TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ደቡብ ክልል‼️

በኢትዮጵያ ደቡብ ክልል የሚነሱ የክልል፣ የዞን እና የልዩ ወረዳ ጥያቄዎችን #ሳይንሳዊ በሆነ መልኩ #ለመመለስ የሚያስችል ጥናት ሊጀመር መሆኑ ተገለፀ።

ጥናቱ የሚጀመረውም የደቡብ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ባለፈው መስከረም ወር ባካሄደው 10ኛ ድርጅታዊ ጉባኤ እየተነሱ ያሉት ጥያቄዎች ሳይንሳዊ በሆነ መልኩ እንዲፈቱ ባስተላለፈው ውሳኔ መሰረት መሆኑ ነው የተገለፀው።

በዚህ መሰረትም ጥያቄዎችን ለመፍታት የሚያስችለውን ጥናት ለማካሄድ ከምሁራን፣ከወጣቶች እና ከመንግስት ሰራተኞች የተውጣጡ 20 አባላትን የያዘ ኮሚቴ መቋቋሙን የጥናት ቡድኑ የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ ዶክተር ያኒአ ሰይድ መክይ ተናግረዋል።

የጥናት ቡድኑ በዋናነትም እየተነሱ ያሉትን ጥያቄዎች ከክልሉ ህዝቦች ፍትሃዊ ተጠቃሚነት እና ዘላቂ ልማት አንፃር በመመርመር፥ ህዝቦቹ በጋራ በኖሩባቸው ጊዜያት ያተረፉትንና ያጡትን አሁን ካለው ነባራዊ ሁኔታ ጋር በማዛመድ የሚያጠና መሆኑ ተነግሯል።

በሚቀጥለው ሳምንት የሚጀምረው የጥናት ሂደት ከአምስት እስከ ስድስት  ወራት ባሉት ጊዜያት ውስጥ ተጠናቆ የክልሉ መንግስት ውሳኔ እንዲሰጥበት ይደረጋል ነው የተባለው ።

ጥናቱ እስኪጠናቀቅ እና ጥያቄዎች በሰለጠነ እና ሳይንሳዊ በሆነ መልኩ ምላሽ እስኪያገኙ ድረስም፥የክልሉ ህዝብ ሰላም እና አንድነቱን ጠብቆ እንዲቀጥል የጥናት ቡድኑ  የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ ጠይቀዋል።

ምንጭ፦ ፋና ብሮድካስቲንግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia