TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.3K photos
1.47K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ህገወጥ_የጦር_መሳሪያ_ዝውውር !

1ኛ. በዛሬው ዕለት በደቡብ ጎንደር አስተዳደር ዞን በአ/ዘመን ከተማ አስተዳደር ፖሊስ በተሽከርካሪ ፍተሻ በህገ ወጥ መንገድ 250 የክላሽ ጥይት ይዞ ከጎንደር ወደ ባህር ዳር በሰሌዳ ቁጥር AA3-03741 ላንድክሮዘር መኪና ተሳፍሮ ሲጓዝ የነበረ አንድ ግለሰብ በቁጥጥር ስር ውሏን። ከሻንጣው ውስጥ ነው 250 የክላሽ ጥይት የተያዘድ። ግለሰቡ አድራሻው ጎንደር ዙሪያ ማክሰኝት ወረዳ ሰንደባ ቀበሌ ነው።

2ኛ. በቡራዩ ከተማ ህገ ወጥ የጦር መሳሪያ መያዙን የቡራዩ ከተማ ፖሊስ መምሪያ አስታውቋል።

በቁጥጥር ስር የዋለው 42 ቱርክ ሰራሽ ሽጉጦችና ከ 2 ሺህ 500 በላይ የተለያዩ ጥይቶች ሲሆን ከሽንኩርት ጋር ተተቀላቅለው ነው የተያዙት። በአሁኑ ወቅት ከዚሁ የወንጀል ድርጊት ጋር በተገናኘ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተደረገ ነው።

3ኛ. ሰሞኑን በህገ-ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀስ የነበረ በርካታ የጦር መሳሪያ በቁጥጥር ስር መዋሉን የፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቢሮ አስታውቋል።

ታርጋ ቁጥሩ " ኮድ 3-12568 አ/አ " የሆነ አይሱዚ የጭነት መኪና መነሻውን ባህርዳር ከተማ ልዩ ቦታው ቀበሌ 04 በማድረግ ህገ-ወጥ የጦር መሳሪያ በመጫን ጉዞውን ወደ አዲስ አበባ በማድረግ በተለምዶ ጎጃም ኬላ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ እንደደረሰ በፖሊስ በቁጥጥር ስር ውሏል፡፡

መኪናው ሲፈትሹ 88 ቱርክ ሰራሽ ሽጉጦችና ከ5,000 (አምስት ሺህ) በላይ የተለያዩ ጥይቶችን ከመኪናው ከላይ አካል ላይ ተገኝቷል። ከዚሁ የወንጀል ድርጊት ጋር በተገናኘ 2 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተደረገ ነው።

ያንብቡ :telegra.ph/Tikvah-07-01

ምንጭ፦ ደብረ ማርቆስ ፖሊስ መምሪያ፣ ቡራዩ ፖሊስ መምራያ ፣ ፌዴራል ፖሊስ

@tikvahethiopia
በአዲስ አበባ ዙሪያ እየተካሄደ ካለው ቤት የማፍረስ ዘመቻ ጋር በተያያዘ ቤታቸው የፈረሰባቸው ግለሰቦች ለኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ ቅሬታ አቅርበው ነበር።

በዚህ መሰረትም የጉባኤው 3 የሰብዓዊ መብቶች ባለሞያዎች እና አንድ ሹፌር ታህሳስ 27 " ዓለም ባንክ " አካባቢ ጥቆማውን ለማጣራት ይሄዳሉ ፤ በፖሊስም ተይዘው ያሉበትን ማወቅ ሳይቻል ከቆየ በኃላ በተደጋጋሚ በተደረገ ጥረት አራቱም ሰራተኞችና የድርጅቱ መኪና ዓለምገና ሁለተኛ ፖሊስ ጣቢያ ታስረው እንደሚገኙ ታውቋል።

በተጨማሪም ፤ ኢሰመጉ ባሉት ባለሙያዎች ላይ የተለያዩ #ጫናዎች፣ $ዛቻ እና #ማስፈራራትን ጨምሮ እየደረሰበት እንደሚገኝ አሳውቋል።

ኢሰመጉ ይህ አይነት ድርጊት ከህግ አግባብ ውጭ የሆነና ጉባኤው የተቋቋመበትን ዓላማ (ለሰብዓዊ መብት መከበር) እንዳያስፈፅም እንቅፋት የሚሆንና ባለሞያዎቹ በነፃነት ተንቀሳቅሰው እንዳይሰሩ ለማድረግና #ለማሸማቀቅ የተደረገ ነው ብሎታል።

መንግስት በኢስመጉ ላይ የተለያየ አይነት #ህገወጥ_እስር እና የተለያዩ ጫናዎችን ከመፈፀም ይቆጠብ ያለው ጉባኤው ፖሊስ ሰራተኞቹን #በአስቸኳይ ከእስር እንዲፈታ አሳስቧል።

@tikvahethiopia
" ' አክሲዮን እናሻሽጣለን ' የሚሉ ማስታወቂያዎችና ግለሰቦች ህገወጥ ናቸው " - የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን

የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን ፤ " የአክሲዮን ድርሻ እናሻሽጣለን " የሚሉ ማስታወቂያዎችም ሆኑ ግለሰቦች ህገወጥ መሆናቸውን ህብረተሰቡ ይወቅልኝ አለ።

በኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን ከፍተኛ የካፒታል ገበያ አማካሪ አቶ አሰፋ ስሞሮ ፤ " በማህበራዊ የትስስር ገጾች ላይ ከአክሲዮን ገበያ ጋር በተገናኘ #የድለላ ስራ እየሰሩ ያሉ #ህገወጥ ግለሰቦች መኖራቸውን መረጃውን አለን ነገር ግን አንዳቸውም ከባለስልጣኑ ፈቃድ አላገኙም " ብለዋል።

ባለስልጣን መ/ቤቱ ለጊዜው ፈቃድ መስጠት አለመጀመሩን የገለጹት ባለሙያው የፈቃድ መመሪያው ለፍትህ ሚኒስቴር መላኩን በማንሳት በሚደረጉ ቀጣይ ውይይቶች ይጸድቃል ተብሎ እንደሚጠበቅ ተናግረዋል፡፡

በዚህም በአሁኑ ወቅት ከባለስልጣኑ ፈቃድ ውጪ " አክሲዮን እናሻሽጣለን " የሚሉ ማስታወቂያዎችም ሆነ ግለሰቦች ህገወጥ መሆናቸውን ህብረተሰቡ ሊያውቅ ይገባል ሲል አስገንዝበዋል።

በተቀመጠው አዋጅ መሰረት የካፒታል ገበያ አገልግሎት ሰጪዎች በሚል መጠሪያ ተቋሙ ፈቃድ እንደሚሰጥ በመግለጽ አስፈላጊው ቁጥጥርና ክትትል የሚደረግባቸው እንደሚሆኑም ከአሁኑ ጠቁመዋል፡፡

ባለስልጣኑ በይፋ ፈቃድ መስጠት ሲጀምርም በመሰል ህገወጥ ተግባራት የሚሳተፉ ግለሰቦችን በህግ #ተጠያቂ እንደሚያደርግም አሳውቋል።

ይህ መረጃ ባለቤትነቱ #የአሃዱሬድዮ ነው።

@tikvahethiopia