TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.44K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
አየር ሃይል ጥቃት ፈፀመ‼️

#የኢፌዲሪ_አየር_ሃይል በሶማሊያ ከባይደዋ በስተምስራቅ 75 ኪሎ ሜትር ላይ ቡርሃይቤ በተባለ የአልሻባብ ይዞታ ላይ ጥር 16 ቀን 2ዐ11 ዓ.ም ድብደባ በመፈፀም ከፍተኛ ሰብአዊና ቁሳዊ ኪሳራ ማድረሱን የኢፌዲሪ መከላከያ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

ሚኒስቴሩ ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው የኢፌዲሪ አየር ሃይል #ተዋጊ ሂሊኮፕተሮች በፈፀሙት ለ44 ደቂቃ የዘለቀ ድብደባ 35 የአልሻባብ ታጣቂዎች ተደምስሰዋል፡፡

ከዚህ ውስጥም በስፍራው የአሸባሪ ቡድኑ የኦፕሬሽን ሃላፊ የነበረው አብዱ ኡስማንና የፈንጂ ቡድን ሃላፊው አብዱሰላም በድብደባው መገደላቸው ተረጋግጧል፡፡

በዚህ የአየር ድብደባ 2 የቴክኒክ፣ አንድ የጭነት፣ አንድ ፈንጂ የጫነ በድምሩ 4 ተሽከርካሪዎች እንዲሁም 5 ካሊበር መሳሪያዎች ወድመዋል፡፡

ከዚህ በፊትም የመከላከያ ሠራዊቱ በአልሸባብ ልዩ ልዩ ይዞታዎች ላይ ጥቃት በመፈፀም ከፍተኛ ሰብአዊና ቁሳዊ ኪሳራ እንዳደረሰበት የመከላከያ ሚኒስቴር የኢንዶክትሪኔሽን ዋና ዳይሬክቶሬት በላከው መግለጫ አስታውቋል፡፡

ምንጭ፦ የኢፌዲሪ መከላከያ ሚኒስቴር
@tsegabwolde @tikvahethiopia