TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.4K photos
1.47K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Afar #Somali🚨

" የግጭቱ ማገርሸት ለሰላማዊ ሰዎች ግድያ እና መፈናቀል ምክንያት ሆኗል " - ኢሰመኮ

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በአፋር እና ሶማሌ አዋሳኝ አካባቢዎች ግጭት ማገርሸቱ ገልጿል።

ኮሚሽሙ ግጭቱ እንዳሳሰበውም አመልክቷል።

ኢሰመኮ በቅርቡ በሚያዚያ ወር የተደረሰውን የተኩስ አቁም ስምምነት በመጣስ በሶማሊ ክልል ሽንሌ ዞን እና አፋር ክልል አዋሳኝ ያገረሸው ግጭት አሳሳቢ ነው ብሏል።

ግጭቱ ለሰላማዊ ሰዎች ግድያ እና መፈናቀል ምክንያት እንዳሆነ ገልጿል።

በኮሚሽኑ የጅግጅጋ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ ዶ/ር ሰኢድ ደመቀ ለዶይቼ ቬለ በሰጡት ቃል ፤ " የአሁኑ ግጭት የተጀመረው ከግንቦት 29 ቀን 2016 ዓ.ም 2024 ወዲህ ነው " ብለዋል።

" በግጭቱ የተወሰኑ ሰዎች ሞት፤ መፈናቀል እና የአካል ጉዳት፤ የንብረት መውደም እንደደረሰ ነው ያለው መረጃ በእኛ በኩል ግጭቱ እንዳገረሸ። በትክልል ስንት ሰው ሞተ፤ ቆሰለ የሚለውን ገና በምርመራ የምናጣራው ነው " ብለዋል።

" በአሁኑ ወቅት ግን ጠቅለል ባለ መልኩ የሰው መፈናቀል፤ ሞት እና ጉዳት እንዳለ ነው " ሲሉ ገልጸዋል።

ኢሰመኮ ከሁለቱ ክልሎች የመንግስት አስተዳዳሪዎች ተረዳሁት ባለው መሠረት ፥ በሁለቱም ክልሎች በኩል የሰላማዊ ሰዎች ግድያ እና መፈናቀሎች ተፈጽሟል።

በቅርቡ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ለተገኘው አዎንታዊ የሰላም ማስፈን ሂደት ሁለቱ ክልሎች ያሰጡትን አዎንታዊ ምላሽ ያደነቀው ኢሰመኮ፤ የተጀመረው የሰላም ጥረት እንዲቀጥል የፌዴራልም ሆነ የሁለቱ ክልሎች መንግስታት የቀጠለውን ግጭት እንዲያስቆሙት ጥሪውን አቅርቧል።

የኢሰመኮ ምክትል ዋና ኮሚሽነር ራኬብ መሰለ የፌዴራል መንግስት አስቸኳይ የግጭት ማስቆም ጥረት እንዲያስደርግ ጥሪ አቅርበዋል።

የሁለቱ ክልሎች አስተዳዳሪዎች በቀጣይ ሕዝበ ሙስሊሙ ከሚያከብረው የኢድ አል-አደሃ በዓል አስቀድሞ ሰላም እንዲሰፍን ጥረት እንዲያደርጉም ጠይቀዋል።

#DWAmharic #EHRC

@tikvahethiopia
🔈 #የነዋሪዎችድምጽ

በመቐለ የተለያዩ ክፍሎች ጨምሮ በሌሎች የትግራይ ከተሞች ተደጋጋሚ የኤሌክትሪክ ኃይል መቋረጥ እያጋጠመ ነው።

ይህን ተከትሎ ነዋሪዎች ለከፋ ችግር ተጋልጠለዋል።

የመቐለ የተወሰነ ክፍል የኤሌክትሪክ ሐይል ከተቋረጠ ከ40 ቀናት በላይ ተቆጥረዋል።

ትላልቅ ኢንዳስትሪዎች ጨምሮ በኃይል እጦትና መቋረጥ እየተፈተኑ ነው።

በተለይ በተያዘው የክረምት ወቅት በስፋት እየታየ ያለው እና መቐለ ከተማ ጨምሮ በርካታ የትግራይ ክልል አካባቢዎች የሚሸፍነው ተደጋጋሚ የኤሌክትሪክ ሐይል መቋረጥ በነዋሪዎች ዘንድ የከፋ ማሕበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ችግር ፈጥሮ ይገኛል።

በመቐለ በተለምዶ ሰብዓ ካሬ ተብሎ በሚታወቅ አካባቢ የኤሌክትሪክ ሐይል አገልግሎት ከተቋረጠ ከ40 ቀናት በላይ ሆኗል።

ከመቐለ ውጪም ቢሆን በሀገረሰላም እና ወጀራት አካባቢዎች ከወር በላይ ለሚሆን ግዜ የኤሌክትሪክ ኃይል ተስተጓጉሎባቸው ቆይቷል።

በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የሰሜን ሪጅን የትራንስሚሽንና ሳብስቴሽን ኦፕሬሽን ዳይሬክተር አቶ ሮቤል ገብረእግዚአብሔር፥ " የኃይል መቋረጡ ዋነኛ ምክንያት በኃይል ማስተላለፊያ ላይ የደረሰ ጉዳት ነው " ብለዋል።

ችግሩ በግዚያዊነት እስከ መጪው ነሐሴ 5 ቀን 2016 ድረስ ለመፍታት ይሰራል። በዘላቂነት ደግሞ ተጨማሪ ጥረቶች ይደረጋሉ ሲሉ ተናግረዋል።

ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የዶቼ ቨለ ሬድዮ ነው።

#DWAmharic

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM