TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.4K photos
1.47K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ወ/ሮ ሙፈሪያት ከሚል⬇️

በሀገሪቱ እየተካሄደ ያለውን የለውጥ ሂደት ከመደገፍና ከማሳደግ ውጪ ሌላ #አማራጭ እንደሌለ የደኢህዴን ሊቀ መንበር በመሆን በድጋሚ የተመረጡት ወይዘሮ #ሙፈሪያት_ካሚል ገለፁ።

ሊቀ መንበሯ ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚል 10ኛው የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ደኢህዴን) ድርጅታዊ ጉባዔ #መጠናቀቅን ተከትሎ ለጉባኤተኛው የማጠቃለያ መልእክት አስተላልፈዋል።

ወይዘሮ ሙፈሪያት በማጠቃለያ ንግግራቸው፥ ሀገሪቱ በአሁኑ ወቅት በለውጥ ሂደት ላይ መሆኗን ገልፀው፤ የደኢህዴን አባላት፣ አመራሮች እና ጉባዔተኛው ለውጡ ተጠናክሮ እንዲቀጥል መስራት አንዳለባቸው ገልፀዋል።

ይሁን እንጂ በአሁኑ ወቅት እየተካሄደ ያለውን ሀገራዊ ለውጥ #ለማደናቀፍ ሌት ተቀን የሚሰሩ ሀይሎች እንዳሉ ሊቀመንበሯ ገልፀዋል።

እነዚህ ሀይሎች 10ኛው የደኢህዴን ጉባዔ እንዳይሳካም ሲንቀሳቀሱ ነበር ያሉት ወይዘሮ ሙፈሪያት፤ ከሀዋሳ ውጪ በህዝቦች መካከል #ግጭት ለመፍጠር ገንዘብ ተመድቦላቸው #ሲንቀሳቀሱ እንደነበረ ከክልሉ የፀጥታ ሀይሎች ጋር በተሰራ ስራ ለማወቅ መቻሉን አንስተዋል።

የደኢህዴን አባላት፣ አመራሮች እና ጉባዔተኛው ይህንን በመገንዘብ እነዚህን የጥፋት ሀይሎች በንቃት መጠበቅና ማጋለጥ ያስፈልጋል ብለዋል።

በአሁኑ ወቅት በሀገሪቱ እየተካሄደ ያለውን ሀገራዊ የለውጥ ሂደት ከመደገፍና ካማሳደግ ውጪ ሌላ አማራጭ የለም ያሉት ሊቀ መንበሯ ወይዘሮ ሙፈሪያት፥ ከዚህ ውጨ ያለው አማራጭ #የጥፋት አማራጭ ነው ሲሉም ተናግረዋል።

ስለዚህ የለውጥ ጉዞውን በማሳከት ሂደት የደኢህዴን አባላት፣ አመራሮች እና የጉባኤተኛው ሚና አጅግ የላቀ መሆኑንም አስገንዝበዋል።

ከነገ ጀምሮ #በሀዋሳ ከተማ የሚካሄደው 11ኛው የኢህአዴግ ድርጅታዊ ጉባዔ ሰላማዊ እና ዴሞክራሲያዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ በማድረግ እንዲሁም የተጀመረውን የህዳሴ ጉዞ ከዳር ለማድረስ የሚደረገውን ርብርብ መቀጠል ይኖርብናል ሲሉም ተናግረዋል።

በኢህአዴግ ጉባኤ ላይ የሚሳተፉ የደኢህዴን ጉባዔተኞች ልክ በደኢህዴን ድርጅታዊ ጉባዔ ላይ ያደረጉትን የነቃ ተሳትፎ፣ ዴሞክራሲያዊ ሂደትና ሰላማዊ ሁኔታን እንዲያስቀጥሉ ጥሪ አቅርበዋል።

ሊቀ መንበሯ ወይዘሮ ሙፈሪያት አክለውም፥ 10ኛው የደኢህዴን ድርጅታዊ ጉባዔ በዚህ መልኩ የተሳካ ሆኖ በመጠናቀቁም እንኳን ደስ አላችሁ እንኳን ደስ አለን ብለዋል።

ጉባዔው የተሳካ እንዲሆን የሀዋሳ ከተማ እና የሲዳማ ዞን እንዲሁም የልግ ባለሀብቶች ላደረጉልት አቀባበል እንዲሁም የኢህአዴግ ጉባዔን ለማስተናገድ እያደረጉ ላለው ዝግጅት ለአመራሩ እና ለህዝቦች ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

ምንጭ፦ ፋና ብሮድካስቲንግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia