TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.7K photos
1.44K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
' ቤቲንግ ' ሊታገድ ነው ?

ከሰሞኑን በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ " ቤቲንግ " ሊታገድ መሆኑን የሚገልፁ በትክክል ምንጫቸው ያልተገለፁ ፅሁፎች ሲሰራጩ ተስተውሏል።

ብሄራዊ ሎተሪ አስተዳደር ግን እየተሰራጩ ያሉት መልዕክቶች ፍፁም ስህተት ናቸው ብሏል በማህበራዊ ትስስር ገፁ ዛሬ ባወጣው ማሳሰቢያ።

" ' አንዳንድ ግለሰቦች በማህበራዊ ሚዲያ ቤቲንግ ሊዘጋ ነው ' በማለት የሚያሰራጩት መልእክት ፍጹም ስህተት መሆኑን እንገልፃለን " ያለው አስተዳደሩ " የስፖርት ውርርድ ጨዋታዎችም ሆነ  ሎተሪን   በተመለከተ ማንኛውም መረጃ ከብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር ብቻ ማግኘት እንደሚገባ አመልክቷል።

ከዚህ ቀደም ከ ' ቤቲንግ / ስፖርታዊ ውርርድ / ' ጋር በተያያዘ ፤ የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር #እንዲታገድ እየሰራ መሆኑን አሳውቆ እንደነበር ይታወሳል።

ሚኒስቴር መ/ቤቱ  ፤ ከታዲጊዎች እና ወጣቶች ስብዕና ግንባታ እንዲሁም በተለያየ መንገድ ከሚያስከትላቸው ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ቀውሶች አንጻር ነው ዘርፉ #ሊታገድ ይገባል በሚል እየሰራ እንደሆነ አሳውቆ የነበረው።

የስፖርት ውርርድ ' ቁማር ነው ' ብሎ የሚያምነው ይኸው የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር መ/ቤት ፤ በተለያየ ጊዜ ሰርቻቸዋለሁ ባላቸው የዳሰሳ ጥናቶች ቤቲንግ ለወጣቱና ለታዳጊው ዘርፈ ብዙ አደጋ የደቀነ መሆኑን አመላካች መሆኑን ፤ ቁማር ታዳጊዎችን ይሁን አዋቂ ሰዎችን ወዳልተፈለገ መንገድ ሊወስድ የሚችል ማህበራዊ ቀውስ እንደሆነና ማንኛውም ሰው ሰርቶ የመለወጥ እሳቤውን የሚያቀጭጭ፣ ቤተሰብን ጭምር ወደ መበተን ሊያደርስ የሚችል ጉዳይ መሆኑን አስገንዝቦ ነበር።

ወጣቶች እና ታዲጊዎች ለቤቲንግ ውርርድ ሲሉ ያላቸውን ነገር በሙሉ እስከማውጣት ይደርሳሉ ፤ ወጣቶች ስራን ከመስራት ይልቅ በአቋራጭ መክበር እንዲያስቡ በማድረግ ምርት እና ምርታማነትን የሚቀንስ ተግባር ነው የሚልው መ/ቤቱ ቤቲንግ እንዲታገድ ፍቃድ ለሚሰጡት የንግድ ሚኒስቴር እና የብሄራዊ ሎተሪ አስተዳደር ተቋማት አስፈላጊውን የግንዛቤ እና የማሳወቅ ስራ ቢሰራም ባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን አስተዋፅኦ ባለማድረጋቸው ለውሳኔው መዘግየት ዋነኛ ምክንያት መሆኑን ገልጾ ነበር።

የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ቤቲንግ እንዲታገድ ብርቱ እንቅስቃሴ ማድረግ መጀመሩን ካሳወቀ ወራት ቢቆጠርም እስካሁን በጉዳዩ ላይ አዲስ ነገር የለም።

የብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር ግን በ ' ቤቲንግ ' ኮሚሽን (15%) በሚሊዮን የሚቆጠር ብር ያስገኛል (ለሀገር) ፣ በርካታ ሰው በተለይ ሴቶችን ቀጥሯል ፣ ለማህበራዊ ጉዳይ ከገቢው ያውላል ፣ ቤት ይከራያል ፣ ገንዘብ ኢኮኖሚ ውስጥ እንዲንቀሳቀስ ያደርጋል ... ይህ ሁሉ ጥቅሞቹ ናቸው ብሎ ያምናል።

" ቤቲንግ " አትራፊ እንደሆነ የሚገልጸው አስተዳደሩ " ጨዋታ " እንጂ " ቁማር " አይደለም ብሎ ያምናል። በስርዓት እንዲመራም መመሪያዎችን አውጥቶ እየሰራ እንደሆነና " እኛ ጨዋታውን አቅርበናል ፤ ተጫዋቹ ደግሞ በኃላፊነት መጫወት አለበት " ባይ ነው።

ማህበራዊ ቀውስ ያመጣ እንደሆነ ኃላፊነት ያለባቸው አካላት አጥንተው ከጉዳቱ ጥቅሙ ያመዝናል በሚል ከሚታገድ በህግ እንዲመራና የማይገባቸው ሰዎች እንዳይጫወቱ ክትትል  ቢደረግ የተሻለ መሆኑ ታምኖበት እየተሰራ እንደሆነ በከወራት በፊት ገልጿል።

ከሰሞኑን በማህበራዊ ሚዲያ ላይ " ከጥር 3 ጀምሮ ቤቲንግ ይታገዳል " የሚሉ ምንጫቸው ያልተረጋገጠ መረጃዎች በስፋት ሲሰራጩ የነበረ ሲሆን የብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር ይህ ፍፁም የተሳሳተ ነው ፤ ማንኛውም ቤቲንግ / የስፖርት ውርርድ ነክ መረጃ የሚገኘው ከኔው ነው እንጂ ከሌላ አይደለም ሲል አስገንዝቧል።

#ቲክቫህኢትዮጵያ

@tikvahethiopia