ኢትዮጵያ ኢንዳይደር አስነብቧል።

@tikvahethiopia
#ችሎት

በአዲስ አበባ ከተማ ከጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ አወጣጥ ጋር በተያያዘ በቁጥጥር ስር በዋሉ ግለሰቦች ላይ ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ተፈቀደ።

ከኮንዶሚኒየም ቤቶች ዕጣ አወጣጥ ጋር በተያያዘ በቁጥጥር ስር የዋሉ ስምንት ግለሰቦች ፦
- የቴክኒክ ሙያ ስልጠና አይሲቲ ቢሮ ም/ቢሮ ኃላፊ አቶ አብርሐም ሰርሞሌ
- የቤቶች ልማት ዳታ ቤዝ ቡድን መሪ አቶ ስመኘው አባተ
- የሶፍትዌር ባለሙያዎች ፦
• ሀብታሙ ከበደ
• ዮሴፍ ሙላት
• ጌታቸው በሪሁን
• ቃሲም ከድር
- የቤቶች የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ባለሙያዎች ሚኪያስ ቶሌራ
- የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ICT ኃላፊ አቶ ኩምሳ ቶላ ላይ የ14 ቀናት የምርመራ ጊዜ በፍርድ ቤት ተፈቅዷል።

የምርመራ ጊዜውን የፈቀደው ዛሬ ሰኞ ሐምሌ 11/2014 የዋለው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት ነው። 

ችሎቱ የምርመራ ጊዜውን የፈቀደው የፌደራል ፖሊስ እና የተጠርጣሪዎቹ ጠበቆች ባለፈው ሳምንት አርብ ሐምሌ 8/2014 ያደረጉትን ክርክር ከመረመረ በኋላ ነው።

የጊዜ ቀጠሮ ችሎቱ በዛሬ ውሎው የተጠርጣሪዎቹ በዋስትና መውጣት “ምርመራው የተፈለገውን ውጤት እንዳያስገኝ ሊያደርግ ስለሚችል” በሚል ጠበቆች ያቀረቡትን የዋስትና ጥያቄ ውድቅ ማድረጉን " ኢትዮጵያ ኢንሳይደር " ዘግቧል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ችሎት

• ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ የዋስትና መብቱ ውድቅ ተደረገ።

• ጠቅላይ ፍርድ ቤት ጋዜጠኛ ተመስገን ወይኒ ቤት እንዲወርድ አዟል።

የጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ የዋስትና መብቱ ላይ አቃቤ ህግ ይግባኝ አልኩኝ ባለው መሠረት ዛሬ ሐምሌ 21/2014 ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ የአቃቤ ህግ አቤቱታ ልክ ነው በማለት የተመስገንን ዋስትና ውድቅ አድሮጎ ተመስገን ክሱን እስር ቤት ሆኖ እንዲከታተል ወስኗል።

አወሳሰኑም በአብላጫ ድምጽ ( ከሦስቱ ዳኞች በሁለቱ ፤ በግራና በቀኝ ) ድጋፍ ፣ እንዲሁም የመሃል ዳኛ በልዩነት የተወሠነ መሆኑን ከወንዱም ከታሪኩ ደሳለኝ የተገኘው መረጃ ያሳያል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ችሎት በአዲስ አበባ ከተማ ከጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ አወጣጥ ጋር በተያያዘ በቁጥጥር ስር በዋሉ ግለሰቦች ላይ ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ተፈቀደ። ከኮንዶሚኒየም ቤቶች ዕጣ አወጣጥ ጋር በተያያዘ በቁጥጥር ስር የዋሉ ስምንት ግለሰቦች ፦ - የቴክኒክ ሙያ ስልጠና አይሲቲ ቢሮ ም/ቢሮ ኃላፊ አቶ አብርሐም ሰርሞሌ - የቤቶች ልማት ዳታ ቤዝ ቡድን መሪ አቶ ስመኘው አባተ - የሶፍትዌር ባለሙያዎች ፦ • ሀብታሙ…
#ችሎት #Update

ከጋራ መኖሪያ ቤቶች ጋር በተያያዘ ከሁለት ሳምንት በፊት በቁጥጥር ስር የዋሉ ስምንት ግለሰቦች ላይ በድጋሚ ለፖሊስ 14 የምርመራ ቀናት ተሰጠ።

ለፖሊስ የምርመራ ጊዜውን የሰጠው ዛሬ አርብ ሐምሌ 22/2014 የዋለው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት ነው።

የምርመራ ጊዜ የተፈቀደባቸው ተጠርጣሪዎቹ የአዲስ አበባ ከተማ የቴክኒክ ሙያ ስልጠና እና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ እና የቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ ሰራተኞች የነበሩ ናቸው።

ከተጠርጣሪዎቹ ውስጥ የአዲስ አበባ የቴክኒክ ሙያ ስልጠና እና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ምከትል ኃላፊ አቶ አብርሃም ሰርሞሎ ይገኙበታል።

የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት በዛሬው ውሎው " ከፖሊስ የምርመራ መዝገብ በርካታ ስራዎች መሰራታቸውን ተገንዝበናል " ብሏል።

" የወንጀሉ ውስብስብነት ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ለመስጠት ምክንያታዊ ነው " ያለው የጊዜ ቀጠሮ ችሎቱ፤ በዚህም መሰረት 14 ተጨማሪ የምርመራ ቀናት ለመርማሪ ፖሊስ መፈቀዱን ማስታወቁን ኢትዮጵያ ኢንሳይደር ዘግቧል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ችሎት #Update ከጋራ መኖሪያ ቤቶች ጋር በተያያዘ ከሁለት ሳምንት በፊት በቁጥጥር ስር የዋሉ ስምንት ግለሰቦች ላይ በድጋሚ ለፖሊስ 14 የምርመራ ቀናት ተሰጠ። ለፖሊስ የምርመራ ጊዜውን የሰጠው ዛሬ አርብ ሐምሌ 22/2014 የዋለው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት ነው። የምርመራ ጊዜ የተፈቀደባቸው ተጠርጣሪዎቹ የአዲስ አበባ ከተማ የቴክኒክ ሙያ ስልጠና እና ቴክኖሎጂ…
#ችሎት

የቀድሞው የአ/አ ከተማ የቴክኒክ እና ሙያ ስልጠና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ሙሉቀን ሀፍቱ ዛሬ ሰኞ ለ2ኛ ጊዜ በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ 1ኛ ጊዜ ቀጠሮ ችሎት ቀርበው ጉዳያቸው ታይቷል።

የፌደራል ፖሊስ መርማሪ በሀምሌ 11 በነበረ ቀጠሮ ለተጨማሪ ምርመራ በተሰጠው 14 ቀን ጊዜ ውስጥ የሰራውን የምርመራ ውጤት ለችሎቱ አብራርቷል።

ለተጨማሪ ምርመራ ስራ የ14 ቀን የምርመራ ጊዜ ጠይቆ ተፈቅዶለታል።

https://telegra.ph/Dr-Muluken-Haftu-08-01

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ችሎት

• ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ለነሐሴ 19/2014 ተቀጥሯል።

• የክስ መቃወሚያው ውድቅ ተደርጓል።

ዛሬ ማክሰኞ ጠዋት ሐምሌ 26 ቀን 2014 ዓ/ም የፌደራል ከፍተኛው ፍርድ ቤት 1ኛ ፀረ ሽብርና የህገ መንግስት ጉዳዮች ችሎት አቃቤ ህግ ባቀረበው ክስ ላይ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ካቀረበው መቃወሚያ ጋር አገናዝቦ ፍርድ ቤቱ ብይን ሰጥቷል።

ፍርድ ቤቱ ጉዳዩ በመገናኛ ብዙሃን አዋጅ መሠረት የሚታይ ቢሆንም ይርጋ እንዴት መቆጠር አለበት የሚለው ጉዳይን በወንጀል ህጉ መሠረት ስናየው ክሱ በይርጋ ቀሪ የሚሆን አይደለም ብሎ የጋዜጠኛ ተመስገንን መቃወሚያ ውድቅ አድርጓል።

ክሱን ከቀረበው ማስረጃ አንፃር መርምሮ እንዲከላከል ወይም በነፃ ለመልቀቅ ለነሐሴ 19 ቀን 2014 ዓ.ም ቀጠሮ ሰጥቷል።

ፍርድ ቤቱ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝን ከ24 ቀን በኋላ እንዲቀርብ እንደቀጠረ የጋዜጠኛ ተመስገን ወንድም ታሪኩ ደሳለኝ አሳውቋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ችሎት #Update ከጋራ መኖሪያ ቤቶች ጋር በተያያዘ ከሁለት ሳምንት በፊት በቁጥጥር ስር የዋሉ ስምንት ግለሰቦች ላይ በድጋሚ ለፖሊስ 14 የምርመራ ቀናት ተሰጠ። ለፖሊስ የምርመራ ጊዜውን የሰጠው ዛሬ አርብ ሐምሌ 22/2014 የዋለው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት ነው። የምርመራ ጊዜ የተፈቀደባቸው ተጠርጣሪዎቹ የአዲስ አበባ ከተማ የቴክኒክ ሙያ ስልጠና እና ቴክኖሎጂ…
#ችሎት

ከኮንዶሚኒዬም ዕጣ ማጭበርበር ወንጀል ጋር ተያይዞ በባንክ ሂሳባቸው በሚሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ ያንቀሳቀሱ ተጠርጣሪ ባለሙያዎች መኖራቸውን ፖሊስ ገለጸ።

ፖሊስ ይህን የገለፀው ተጠርጣሪዎቹን ዛሬ ለ3ኛ ጊዜ በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት ባቀረበበት ወቅት ነው።

በጋራ መኖሪያ ቤት ዕጣ (ኮንዶሚኒዬም) ዕጣ ከህግ ውጪ ግለሰቦች እንዲካተቱ አድርገዋል ተብለው ከተጠረጠሩ ከ8 የሶፍትዌር ባለሙያዎች መካከል በባንክ ሂሳባቸው ውስጥ በሚሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ ያንቀሳቀሱ ተጠርጣሪዎች መኖራቸውን ፖሊስ ለፍ/ቤት ገልጿል።

ቤት ድረስ እየተኬደ በዕጣው የሚገባው ሰው ገንዘብ ይከፍል እንደነበርና ደላላ ተቋቁሞ ከባለሙያ ጋር እየተገናኙ በዕጣው እንዲካተቱ የተደረጉ ግለሰቦች ነበሩ ሲል ፖሊስ ለፍ/ ቤት አስረድቷል። 

በተጨማሪም ፖሊስ ሶፍትዌሩን ካለሙት ባለሙያዎች መካከል ሲስተሙ የማልማት ተግባር በተከናወነበት ጊዜያት ብቻ #በሚስቶቻቸው ሂሳብ ውስጥ በርካታ ሚሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ በሂሳባቸው ያቀሳቀሱ ተጠርጣሪዎችም እንደነበሩ ማስረጃ ማግኘቱን ጠቅሶ ለችሎት አስረድቷል።

(Credit : Journalist Tarik Adugna)

ያንብቡ :
https://telegra.ph/Condominium-08-12-2
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ችሎት

#ክርስቲና_መላኩ #ጊዮናዊት_መላኩ

የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ 2ኛ ጊዜ ቀጠሮ ችሎት ፤ የህጻን ግዮናዊት መላኩ እና ህጻን ክርስቲና መላኩን በአሰቃቂ ሁኔታ ህይወታቸው እንዲያልፍ አድርጋለች የተባለችው ተጠርጣሪ ላይ ፖሊስ ተጨማሪ ምርመራ እንዲያደርግ የ14 ቀን ጊዜ ሰጠ።

ተጠርጣሪ ህይወት መኮንን ሀይሉ በነሃሴ 26 ቀን 2014 ዓ/ም ከጠኋቱ 3:30 ላይ በለሚ ኩራ ክ/ከ አራብሳ ኮንዶሚኒዬም ተቀጥራ በምትሰራበት መኖሪያ ቤት ውስጥ ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ የህጻን ግዮናዊት መላኩ አፏን በማፈን በቢላ በማረድ ህይወቷ እንዲያልፍ ማድረጓን እና ህጻን ክርስቲና መላኩን ደግሞ አፏን በማፈን በማነቅ በአጠቃላይ በአሰቃቂ ሁኔታ ህይወታቸው እንዲያልፍ ማድረጓን ፖሊስ ለችሎቱ አስረድቷል።

በዚህ መልኩ ተጠርጣሪዋን በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እያደረገ መሆኑን የገለጸው ፖሊስ የሰው ማስረጃ ለማሰባሰብና የግድያ ወንጀል የተፈጸመበትን ትክክለኛ ምክንያት በማስረጃ ለማረጋገጥ እንዲሁም በተጠርጣሪዋ ዙሪያ ያሉ ግለሰቦች ላይ ማስረጃ ለማሰባሰብና በወንጀሉ ስፍራ የተገኘ ስለታማ ቢላን በፎረንሲክ ለማስመርመር በተጨማሪም የአስከሬን ምርመራ ውጤት ለማምጣት የ14 ቀን ጊዜ እንዲሰጠው ጠይቋል።

በተጠርጣሪዋ በኩል ምንም አስተያየት ያልቀረበም።

የምርመራ መነሻ መዝገብን የተመለከተው የጊዜ ቀጠሮ ችሎቱ ተጠርጣሪዋ ላይ ፖሊስ ተጨማሪ ምርመራ እንዲያደርግ የ14 ቀን ጊዜ ፈቅዷል።

ምንጭ ፦ ጋዜጠኛ ታሪክ አዱኛ

@tikvahethiopia
#ችሎት

ዶ/ር ሙሉቀን ሃፍቱን ጨምሮ 5 ገለሰቦች ነፃ ተባሉ።

የቀድሞው የአዲስ አበባ ከተማ የቴክኒክ ሙያና ስልጠና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ሙሉቀን ሀብቱን ጨምሮ፥ ከኮንዶሚኒዬም ዕጣ ማጭበርበር ጋር በተያያዘ " ከባድ የሙስና ወንጀል " ክስ የተመሰረተባቸው 5 ግለሰቦች በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ነጻ ተብለዋል።

በዚሁ መዝገብ ክስ ከቀረበባቸው ግለሰቦች መካከል አንድ ተከሳሽ በሌሉበት ጥፋተኛ ሲባሉ፥ ቀሪ አምስት ተከሳሾች ደግሞ የተከሰሱበት ድንጋጌ ተቀይሮ እንዲከላከሉ ፍርድ ቤቱ በይኗል።

ችሎቱ አምስት ተከሳሾችን በነጻ ያሰናበተው ፥ " ዐቃቤ ህግ ባቀረበው የሰው እና የሰነድ ማስረጃ፥ ወንጀሉን በበቂ ሁኔታ ባለማስረዳቱ "መሆኑን ገልጿል።

በነጻ ከተሰናበቱት ውስጥ የአዲስ አበባ ከተማ የቴክኒክ ሙያና ስልጠና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ምክትል ኃላፊ የነበሩት አቶ አብርሃም ሰርሞሎ እና የከተማይቱ የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ቢሮ የአይሲቲ ዳይሬክቶሬይትን ሲመሩ የነበሩት አቶ ኩምሳ ቶላ ይገኙበታል።

#ኢትዮጵያኢንሳይደር

@tikvahethiopia