TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.3K photos
1.47K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ጨፌ ኦሮሚያ🔝

የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ፕሬዝዳንት አቶ #ለማ_መገርሳ የ6 ወራት የስራ አፈጻጸምን ለጨፌ ኦሮሚያ ያቀረቡ ሲሆን፣ በሪፖርታቸው የመሬት ወረራና ሕግ ወጥ ግንባታን ለመከላከል ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን ገልጸው፣ ህዝቡ #የሕግ_የበላይነትን የማስከበር ሂደት ውስጥ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማድረጉን ተናግረዋል፡፡ በክልሉ ተከስቶ የነበረውን የጸጥታ ችግር ለመፍታት ባለፉት 6 ወራት በርካታ ስራዎች መሰራታቸውን አቶ ለማ ተናግረዋል፡፡

የክልሉ መንግስት #ሰላም_እንዲኖር እየሰራ ቢሆንም በክልሉ አንዳንድ አከባቢዎች የጸጥታ ችግሮች መከሰታቸውን የገለጹት አቶ ለማ፣ ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት ችግሩ እንዲከሰት ያደረጉ አካላትን ወደ ሕግ የማቅረብ ስራዎች እየተሰሩ ናቸው ብለዋል፡፡

በተለይ በጉጂና በምዕራብ ጉጂ ዞኖች የተከሰቱትን #የጸጥታ_ችግሮች በትዕግስትና በሳል አመራር በመስጠት ሁኔታው ወደ #ሰላም እንዲመጣ መደረጉን አቶ ለማ በሪፖርታቸው ገልጸዋል፡፡ ህዝቡ ከመጣው ለውጥ ተጠቃሚ እንዲሆን ለማድረግ ስራዎች መሰራታቸውንም አቶ ለማ ገልጸዋል፡፡ የፖለቲካ ምህዳሩን ለማስፋት በተሰራው ስራ የተለያዩ ፓርቲዎች ወደ አገር ገብተው የፖለቲካ እንቅስቃሴ እያደረጉ መሆናቸው በሪፖርቱ ተገልጿል፡፡

#OBNLive

Via EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia