TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.3K photos
1.47K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Passport

ክፍያ የፈጸሙ ተገልጋዮች ሁሉ አስቸኳይ ፓስፖርት እንዲያገኙ ሊደረግ ነው።

የኢሚግሬሸንና ዜግነት አገልግሎት አስቸኳይ ፓስፖርት ለማግኘት የተቀመጡ ቅድመ ሁኔታዎችን በማንሳት፣ ክፍያ የፈጸሙ ተገልጋዮች ሁሉ በአስቸኳይ እንዲያገኙ ለማድረግ በዝግጅት ላይ መሆኑን ማስታወቁን ሪፖርተር ጋዜጣ ዘግቧል።

ቅድመ ሁኔታዎች ሲነሱ አሁኑ ላይ አስቸኳይ ፓስፖርት ለማግኘት ተገልጋዮች ማቅረብ ሚጠበቅባቸውን የሕክምና ደብዳቤ ፣ ነፃ የትምህርት ዕድል ማስረጃ... የመሳሰሉትን ማቅረብ አይጠበቅባቸውም፡፡

በቅርቡ በሚኒስትሮች ም/ቤት በፀደቀው የአገልግሎት ክፍያ ተመን ላይ ፓስፖርት በአንድና በአምስት ቀናት ውስጥ በአስቸኳይ ለማግኘት የተቀመጠውን ክፍያ " መክፈል የቻለ ሁሉ " ፣ የአገልግሎቱ ተጠቃሚ እንደሚሆን የኢሚግሬሽን ዜግነት አገልግሎት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ታምሩ ግንበቶ መናገራቸውን ሪፖርተር ገልጿል።

ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ ለሪፖርተር ጋዜጣ በሰጡት ቃል የተናገሩት ፦

- #በአስቸኳይ_ፓስፖርት ለማግኘት የተቀመጡትን ቅድመ ሁኔታዎችን ለማንሳት ዝግጅት እየተደረገ ያለው የአስቸኳይ ፓስፖርት አሰጣጡ ከሙስናና ከብልሹ አሠራር ጋር የተያያዘ በመሆኑ ነው፡፡

- " አስቸኳይ ፓስፖርት ከውስጥ ሠራተኞች ተነጋግረን እናስጨርሳለን " የሚሉ ደላሎች አሉ ከብልሹ አሠራሮች ጋር በተያያዘ ፣ በዓመት ግፋ ቢል ከ50 ሰዎች በላይ እያባረርን ነው። ከአስቸኳይ ፓስፖርት አሰጣጥ ጋር የተያያዙ ችግሮችን ሥር ነቀል በሆነ መንገድ ለመፍታት ያስችላል ተብሎ የታሰበው መፍትሔ አገልግሎቱን ለማግኘት የተቀመጡ ቅድመ ሁኔታዎችን ማንሳት ነው።

- አሁን ባለው አሠራር ፓስፖርት በአስቸኳይ ለማግኘት ከሚያስችሉ ማስረጃዎች መካከል ፦

• ወደ ውጭ ሄደው መታከም እንዳለባቸው የሚገልጽ የሕክምና ደብዳቤ ፣
• ለሁለተኛ ዲግሪና ከዚያ በላይ የሆነ የትምህርት ዕድል ማግኘትን የሚገልጽ ደብዳቤ
• የዲቪ ሎተሪ ዕድል ማግኘትን የሚያሳይ ማስረጃ ተጠቃሽ ናቸው፡፡ እነዚህ ቅድመ ሁኔታዎች ተነስተው ሥራ ሲያስጀምር ደንበኞች የሚስተናገዱት በአዲሱ የክፍያ ተመን ይሆናል።

- ቅድመ ሁኔታዎችን አንስቶ አገልግሎቱን ለመጀመር ጥናት ተጠንቷል፤ ይህንን አገልግሎት ለማስጀመር የፓስፖርት ወረቀት ፣ ላምኔት ፣ የማተሚያ ቀለም እና የቴክኖሎጂ ሥርዓቱ መለዋወጫዎችን ... የመሳሰሉ ግብዓቶች መሟላት እንዳለባቸው በጥናቱ ታይቷል።

የሚግሬሸንና ዜግነት አገልግሎት የኦንላይን ፓስፖርት ቡድን መሪ አቶ ዳንኤል የሻነው ለሪፖርተር የሰጡት ቃል ፦

• በአገልግሎቱ ዋና መሥሪያ ቤት ውስጥ የአስቸኳይ ፓስፖርት የሚሰጥባቸው መስኮቶች ሁለት ናቸው የአስቸኳይ ፓስፖርት አገልግሎትን ያለገደብ ለማስጀመር እንዲቻል ቢያንስ ስድስት መስኮቶች መኖር አለባቸው።

• አገልገሎቱን ለማስጀመር ሚያስፈልጉ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች ተጀምሯል ፤ ምን ያህል ብር እንደሚጠይቅም አዘጋጅተን ለሚመለከተው ክፍል አቅርበናል።

• አገልግሎቱ እንዲጀመር ተጨማሪ በጀት ይጠይቃል ፤ በጀቱ የሚፈቀድልን ከሆነ #በቅርብ_ወራት ውስጥ ይኼንን አስጀምረን አገልግሎት አሰጣጡን እናሻሽላለን።

አሁን ያለው የአስቸኳይ ፓስፖርት ክፍያና የሚሻሻለው ክፍያ ምን ይመስላል ?

አሁን በሥራ ላይ ባለው አሠራር መሠረት ባለ 32 ገጽ ፓስፖርት በ5 ቀናት ውስጥ በአስቸኳይ ለማግኘት 2,186 ብር የሚከፈል ሲሆን፣ ይኼንኑ ፓስፖርት በሁለት ቀናት ውስጥ ለማግኘት 3,279 ብር ክፍያ ይፈጸማል፡፡

በቅርቡ በሥራ ላይ መዋል ይጀምራል የተባለው አዲስ የአገልግሎት ክፍያ ተመን በ5 ቀናት ውስጥ ባለ 32 ገጽ ፓስፖርት ለማግኘት የሚጠየቀውን ገንዘብ ወደ 5,000 ብር አሳድጎታል፡፡

ፓስፖርቱን በአንድ ቀን ለማግኘት ደግሞ 6,500 ብር ክፍያ መፈጸም እንዳለበት ደንቡ ያስረዳል፡፡

የባለ 64 ገጽ ፓስፖርት በ5 ቀናት ውስጥ ለማግኘት 6,500 ብር የሚከፈል ሲሆን፣ በአንድ ቀን ለማግኘት የሚከለፈለው ክፍያ 8,000 ብር ይደርሳል።

ምንጭ፦ ሪፖርተር ጋዜጣ (ethiopianreportr.com)

@tikvahethiopia