TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.9K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ሀላባ ከተማ‼️

በደቡብ ክልል ሀላባ ከተማ ትናንት በተሰራጨ #ሀሰተኛ_ወሬ የተነሳሱ ወጣቶች በከተማው በሚገኙ ቤተክርስቲያናት ላይ #ጉዳት ማድረሳቸውን የከተማው ነዋሪዎች ገለጹ፡፡

ነዋሪዎቹ እንዳሉት በከተማው #የማቃጠልና የንብረት #ማውደም ድርጊቱ የተፈጸመው ሌንዳ በር እና ዋጃ በር በተባሉ ቀበሌያት ውስጥ በሚገኙ የፕሮቴስታንት ቤተክርስቲያናት ላይ ነው፡፡ በስፍራው ነበርኩ ያሉ እንድ የከተማው አዛውንት ጥቃቱ የተጀመረው በድራሜ ከተማ መስኪድ መቃጠሉንና ኢማም መገደሉን የሚገልጹ ወሬዎች ከተናፈሱ በኋላ በቡድን የተሰባሰቡ ወጣቶች በቤተክርስቲያናቱ ላይ ጥቃት ሲያደርሱ መመልከታቸውን ለጀርመን ድምፅ ራድዮ ገልጸዋል፡፡

የጀርመን ድምፅ ራድዮ በሥልክ ያነጋገራቸው የሀላባ ዞን ሰላምና ፀጥታ መምሪያ ሃላፊ አቶ #ዓለሙ_ሌንቢሶ ደግሞ በከተማው በተሳሳተ ወሬ የተነሳሱ ወጣቶች አንድ ቤተክርስቲያን በእሳት ያቃጠሉ ሲሆን በሌሎች ሰባት ቤተክርስቲያናት ላይ ደግሞ ንብረቶችን የማውደም ድርጊት መፈጸማቸውን ገልጸዋል፡፡ በአሁኑ ወቅት እጅ ከፍንጅ የተያዙ 20 ግለሰቦችን ጨምሮ 63 ተጠረጣሪዎች በህግ ቁጥጥር ስር መዋላቸውን የጠቆሙት ሃላፊው የዞኑ ፖሊስ ኮሚሽነርም ጥቃቱን ለመከላከል ጥረት ባለማድረጋቸው ከሃላፊነታቸው ተነስተው ምርመራ እየተካሄደባቸው እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡

በኢትዮጲያ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ምንጫቸው ባልተረጋገጡ ወሬዎች በመነሳሳት የሚፈጸሙ የደቦ ጥቃቶች እየተበራከቱ መምጣታቸው ይታወቃል፡፡ በቅርቡ በጉዳዩ ዙሪያ ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ጥያቄ የቀረበላቸው ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር አብይ አህመድ ቀደም ባሉት ጊዚያት ደቦ እርሻን በህብረት ለመሥራት ይውል እንደነበር አስታውሰው አሁን ግን ጸብም በደቦ እየሆነ መምጣቱ አሳሳቢ ነው ሲሉ ምላሽ መስጠታቸው ይታወሳል፡፡

ምንጭ፦ የጀርመን ድምፅ ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia