TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.8K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ኮንትሮባንድ⬇️

በ2010 በጀት ዓመት በወጪና በገቢ እቃዎች ላይ በተካሄደ ጸረ ኮንትሮባንድ ቁጥጥር ከአንድ ቢሊየን ብር በላይ ግምት ያለው ንብረት በቁጥጥር ስር መዋሉን የኢትዮያ ገቢዎችና ጉሙሩክ ባለስልጣን አስታውቋል።

የኢትዮያ ገቢዎችና ጉሙሩክ ባለስልጣን የትምህርትና ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ኤፍሬም መኮነን ለFBC እንደተናገሩት የወጪውም ሆነ የገቢ ኮንትሮባንዶች በቁጥጥር ስር ባይውሉ መንግስት ሊያገኝ የሚገባውን የታክስና ቀረጥ ገቢ ከማሳጣትም በላይ በህዝብ ላይ ጉዳት ሊያደርሱ የሚችሉ ናቸው።

በቁጥጥር ስር ከዋሉት የኮንትሮባንድ እቃዎች መካከል ህገ ወጥ የገንዘብ ዝውውር፣ አልባሳት፣ ምግብና መጠጥ ዋና ዋናዎቹ መሆናቸውም ነው የተገለጸው።

ጫት፣ የቀንድ ከብት፣ ጤፍና ምስርም ሌሎች በህገ ውጥ መንገድ ሲወጡ የተያዙ ምርቶች ሲሆኑ፥ የኢንዱስትሪ ጥሬ እቃ ፋቃድን ሽፋን በማድረግ ያልተፈቀዱ እቃዎች ወደ ሃገር ውስጥ ሲገቡ ተይዘዋል ተብሏል።

በገቢ ኮንትሮባንዶች ላይ ትልቁን ድርሻ የያዙት አልባሳት፣ ምግብና መጠጥ፣ ጦር መሳሪያ፣ ኤሌክትሮኒክስና መለዋወጫ እቃዎች እንደሆኑም ነው የተጠቆመው።

ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በ2010 ዓ.ም አሰራሩን በማሻሻል የተለያዩ ባለድርሻ አካላቶችን በማሳተፉ የተሻለ ውጤት መመዝገቡን ያመላከቱት ዳይሬክተሩ የሀገር አቀፍ የጸረ ኮንትሮባንድ ግብረ ሀይል ወደ ታችኛው መዋቅር እንዲወርድ መደረጉን እና በየደረጃው እራሱን የቻለ ኮማንድ ፖስት መቋቋሙን አስረድተዋል።

በዚህም በጥቂት ጊዚያት #ሚሌና #ጅግጅጋ ላይ ከ315 ሚሊየን ብር፣ #ሞያሌ#ሀዋሳና #ድሬዳዋ ላይ 300 ሚሊየን ብር የሚጠጋ ግምት ያለውን ንብረት በቁጥጥር ስር ለማዋል መቻሉን ነው የተናገሩት።

አሁን ላይ በጸረ ኮንትሮባንድ እንቅስቃሴው ለተገኘው ውጤት የህብረተሰቡ ተሳትፎ ትልቅ ሚና አንዳለው የጠቆሙት ዳይሬክተሩ ይህ ተግባር በ2011 ዓ.ም ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ጥሪ አስተላልፈዋል።

©FBC
@tsegbwolde @tikvahethiopia
#update ሀዋሳ⬇️

የደኢህዴን 10ኛው ድርጅታዊ ጉባኤ #በነገው ዕለት እንደሚጀምር የደኢህዴን ማ/ኮሚቴ ፅ/ቤት ኃላፊው አቶ ሞገስ ባልቻ ገለፁ፡፡ አቶ ሞገስ ባልቻ ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫቸው፦

የ10ኛው መደበኛ ጉባኤ ዝግጅት መጠናቀቁን፣ #ሀዋሳና ነዋሪዎቿ በተለመደው እንግዳ ተቀባይነት ባህላቸው እንግዶቻቸውን እየተቀበሉ መሆኑን፣ በጉባኤው በክብር #የሚሰናበቱ አመራሮች እንደሚኖሩ፣ የህገ ደንብ፣ #አርማና #ስያሜ ለውጥን የሚመለከት ውይይት እንደሚካሄድና በጉባኤተኛው እንደሚወሰን እንዲሁም አዳዲስ አመራሮች ወደ ድርጅቱ የመሪነት እርከን እንደሚቀላቀሉ አስታውቀዋል፡፡

ምንጭ፦ የደህዴን ፅ/ቤት
@tsegabwolde @tikvahethiopia