TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.4K photos
1.47K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ህዳር 30 የሚዘጉ መንገዶች‼️

በአዲስ አበባ ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎችን ለመከላከል ከትራፊክ ፍሰት ነፃ የሆነ ቀን ለማክበር #ሚዘጉት_መንገዶች ይፋ ሆኑ።

ለትራፊክ ዝግ የሚሆኑ ሁለት መንገዶች የተለዩ ሲሆን አንደኛው ከጊዮርጊስ አደባባይ- በቸርችል ጎዳና-ኢትዮ ኩባ ወዳጅነት ፓርክ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ከጊዮርጊስ አደባባይ-በ6ኪሎ-በ5ኪሎ አድርጎ መድረሻውን ጊዮርጊስ አደባባይ ያደርጋል፡፡

የአዲስ አበባ አስተዳደር ጤና ቢሮ ከአዲስ አበባ ስፖርትና ወጣቶች ፌዴሬሽን ጋር በመሆን በሰጠዉ ጋዜጣዊ መግለጫ የጤና ቢሮ ምክትል ሃላፊ ዶክተር ሳሙኤል ዘ/መንፈስ ቅዱስ ፤የስኳር፣ የደም ግፊት እና የጡት ካንሰር #ነጻ የምርመራ አገልግሎትም ይሰጣል ብለዋል፡፡

በእለቱ የህብረተሰቡን የጤና ግንዛቤ ለማሳደግ የተለያዩ የጤና መልእክቶች ይተላለፋሉ፡፡

በአዲስ አበባ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ የስፖርት ውድድርና ተሳትፎ ባለሙያ አቶ እንግዳወርቅ ዳንኤል በበኩላቸው በእለቱ ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎችን የሚመሩ የአካል ብቃት ባለሙያዎችም እንደሚገኙ ገልጸዋል፡፡

የፊታችን ህዳር 30 በሚካሄደው ከትራፊክ ፍሰት ነጻ ቀን የመንግስት የስራ ሃላፊዎችና ዲፕሎማቶች የሚሳተፉበት ሲሆን፤ በዕለቱ ከ3ሺ እስከ 5ሺ ሰዎች ይሳተፋሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

🔹ፕሮግራሙ ከጠዋቱ 1 ሰዓት እስከ 6 ሰዓት የሚካሄድ መሆኑም ታውቋል፡፡

ምንጭ፦ አርትስ ቴሌቪዥን
@tsegabwolde @tikvahethiopia