TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ከዘር ማጥፋት እልቂት ለማምለጥ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ የተሸሸጉ 2 ሺህ ቱትሲዎች እንዲገደሉ ትዕዛዝ በመስጠት የተጠረጠረው ግለሰብ ተያዘ።

እ.አ.አ በ1994 በሩዋንዳ በነበረው የዘር ማጥፋት እልቂት፣ ከጥቃት ለማምለጥ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ የተሸሸጉ ሁለት ሺሕ #ቱትሲዎች እንዲገደሉ ትዕዛዝ አስተላልፏል በሚል የተጠረጠረው ግለሰብ ደቡብ አፍሪካ ውስጥ መያዙን የሩዋንዳውን የዘር ማጥፋት የሚከታተለው፣ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የጦር ወንጀል ችሎት አስታውቋል።

የቀድሞው የፖሊስ አባል፣ ፉልጌንሴ ካይሼማ፣ ፍ/ቤቱ በይፋ ክሥ ከመሠረተበት ካለፉት 22 ዓመታት ጀምሮ በሽሽት ላይ ነበር።

በተመድ የተቋቋመው ችሎት፣ ሥራውን ለሩዋንዳ በማስረከቡ፣ ካይሼማ፥ ለሩዋንዳ ተላልፎ እንደሚሰጥ የሮይተርስ ዘገባ አመልክቷል።

የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ ካይሼማ ያለበትን ለሚጠቁም፣ የአምስት ሚሊዮን ዶላር ጉርሻ እንደሚሰጥ አስታውቆ ነበር።

ሌላው የዘር ማጥፋቱ ጠንሳሽ የተባለው ፌሊሲን ካቡጋ፣ ከ26 ዓመታት ሽሽት በኋላ ከሦስት ዓመት በፊት በፈረንሳይ ውስጥ መያዙ ይታወቃል።

እ.አ.አ በ1994 በሩዋንዳ፣ በአክራሪ ሁቱዎች በተፈጸመ የዘር ማጥፋት፣ 800ሺሕ የሚሆኑ ቱትሲዎች መገደላቸው ይታወሳል።

#ቪኦኤ #ሩዋንዳ #Genocide

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
በሩዋንዳው #ጄኖሳይድ ወቅት የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ምን አደረገ ? ከ800 ሺህ እስከ 1 ሚሊዮን የሚደርሱ ሰዎች ባለቁበት የሩዋንዳ የዘር ጭፍጨፋ ወቅት የዓለም መሪዎች ምንም እንኳን ስለ ዘር ጭፍጨፋው (ጄኖሳይድ) ቢያውቁም ጣልቃ አልገቡም ነበር። ለረጅም ጊዜ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ' ጄኖሳይድ ' የሚለውን ቃል ከመጠቀም ተቆጥቦ ነበር ፤ ይህም #በአሜሪካ ጫና እንደሆነ ይነገራል። አሜሪካም…
ሚዲያ የሩዋንዳውን የዘር ጭፍጨፋ (ጄኖሳይድ) እንዴት አቀጣጠለ ?

በ100 ቀናት ከ800,000 እስከ 1,000,000 ቱትሲዎችና ለዘብተኛ የሚባሉ ሁቱዎች ባለቁበት የሩዋንዳው የዘር ጭፍጨፋ/ጄኖሳይድ ሚዲያዎች ከፍተኛ ድርሻ ነበራቸው።

እንዴት ?

- ራዲዮ-ቴሌቭዥን ሊብሬስ ዴስ ሚልስ ኮሊንስ (RTML) እንዲሁም መንግታዊው ' ሬድዮ ሩዋንዳ ' በቱትሲዎች ላይ በመላ ሀገሪቱ ጥላቻ እንዲፈጠርና የሩዋንዳ ጄኖሳይድ እንዲፈፀም ዋና አቀጣጣይ ነበሩ።

- RTML ሚዲያ በወቅቱ በብዙ ወጣቶች ዘንድ ተደማጭነት የነበረው ነው። ጣቢያው በወጣቶች ዘንድ እጅግ የሚወደዱ ሙዚቃዎችን እያስተላለፈ #በመሃል ያቋርጠውና ቱትሲዎችን በመጥቀስ " እነዚያ ሰዎች እጅግ ቆሻሻ ቡድን ናቸው " የሚሉ አዋራጅና ቀስቃሽ መልዕክቶችን ያስተላልፋል። በስርጭቶቹ ውስጥ "#በረሮዎች" እና "#እባቦች" የሚሉ ቃላት በተደጋጋሚ ጥቅም ላይ ያውላል።

- RTML ሚያዚያ 6 /1994 ፕሬዜዳንት ጁቬናል ሃብያሪማና የነበሩበት አውሮፕላን ተመቶ ሲወድቅ በቅድሚያ ድርጊቱን የፈፀመው RPF ነው ብሎ የፈረጀ እና ንፁሃንን ለጭፍጨፋ ያመቻቸ ሚዲያ ነው።

- በጭፍጨፋው ወቅት ጨፍጫፊዎቹ በአንድ እጃቸው ሬድዮ በአንድ እጃቸው ደግሞ #ቆንጨራ ይዘው ነበር ሲንቀሳቀሱ የነበሩት። በዚህም ወቅት RTML እና ሬድዮ ሩዋንዳ ቱትሲዎች እና እነሱን የሚሸሽጉ ሁቱዎች እንዲገደሉ ያሉበትን አድራሻ ጭምር ሲገልጹ ነበር።

- ሚዲያዎቹ ጎረቤት በጎረቤቱ ላይ እንዲነሳ እና ቱትሲ የሚባሉትን በጠቅላላ እንዲያጠፏቸው ሲሰብኩ ነበር። በዚህም ብዙዎቹ ሁቱዎች የገዛ ጎረቤታቸውን አንዳንዶቹ ከቱትሲ ጋር የተዛመዱ #ዘመዶቻቸውን ጭምር ጨፍጭፈዋል።

- ሚዲያዎቹ የተለያዩ አነሳሽ ቃላቶች በመጠቀም ቱትሲዎች #እንዲጠሉ#እንዲገደሉ ሰዎችን ሲያበረታቱ ነበር። ትንንሽ ልጆች ፣ ታዳጊዎች ሳይቀሩ በራሳቸው ወገን #ጥላቻ እንዲሞሉ አድርገዋል።

- የሁቱ ሚዲያዎች በቀደመው ጊዜ #ቱትሲዎች ሀገሪቱ ውስጥ ትልቅ ስፍራ ይዘው በነበረበት ወቅት " በደል ፈፅመዋል " በማለትና " የሀገሪቱ ችግሮች እነሱናቸው እስከመጨረሻ ካልጠፉ በቀር ምንም መፍትሄ የለም " በማለት ሁቱዎችን ይቀሰቅሱ ነበር።

በነገራችን ላይ ከጭፍጨፋው ጅማሮ #በፊትም የሀገሪቱ መንግሥት ሚዲያዎችን በመጠቀም ሰፊ የሆነ የጥላቻ ፕሮፖጋዳንዳ ሲሰራ ቆይቷል።

በተለይ ቱትሲዎችን ከRPF ኃይል ጋር በማገናኘት ሁቱዎች ውስጣቸው በከፍተኛ ጥላቻ ታውሮ የገዛ ወገናቸውን እንዲጨፈጭፉ ሰርቷል።

አጠቃላይ በሰው ልጅ ታሪክ ውስጥ የታየ እጅግ  አስከፊው የዘር ጭፍጨፋ የአንድ ሌሊት ውጤት አልነበረም፤ በሂደት የመጣ እንጂ።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
Rwandan genocide
Apr 7, 1994 – Jul 15, 1994

@tikvahethiopia