TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.7K photos
1.44K videos
207 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ETHIOPIA

" የድርቅና ጎርፍ አደጋዎች በቀጣዮቹ ሳምንታትም #ተባብሠው ሊቀጥሉ ይችላሉ " - የሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት

በኢትዮጵያ በተለያዩ አካባቢዎች እየተከሠቱ ያሉት የድርቅና የጎርፍ አደጋዎች በቀጣዮቹ ሳምንታትም #ተባብሠው_ሊቀጥሉ እንደሚችሉ የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት አስታውቋል።

የኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳሬክተር አቶ ክንፈ ኃ/ማሪያም በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ62ኛ በኢትዮጵያ ለ42ኛ ጊዜ በሚከበረው የሚቲዎሮሎጂ ቀን ላይ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር ነው ይህ የተሰማው።

አቶ ክንፈ " በተቋሙ የተሠሩ ጥናቶች የሚያሳዩት #የድርቅ እና #የጎርፍ አደጋዎች በሀገሪቱ በቀጣይም በይበልጥ ተጠናክረው ይከሰታሉ " ብለዋል።

" የሚደርሰውን አደጋ ለመቋቋም የተጠናከረ የአየር ሁኔታ መከታተል ፣ መተንበይ እና ቅድሚያ ማስጠንቀቂያ ሥርዓትን መገንባትና ማዘመንን ይገባል " ያሉት ምክትል ዳይሬክተሩ " እየተከሰተ ያለውን የአየር ንብረት መዛባት ቀድሞ ለመተንበይ የሚያስችል ብሔራዊ የአየር ጠባይ አገልግሎት ማዕቀፍ በሀገሪቱ ተዘርግቷል ፤ ይህ ተጠናክሮ ወደ ሙሉ ትግበራ እንዲገባ የባለድርሻ አካላት ርብርብ ያስፈልገዋል " ብለዋል።

አቶ ክንፈ ፤ በሀገሪቱ ለማኅበራዊ እና ለኢኮኖሚ መሠረት የሆኑ የግብርና፣ የውሀ፣ የኢነርጂና የአደጋ ሥጋት ቅነሳ መርሐ ግብሮች በአየር ንብረት መዛባት ተፅዕኖ ስር መሆናቸውን ገልፀው በእነሱ ላይ የሚደርሠውን የአየር ንብረት መዛባት አደጋ ለመቀነስ ተቋሙ ጥናትና ክትትል የማድረግ ሥራ እየሰራ መሆኑን ጠቁመዋል።

" በአየር ንብረት መዛባት የሚመጡ አደጋዎችን ማለትም ጎርፍ፣ ድርቅና የመሳሰሉትን ለመቀነስ ተቋሙ ክትትልና ጥናት በማድረግ ኅብረተሰቡን ከአደጋ ለመከላከል እየሠራ ነው " ሲሉ የገለፁት አቶ ክንፈ ፥ በአየር ንብረት መዛባት የሚደርሰውን የተለያየ አደጋ በዘላቂነት ለመቋቋም ተቋሙ ከባለድርሻ አካላት ጋር እየሠራ መሆኑን ባለድርሻ አካላትም በአጋርነት እየሰሩ ስለመሆናቸው ተናግረዋል።

#ኢፕድ

@tikvahethiopia