TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የክልል እና የዞን ጥያቄዎችን በተመለከተ‼️

በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች የሚነሱ የዞንና የክልል ጥያቄዎችን በጥናትና ህግ በሚፈቅደው መንገድ #ለመመለስ እንደሚሰራ ጠቅላይ ሚኒስትር #አብይ_አህመድ ተናገሩ።

በአሁኑ ወቅት በርካታ የማንነት ጥያቄዎች እየቀረቡ መሆኑን የገለፁት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጥያቄዎችን በህጋዊ መንገድ ማቅረብና መደመጥ መቻል በራሱ የዴሞክራሲ መብት አካል መሆኑን አስገንዝበዋል።

ይሁን እንጂ ዞን ወይም ክልል የሚለው ጥያቄ ከመመለሱ በፊት የጥያቄዎቹ ዋና ዓላማ፤ እንዲሁም ጥቅምና ጉዳቱን መታየት አለበት ብለዋል።

የአንድ አካባቢ የዞን ወይም የክልል ጥያቄ ሲመለስ በአካባቢው ካሉ ጎረቤት ክልሎች ጋር በሰላም፣ በኢኮኖሚና በሌሎች ጉዳዮች ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ እንደማይኖረው መረጋገጥም ይኖርበታል ብለዋል።

ይሁን እንጂ የክልልና የዞን ጥያቄዎች በህጋዊ መንገድ መቅረብ እንዳለባቸው፤ የጥያቄው አግባብነት እስከሚታይ #መታገስ እንጂ በህገ-ወጥ መንገድ ይመለሳል ብሎ መንቀሳቀስ #አዋጭነት_የለውም ብለዋል።

መንግስት ይህንኑ ጉዳይ የሚከታተል ኮሚሽን አዋቅሮ እየሰራ መሆኑንና በቀጣይ ጥናት ላይ ተመስርቶ በህጋዊ መንገድ ለመፍታት የምናየው ይሆናል ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ።

“የሚወሰነው ውሳኔም የሚያዋድደን፣ አንድ የሚያደርገን እንጂ የሚያጣላን መሆን የለበትም” ሲሉም ተናግረዋል።

“ኢትዮጵያ ውስጥ የትኛውም ጫፍ ከሌላው ጋር ተሳስሮና ተደጋግፎ መሄድ ካልቻለ #መቀጠል አይችልም፣ ህይወታችን በራሱ #ተደጋግፈን እንድንቀጥል ያደርገናል” ሲሉም ነው መልዕክት ያስተላለፉት።

ምንጭ፦ ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ ምን አሉ ? የተ/ም/ቤት አባል ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ ፦ " ጠ/ሚ ዐቢይ ወደ መንበረ ስልጣን ከወጡበት ከመጋቢት 2010 ዓ/ም ጀምሮ እየተወሳሰቡ የሄዱት የሀገራችን ፖለቲካዊ ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ችግሮች አሁን ላይ ወደ ሁለንተናዊ ቀውስ መሸጋገራቸውን ማሸፋፈን ወደማይቻልበት ደረጃ ደርሰዋል። ብልፅግና መራሹ መንግስትዎ ፦ - የኢትዮጵያ ህዝብ በሰላም ወጥቶ የሚገባበት ፣ - ነጋዴው…
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለዶ/ር ደሳለኝ ምን ምላሽ ሰጡ ?

ኢትዮጵያ ቀውስ ውስጥ መሆኗና ለዚህም ተጠያቂው ገዢው ብልፅግና ፓርቲና የጠቅላይ ሚኒስትሩ የወደቀ አመራር በመሆኑ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከስልጣናቸውን #እንዲለቁና ስልጣናቸውን ለሚቋቋም ጊዜያዊ ሲቪል አስተዳደር እንዲያስረክቡ ፤ ፓርላማውም ተበትኖ ለምርጫ መንገድ እንዲጠርግ በሚል በዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ ለተጠየቀው ጥያቄ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ምላሽ ሰጥተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በፓርቲያቸውና መንግሥታቸው ላይ ከታቃዋሚ ፓርቲ በኩል የቀረበውን ክስ በተመለከተ " እንዲህ ያለው ንግግር ለዛሬ #ፌስቡክ፣ ለዛሬ #ዩትዩብ ጥሩ ነው ፤ አቶ እንትና እንትና እንዲህ አደረጉ ለሚለው ለፌስቡክ ፍጆታ ጥሩ ነው ለትውልድ እና ሀገር ግን አይጠቅምም " ብለዋል።

" ቆም ብለን እኛ ማናየውን በማሳየት ለኢትዮጵያ ህዝብ የሚጠቅመውን ሃሳብ ብናቀርብ ጠቃሚ ነው " ሲሉ ተደምጠዋል።

" በኢኮኖሚ፣ በሰላም እና በአንዳንድ ጉዳዮች የቀረቡትን የምንወስዳቸውና የምንሰራባቸው እንደሆነ ምንም ጥያቄ የለውም " ያሉት ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ " በጥቅሉ ኢትዮጵያ ጨለማ ውስጥ ናት ከተባለ ግን ከሰሀራ በታች ካሉ ሀገራት በኢኮኖሚ 3ኛ ናት፣ ከምስራቅ አፍሪካ አንደኛ ናት ፣ ትላልቅ ተቋማትን እየገነባች ያለች ሀገርናት የሚል መልስ ሆኖ ያልቃል " ሲሉ ተናግረዋል።

ምርጫን በተመለከተ ፤ " ምርጫ ይካሄድ የሚለውን ሃሳብ በጣም አደንቃለሁ ፤ ብዙ ጊዜ የተቃዋሚዎች ችግር ምርጫ አይፈልጉም ዝም ብላችሁ ልቀቁና እኛ እንያዝ ነው የሚሉት ፤ አሁን ምርጫ ይደረግ የሚለው በጣም ጠቃሚ ነው ግን ሶስት ዓመት #መታገስ አለብን " ብለዋል።

" በየሳምንቱ ምርጫ ስለማይደረግ ፤ ሶስት አመት ታግሰን ያለንን ሃሳብ ይዘን ቀርበን እኛም ይዘን ቀርበን የኢትዮጵያ ህዝብ የሚፈርደውን ፍርድ በፀጋ መቀበል ነው ፤ የዛሬ ሁለት ዓመት የፈረደውን ፍርድ አልተቀበልኩምና አሁን ፓርላማው ፈርሶ ምርጫ ካልተካሄደ አሁንም ፈርሶ ቢካሄድና ቢመረጥ ካልተመረጥን ይቀጥላል ጉዳዩ በየሁለት አመቱ ምርጫ ለማካሄድ አቅም ስለሚያንሰን በተቀመጠው መንገድ በ5 ዓመት እናደርጋለን " ብለዋል።

" ምርጫ ሲደረግ ያሉ ሀሳቦች ለህዝብ ቀርበው እኛ ህዝቡ በሚፈልገው ልክ ካላገለገልንና ካልጠቀምን ህዝቡ በምርጫው ሲቀጣን እጅ ስመን፣ ባንስምም እጅ ነስተን እናስረክባለን ፤ እስከዛ መታገስ ጥሩ ነው ፤ ፍርዱን ለህዝብ እንተወው " ሲሉ መልሰዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሀገሪቱ ከገባችበት ቀውስ ጋር በተያያዘ ስልጣናቸውን እንዲለቁ በአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ህዝብ በመረጣቸው የምክር ቤት አባላት ሲጠየቁ የዛሬው ሁለተኛ ነው።

የምክር ቤት አባሉ አቶ ክርስቲያን ታደለ ከወራት በፊት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስልጣን በመልቀቅ " ላለው ችግር የመፍትሄው አካል ለመሆን አላሰቡም ወይ ? በሰብዓዊነት ላይ በተፈፀሙ እንዲሁም በማንነት ተኮር የዘር ማጥፋት ፣ የዘር ማፅዳት እና የማንነት ማሳሳት ወንጀሎች ተጠያቂ ለመሆን ምን ያህል ዝግጁ ኖት ? " የሚል ጥያቄ አቅርበው የነበረ።

በወቅቱ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ፤ ኃላፊነት መውሰድ ካለብን በጋራ ቢሆን መልካም ስለሆነ " ስልጣን ብንለቅ " ነው የሚባለው ምክንያቱም መንግስት ማለት አስፈፃሚ ብቻ አይደለም የሚል ምላሽ ሰጥተዋቸው ነበር።

የዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ ንግግር : https://t.iss.one/tikvahethiopia/79527

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia