TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.4K photos
1.47K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
"ማስፈራሪያ እየደረሰብን ነው"
.
.
የመርሃቢቴ ወረዳ ወጣቶች በአስተዳድሩ ማስፈራሪያ እየደረሰብን ነው አሉ። በመርሃቢቴ ወረዳ #የመብራት_ትራንስፎርመር ተነቅሎ እንዳይወሰድ አድርጋችኋል ተብለን ማስፈራሪያ እየደረሰብን ነው ሲሉ የአካባቢው ወጣቶች ተናገሩ፡፡

የወረዳው አስተዳድር በበኩሉ በፊት ከነበረው የተሻለ ትራንስፎርመር ለማስተከል እንቅስቃሴ ሲደረግ ሁከት የፈጠሩትን በህግ የመጠየቅ እንጂ ማስፈራሪያ አለማድረሱን ተናግሯል፡፡

የመርሃቢቴ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ተሾመ አስፋው፤ በአማራ ክልል ትራንስፎርመር የማሳደግ ስራ እየተሰራ በመሆኑ በወረዳው የነበረው 200 ኪሎ ዋት ትራንስፎርመር አቅም ስለበዛበት ለመቀየር 315 ኪሎ ዋት ሊቀየር ሲል ብጥብጥ መነሳቱን ገልፀዋል፡፡

በዚህ ምንም አይነት ትራንስፎርመር ከአካባቢው እንዳይወጣ መደረጉን ይገልፃሉ፡፡

በአሁን ወቅት አመራሩን ከህዝቡ የመነጠል ስራ እየተከናወነ መሆኑን በመጥቀስ፤ የከተማ መዘጋጃ ቤት ትራስፎርመር ሊሰርቁ ነው በሚል ማህበራዊ ሚድያው ላይ የሚሰራጨው ወሬ ስብዕናን የሚነካ ጉዳይ በመሆኑ በህግ እንደሚታይ አመልክተዋል፡፡

እንደ አቶ ተሾመ ገለፃ ሌባ እያሉ በማህበራዊ ሚድያ የሚያሰራጩትን በህግ የመጠየቅ ስራ እንጂ ፖሊስ እያስፈራራ አደለም፤ በወረዳው ማንኛውንም ጥያቄ በሰላም እንጂ በሁከትና በብጥብጥ የሚደረጉ እንቅስቃሴዎች ተቀባይነት የላቸውም፡፡

መምህር እንዳሻው ጌትዬ እንደሚናገረው፤ ትራንስፈርመር ሊወስዱ ሲሉ በወጣቱ ሃይል እንዲመለስ ተደርጓል፤ እንዲመለስ ጥረት ያደረጉትን ወጣቶች ፖሊስ ጣቢያ እየተጠሩ ማስፈራሪያ እየደረሰባቸው ነው፡፡

ነባሩ ትራንስፎርመር በቦታው ላይ የሚገኝ ሲሆን አዲሱ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ይገኛል፡፡ ይዘውት የመጡት አዲስ የተባለው የተበላሸ ሲሆን ከየት እንደመጣ አይታወቅም፡፡

በማይመለከታችሁ ነገር ውስጥ እየገባችሁ ነው እርምጃ ይወሰድባችኋል በማለት ኢንስፔክተር አያሌው ደበበ የሚባል የፖሊስ አዛዥ ወጣቶቹን ቢሮ በመጥራት እያስፈራራ እንደሚገኝ ተናግሯል፡፡ ወጣቶቹ እንዳይታሰሩ በተደረገ ጥረት እስካሁን የታሰረ ወጣት እንደሌለም ጠቁሟል፡፡

ምንጭ፦ ኢ.ፕ.ድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia