TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
Fake Page Alert‼️ #አልጀዚራ የአማርኛ ፌስቡክ ገፅ የለውም!

©enf
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የ9/11 የሽብር ጥቃት #USA!

ዘጠኝ አስራ አንድ ተብሎ በሚታወቀው የአሜሪካው #የሽብር ጥቃት አቀነባባሪነት የተጠረጠረው ግለሰብ ሳዑዲ አረብያን በተመለከተ ቃሉን ሊሰጥ እንደሆነ ተገለፀ። ከ18 ዓመታት በፊት በሁለቱ የአሜሪካ የንግድ ህንፃዎች ላይ የደረሰውን የሽብር ጥቃት አቀነባብሯል በሚል የሚጠረጠረው እና የአል ቃይዳ ቁልፍ ሰው እንደሆነ የሚነገርለት ካሊድ ሼክህ ሞሃመድ የዩናይትድ ስቴትስ ፍርድ ቤት የሞት ቅጣት የማይበይንበት ከሆነ በጉዳዩ ዙሪያ ቃሉን እንደሚሰጥ አስታውቋል፡፡

ተጠርጣሪው ይህንን አማራጭ ያቀረበው ባለፈው ሳምንት መጨረሻ አርብ ሲሆን በአሜሪካ ማንሃታን ወረዳ ፍርድ ቤት በጥቃቱ ጉዳት የደረሰባቸው ባለሀብቶች እና ግለሰቦች ጠበቆች ባዘጋጁት ደብዳቤ ላይም ፍቃደኝነቱን በመሙላት ማረጋገጡ ነው የተገለፀው፡፡

ግለሰቡ በሳዑዲ አረብያ ላይ ሊመሰክር ቃል ይግባ እንጂ ሀገሪቱ በተደጋጋሚ ጊዜ ከጉዳዩ ጋር ግንኙነት እንደሌላት ስትገልፅ ቆይታለች። ዋሺንግተን ዲሲ የሚገኘው እና የሳዑዲ አረብያ መንግስት ጠበቃ ሚሼል ኬሎጅ ግን በጉዳዩ ላይ ሀሳብ ከመስጠት ተቆጥቧል፡፡ ግለሰቡ ጠበቆቹ ያቀረቡት ደብዳቤ ላይ ሀሳቡን እንዲያሳርፍ የተለያዩ የህግ ባለሙያዎች በታዛቢነት መሳተፋቸውም ተገልጿል፡፡

ካሊድ ሼክ ሞሃመድን ጨምሮ 3 ተጠርጣሪዎች የሞት ክሱ ተመስርቶባቸው ጥብቅ ቁጥጥር በሚደረግበት እስር ቤት እንደሚገኙ ጠበቆቹ ገልፀዋል፡፡

Via #አልጀዚራ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#COVID19

በቅርቡ ወደ ኢራን ማርካዚ ግዛት በገባው ኮሮና ቫይረስ ስምንት የሚሆኑ የሀገሪቱ ዜጎች ለህልፈት መዳረጋቸውን የሀገሪቱ ጤና ሚኒስቴር አስታውቋል። በቫይረሱ የተጠቁ ሰዎች ቁጥርም 43 መድረሱ ነው የተገለጸው።

ይህን ተከትሎም ሀገሪቱ ቫይረሱ በተከሰተባቸው ግዛቶች የሚገኙ ትምህርት ቤቶች እና የተለያዩ ባህላዊ ማዕከሎች እንዲዘጉ መወሰኗ ተሰምቷል።

ከዚህ ባለፈም የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ሃሰን ሩሃኒ የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት ብሄራዊ የመቆጣጠሪያ ማዕከል እንዲቋቋም ትዕዛዝ መስጠታቸው ተገልጿል።

የሚቋቋመው ማዕከልም በሀገሪቱ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከል የሚደረገውን ዘመቻ የሚያስተባብር ይሆናል።

#አልጀዚራ #ኤፍቢሲ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#COVID19

ሳዑዲ ዓረቢያ ወደ መካ የሚደረጉ ጉዞዎች ላይ እገዳ መጣሏን አስታውቃለች። የጉዞ እገዳው ሐይማኖታዊ እና መደበኛ ተጓዦችን የሚያካትት ሲሆን፥ የስርጭት አድማሱን እያሰፋ ካለው የኮሮና ቫይረስ ጋር የተያያዘ መሆኑንም ተሰምቷል።

ይህን ተከትሎም ወደ ሳዑዲ ለሐይማኖታዊ የፀሎት ስነ ስርአትም ይሁን ለጉብኝት የሚደረጉ ጉዞዎች መታገዳቸውን ገልጻለች። ከዚህ ባለፈም የኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎች ከተገኙባቸው ሃገራት የሚነሱ መንገደኞች ወደ ሳዑዲ እንዳይገቡም እገዳ ተጥሏል።

አመታዊው የሃጅ እና ዑምራ ጉዞ ከአምስት ወራት በኋላ ይካሄዳል፤ በአመታዊው ሃይማኖታዊ ስነ ስርአት ላይ በሚሊየኖች የሚቆጠሩ የእስልምና እምነት ተከታዮች ወደ መካ ያቀናሉ። የአሁኑ የጉዞ እገዳ እስከ ሃጅ ዑምራ ጉዞ ስለመቆየት አለመቆየቱ ግን የተባለ ነገር የለም።

#አልጀዚራ #ኤፍቢሲ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የዓለም አቀፍ ዜና አውታሮች ድረገፆች ተቋረጡ።

ዓለም አቀፍ የዜና አውታሮች የሆኑት የፋይናንሻል ታይምስ ፣ የኒው ዮርክ ታይምስ እና የብሉምበርግ ኒውስን ጨምሮ የሌሎችም የዜና አውታሮች ድረገፆች አገልግሎታቸው ተቋረጠ።

የCNN እና የፈረንሳይ ሌሞንዴ ድረገፆችም 4 ሰዓት አካባቢ የስህተት ምልክት ታይቶባቸዋል። አልጀዚራ ድረገፅም ተመሳሳይ ችግር ገጥሞት ነበር።

የብሪታኒያው ዘጋርዲያን በድረገፁና በአፕሊኬሽኑ ላይ ችግር ገጥሞት እንደነበረ ገልጿል ሌሎች የብሪታኒያ የዜና አውታሮች ድረገፆች ወዲያው መስራት አቁመው ነበር።

በርከት ባሉት ዓለም አቀፍ ዜና አውታር ድረገፆች ላይ ምን እንደተፈጠረ እና ለምን እንደተቋረጡ ለጊዜው አልታወቀም።

#አልጀዚራ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update #ፊንላንድ #ስውዲን #ሩስያ #NATO ➡️ የስዊድን ውጭ ጉዳይ ሚንስትር አን ሊንዴ ሀገራቸው የNATO አባል እንድትሆን ማመልከቻ መፈራረማቸው ተነግሯል። ሚኒስትሯ የፈረመት የአባልነት ጥያቄ ማማልከቻ ከፊንላንድ የNATO ማመልከቻ ጋር አብሮ ይቀርባል ሲሉ የሀገሪቱ ሚዲያዎች ዘግበዋል። ➡️ ዛሬ የፊንላንድ ፓርላማ የNATO ወታደራዊ ጥምረት አባል ለመሆን የቀረበውን ሀሳብ በ188 ድምጽ…
#Update

#ፊንላንድ #ስውዲን #ሩስያ #NATO

➡️ ፊንላንድ እና ስዊድን NATOን ለመቀላቀል በይፋ የማመልከቻ ደብዳቤያቸውን ለNATO አስገብተዋል።

➡️ የNATO ዋና ፀሃፊ ጄንስ ስቶልተንበርግ ፊንላንድ እና ስዊድን የዓለም ትልቁን ወታደራዊ ህብረት ለመቀላቀል በይፋ ጥያቄ ማቅረባቸውን አረጋግጠዋል። ዋና ፀሀፊው 2ቱ ሀገራት የNATO አባል ለመሆን ያቀረቡትን ጥያቄ በከፍተኛ ደስታ መቀበላቸውን ገልፀዋል።

➡️ ፊንላንድ እና ስዊድን የNATO ጥምረት አባል ለመሆን ያቀረቡት ማመልከቻ በ30ዎቹ አባል አገራት የሚታይ ሲሆን ሂደቱ ሁለት ሳምንታትን ሊፈጅ እንደሚችል ተነግሯል። ቱርክ ሀገራቱን የአሸባሪዎች ማረፊያ ናቸው በማለት NATOን ለመቀላቀል የሚያደርጉትን እንቅስቃሴ ደጋግማ መቃወሟ ይታወቃል።

➡️ ነገ ሀሙስ የአሜሪካው ፕሬዜዳንት ጆ ባይደን የስውዲን ጠቅላይ ሚኒስትር እና የፊንላንድ ፕሬዜዳንት በዋይትሀውስ ተቀብለው ያነጋግራሉ፤ የ2ቱ ሀገራት መሪዎች NATOን ለመቀለቀል እያደረጉት ስለለው ሂደት ከባይደን ጋር ይወያያሉ ተብሏል። አሜሪካ ሀገረቱ የNATO አባል እንዲሆኑ ከፍተኛ ድጋፍን እየሰጠች ከምትገኝ ሀገር አንዷ ናት።

➡️ NATOን መቀላቀል በማሰቧ ከዩክሬን ጋር ጦርነት ውስጥ የምትገኘው ሩስያ አሁንም ወታደራዊ ኦፕሬሽኖችን እያካሄደች ነው። ሩስያ
በዶኔትስክ እና ሉሃንስክ የምድር ላይ ወታደራዊ ኦፕሬሽኖች መቀጠሏ ተነግሯል።

➡️ ሩስያ፤ ፊንላንድና ስዊድን NATO የሚቀላቀሉ ከሆነ አፀፋዊ እርምጃ እንደምትወስድ እየዛተች ነው ይህን ተከትሎ ፊንላንዳውያን በገፍ ወታደራዊ ስልጠናዎችን እየወሰዱ ነው። እንደ ዩክሬን ልንወረር እንችላል በሚል የሃገሪቱን ጦር በመቀላቀል በፈቃደኝነት ወታደራዊ ስልጠናዎች እየወሰዱ ይገኛሉ።

#አልጀዚራ #አፒ #አልአይን #ቲአርቲ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

➡️ ፈረንሳይ ፣ ጣልያን እና ስፔን 85 የሩሲያ ዲፕሎማቶችን ማባረራቸውን የሩሲያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል። ዲፕሎማቶቹ ሀገራቱን ለቀው እንዲወጡ የታዘዙት በስለላ ስራ ላይ ተሰማርተዋል በሚል ተከሰው ሲሆን፤ ሩስያ ክሱ ሀሰት ነው ብላለች፤ የዩክሬን ጦርነት ከጀምረ ጊዜ አንስቶ 300 የሩሲያ ዲፕሎማቶች ከተለያዩ ሀገራት ተባረዋል።

➡️ ሩስያ ዛሬ የስፔን እና የፈረንሳይ ዲፕሎማቶችን አባረረች። እስካሁን 27 የስፔን፣ 34 የፈረንሳይ ያባረረች ሲሆን 24 የጣልያን ዲፕሎማቶችን ልታባርር እንደሆነ ተሰምቷል።

➡️ የቱርክ ፕሬዜዳንት ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን የNATO አባላት ሀገራቸው ፊንላንድ እና ስዊድን ወደ ህብረቱ አባልነት እንዳይገቡ ያደረባትን ስጋት እንዲያከብሩ ጠየቀዋል። ኤርዶጋን ፊንላንድ እና ስውዲን የNATO አባል ሀገር እንዲሆኑ ሀገራቸው ድጋፏን እንደማትሰጥ በተደጋጋሚ ገልፀዋል።

➡️ የዩክሬን ጦርነትን ለማስቆም በዩክሬን እና ሩሲያ መካከል ሲደረግ የነበረው ድርድር ቆሟል። ሁለቱም ወገኖች ለድርድሩ መደናቀፍ አንዱ ሌላውን እየወነጀለ ነው።

➡️ የአሜሪካው ፕሬዜዳንት ጆ ባይደን የፊንላንድ እና ስዊድን ለNATO አባልነት ያቀረሹትን ታሪካዊ ያሉትን ማመልከቻ ባደስታ እንደሚቀበሉትና አጥብቀው እንደሚደግፉ አስታውቀዋል። ፕሬዜዳንቱ ዛሬ ባወጡት ተግለጫ ከUS ኮንግረስ እና ከNATO አጋሮች ጋር በመሆን በፍጥነት ፊንላንድ እና ስዊድን ወደ ጠንካራው የመከላከያ ህብረት (NATO) ለማምጣት እሰራለሁ ብለዋል።

➡️ ፊንላንድ NATO ለመቀላቀል ባሳለፈችው ውሳኔ ላይ የሩሲያ ምላሽ ድንገተኛ ቢሆንም እርምጃዎቹ ግን ወታደራዊ ይሆናሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ተነግሯል።

#አልጀዚራ #ኤኤፍፒ #ዘኪየቭ_ኢንዲፔንደንት #አልአይን

@tikvahethiopia
ከዓለም ዙሪያ #1 ፦

➡️ #ሴኔጋል ፦ በምዕራብ ሴኔጋል ፤ ቲቫዋን በምትሰኝ ከተማ በአንድ ሆስፒታል ውስጥ በደረሰ ቃጠሎ 11 አዲስ የተወለዱ ህጻናት መሞታቸውን ፕሬዝዳንት ማኪ ሳል ተናግረዋል።

➡️ #አፍጋኒስታን ፦ በአፍጋኒስታን ዋና ከተማ ካቡል እና ሰሜናዊ ከተማ ማዛር ኢ ሻሪፍ ከተከታታይ በደረሱ ፍንዳታዎች ቢያንስ 14 ሰዎች መገደላቸው ተነግሯል። ዳኢሽ ለጥቃቱ ኃላፊነት መውሰዱን ሮይተርስ ዘግቧል።

➡️ #ሩስያ ፦ የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን በዩክሬን ላይ ለሚያካሂዱት ኦፕሬሽን ወታደሮቻቸውን ወደ ሀገሪቱ ከላኩ በኃላ ለመጀመሪያ ጊዜ ዩክሬን ውስጥ በወታደራዊ ዘመቻው ከቆሰሉ ወታደሮች ጋር ተገናኝተዋል። በሌላ የሩስያ ጉዳይ ፤ ሀገሪቱ ያለባትን የውጭ ሀገራት እዳ በራሷ መገበያያ ገንዘብ “ሩብል” ለመክፈል ወስናለች ፤ እዚ ውሳኔ ላይ የደረሰችው የአሜሪካ ግምጃ ቤት ከቀናት በፊት በሩሲያ በአሜሪካ ባንኮች በኩል የምትፈጽመውን የውጭ ዕዳ ክፍያ ፍቃድ መሰረዙን ተከትሎ ነው።

➡️ #ዩክሬን ፦ ወደ ሰቨሮዶንስክ ከተማ የሚወስደውን አውራ ጎዳና ለመቆጣጠር በሩስያ እና ዩክሬን ኃያሎች መካከል ከፍተኛ ጦርነት እየተደረገ ነው። ሩሲያ ይህን ከተማ ለመቆጣጠር ተቃርቢያለሁ ብትልም አንድ ከፍተኛ የዩክሬን ባለሥልጣን ነገሩን አስተባብለዋል። ይህ ጎዳና ዩክሬን የምትቆጣጠራቸውን ከተሞች ሩሲያ ከያዘቻቸው ከተሞች ጋር የሚያገናኝ ከፍ ያለ ወታደራዊ ዋጋ ያለው ነው።

➡️ #ጋምቢያ ፦ የጋምቢያ መንግስት የቀድሞ ፕሬዝዳንት ያህያ ጃሜህ ከ20 አመታት በላይ በዘለቀው የስልጣን ዘመናቸው ተፈጽመዋል በተባሉ ግድያ፣ አስገድዶ መድፈር፣ ማሰቃየት እና ሌሎች ወንጀሎች ላይ ክስ እንደሚመሰርት አስታውቋል።

#አልጀዚራ #ቲአርቲወርልድ #ስፑትኪን #ሮይተርስ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update በቱርክ እና ሶሪያ መሬት መንቀጥቀጥ የሞቱ ሰዎች ከ7,300 አልፈዋል። በቱርክ እና ሶሪያ በተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ አሁን ላይ የሞቱ ሰዎች ቁጥር ከ7,300 ማለፉን ባለስልጣናት አሳውቀዋል። ሰዎችን ከፍርስራሽ ውስጥ ፈልጎ የማውጣቱ እንዱሁም የነፍስ አድን ስራው አሁንም መቀጠሉ የታወቀ ሲሆን የሟቾች ቁጥር ከዚህም ሊጨምር እንደሚችል ተነግሯል። @tikvahethiopia
#Update

በቱርክ እና ሶሪያ የሟቾች ቁጥር 11,000 ደረሰ።

ሰኞ በቱርክና ሶሪያ በተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ ሳቢያ ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር 11,000 መድረሱን አልጀዚራ ዘግቧል።

ከ11 ሺህ ሟቾች መካከል በትንሹ ከቱርክ 8,574 ሲሆኑ ከሶሪያ ደግሞ 2,530 ሆነው መመዝገባቸው ተመላክቷል።

ሰዎችን ከህንፃ ፍርስራሾች ውስጥ ፈልጎ የማውጣቱ እንዱሁም የነፍስ አድን ስራው አሁንም መቀጠሉ የታወቀ ሲሆን የሟቾች ቁጥር ከዚህም ሊጨምር እንደሚችል ተነግሯል።

#አልጀዚራ

@tikvahethiopia