TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.7K photos
1.49K videos
211 files
4.06K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ትግራይ

በትግራይ፣ መቐለ የሚገኘው ፍሬምናጦስ የአረጋውያን ፣ የአእምሮ ህሙማንና የህፃናት እንክብካቤ ማእከል ከ30 ሚሊዮን ብር በላይ ሚገመት የገንዘብ የቁሳቁስ ድጋፍ ቃል ተገባለት።

ይህን የገንዘብና የአይነት ድጋፍ ቃል የተገባለት ትላንት " #አለሁ_ለፍሬምናጦስ " በሚል በመቐለ ከተማ በተካሄደ ዓለም አቀፍ የሆነ የገቢ ማሳባሰብያ የቴሌቶን ፕሮግራም ላይ ነው።

መስፍን ኢንዱስትሪያል ኢንጅነሪንግ የተባለ የትእምት ኩባንያ በምግባረ ሰናይ ደርጅቱ ላክ በባለፈው ሚያዝያ ወር በተነሳ የእሳት ቃጠሎ የወደመውን አዳራሽ ሙሉ ለሙሉ መልሶ እንደሚገነባው ቃል ገብቷል።

ከዚህ በተጨማሪም የ20 ሚሊዮን ብር ግምት ያላቸው የጭነት መኪና፣ አምቡላንስ የምግባረ ሰናይ ድርጅቱ ለሚያሰገነባው ግዙፍ የእንክብካቤ ማእከል የሚውሉ ማሽነሪዎች በአገር ውስጥና በውጭ በጎ ለጋሾች ተበርክቷል።

የምግባረ ሰናይ ድርጅቱ መስራችና ስራ አስኪያጅ አባ ገብረ መድህን በርሀ ፥ " ጦርነት በፈጠረው ጉዳት ምክንያት #የአእምሮ_ህሙማን_ቁጥር በመጨመር ላይ በመሆኑ ድርጅቱ ለሚሰጠው የነፃ እንክብካቤ አገልግሎት የህዝቡ እገዛ ይሻል " ብለዋል።

ፍሬምናጦስ የአረጋውያን የአእምሮ ህሙማን የህፃናት እንክብካቤ ማእከል በአሁኑ ወቅት 29 አረጋውያን ፣ 206 የአእምሮ ህሙማን እና 40 አሳዳጊ የሌላቸውን ህፃናት ጨምሮ በአጠቃላይ #ከ275_በላይ ለሆኑ ወገኖች የተሟላ የመጠለያ አገልግሎት በመስጠትና በመንከባከብ ላይ ይገኛል። 

በትግራይ በነበረው አስከፊ የሆነ ጦርነት ምክንያት ግን ወደ ማዕከሉ መግባት የሚፈልጉ ወገኖች ቁጥር በእጅጉ ጨምሯል።

ለማሳያ ባለፉት ወራት ብቻ 1500 የእእምሮ ህሙማን ወደ ማእከሉ ለመግባት መመዝገባቸው ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከምግባረ ሰናይ ድርጅቱ ያገኘው መረጃ ያመለክታል። 

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia