TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.4K photos
1.47K videos
209 files
4.04K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#JimmaUniversity

የጅማ ዩኒቨርሲቲ ኮሚዩኒቲ ትምህርት ቤት በ2011 ዓም የትምህርት ዘመን በትምህርታቸው ከፍተኛ ውጤት ላመጡ የ10ኛ ክፍል ተማሪዎች የማበረታቻ ሽልማት ስነ-ስርዓት አካሔደ፡፡ በዚህ ስነስርዓትም ላይ አራት ነጥብ ያመጡ 53 ተማሪዎች የእውቅና ምስክር ወረቀት የተሰጣቸው ሲሆን ከነዚሁ መካከል ስምንቱ አስሩንም የትምህርት አይነት “A” ያስመዘገቡ ናቸው፡፡

በዕውቅና ዝግጅቱ ላይ የተገኙት #የጅማ_ዩኒቨርሲቲ ፕሬዘደንት ዶ/ር ጀማል አባፊጣ ባስተላለፉት መልዕክት እንደገለጹት ተማሪዎች ጠንክረው በመስራት ለወደፊቱም የበለጠ ውጤት ማስመዝገብ እንደሚችሉና ለሌሎች ተማሪዎች አርዓያ በመሆን ጓደኞቻቸውንም ለጥሩ ውጤት እንዲያበቁ፣ የምክርና የሞራል ድጋፍ እንዲያበረክቱ አሳስበዋል፡፡ አያይዘውም ተማሪዎቹን ለአመርቂ ውጤት ላበቁ መምህራን ምስጋናቸውን በማቅረብ ወደፊት ትምህርት ቤቱን በማጠናከር የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ እንደሚሰራም ጠቁመዋል፡፡

በዝጅቱ ላይ የተገኙት የዩኒቨርሲቲው አካዳሚክ ጉዳዩጭ ም/ፕሬዘደንት ዶ/ር አዱላ በቀለ በበኩላቸው የመምህራንን አቅምና ጥረት መደገፍ የትምህርት ጥራትን ከማስጠበቅ ባለፍ ውጤታማ ተማሪዎችን ለማፍራ እንደሚያስችል ጠቁመዋል፡፡ በመጨረሻም በትምህርታቸው ውጤታማ ለሆኑ ተማሪዎችና በተማሪዎቹ ለተመረጡ 3 መምህራን የዕውቅና ሽልማት ተሰጥቷል፡፡

Via Jimma University
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#JimmaUniversity

የጅማ ዩኒቨርሲቲ የስራ አመራር ቦርድ ጥቅምት 20/2012 ዓ.ም ባካሄደው ልዩ ስብሰባ ለአራት ነባር መምህራን የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ መስጠቱን ለኢፕድ በላከው መግለጫ አሳውቋል፡፡ የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ያገኙት ፕሮፌሰር ገመዳ አበበ በMolecular Medical Microbiology፣ ፕሮፌሰር ገዛኻን በሬቻ በ Applied Ecology፣ ፕሮፌሰር ሱልጣን ሱሌማን በPharmaceutical Analysis and Regulatory Affairs እና ፕሮፌሰር ዘለቀ መኮንን በMedical Parasitology ናቸው፡፡

(ኢፕድ)

@tsegabwolde @tikvahethiopia
"ከየትኛዉም ጊዜ በላይ #ወንድማዊ ትስስራችሁን አጥብቃችሁ ተረጋግታችሁ የትምህርታችሁን ጊዜ በአግባቡ እንድትጠቀሙ ቤተሰባዊ ምክራችንን እንለግሳለን!" - ጅማ ዩኒቨርሲቲ

መላዉ የጅማ የኒቨርሲቲ ማህበረሰብና ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች በወልዲያ ዩኒቨርሲቲ በተከሰተዉ ግጭት ህይወታቸዉን ላጡና የአካል እና መንፈስ ጉዳት ለደረሰበቸዉ ተማሪዎች የተሰማዉን ጥልቅ ሃዘን እየገለጸ በእነዚህ በምንሳሳላቸዉ ልጆቻችን ላይ የደረሰዉ ጉዳት በዬትኛዉም መመዘኛ ተቀባይነት የሌለዉና ሰብአዊነትን ያልተላበሰ በመሆኑ በከፍተኛ ደረጃ እናወግዛለን፡፡

ከዚህ በተጨማሪ የሚመለከታቸዉ የመንግስት አካላት ሁሉ የችግሩን አሳሳቢነት በመገንዘብ በሙሉ ሃይላቸዉ ተንቀሳቅሰዉ በዚህ አስነዋሪ ድርጊት ዉስጥ የተሳተፉ አካላት ላይ በአፋጣኝ ህጋዊ እርምጃ እንዲወስዱ አጥብቀን እንጠይቃለን፡፡

የዩኒቨርሲቲያችን ተማሪዎችም ከዬትኛዉም ጊዜ በላይ ወንድማዊ ትስስራችሁን አጥብቃችሁ ተረጋግታችሁ የትምህርታችሁን ጊዜ በአግባቡ እንድትጠቀሙ ቤተሰባዊ ምክራችንን እየለገስን የዩኒቨርሲቲዉ ማህበረሰብና የበላይ አስተዳደር አካላት ከመቼዉም ጊዜ በበለጠ ከጎናችሁ መሆናችንና እያነሳችሁ የምትገኙትን ጥያቄ ለሚመለከታቸዉ የመንግስት አካላት በማቅረብ ተገቢዉን ምላሽ እንድታገኙ የበኩላችንን ጥረት ሁሉ እንደምናደርግ ልንገልጽላችሁ እንወዳለን፡፡

ሰላም ከሁላችንም ጋር ይሁን!

#JimmaUniversity

@tsegabwolde @tikvahethiopia
"...ተማሪዎቻችንን ለመመለስ ሌትና ቀን የሐይማኖት ቦታዎችና የተማሪዎች መኖሪያ ድረስ በመግባት ከፍተኛ ስራ በመስራት ላይ እንገኛለን!" - ጅማ ዩኒቨርሲቲ

#JimmaUniversity

መልካም ምክራችሁን ለወንድምና እህቶቻችሁ በመለገስ ተማሪዎች ተረጋግተው ትምህርት እንዲጀምሩ ከፍተኛ ጥረት ለምታደርጉ የተማሪዎች ህብረት፣GDASAO ክበብ አባላት እና ቅን ልቦና ያልተለያችሁ ውድ ተማሪዎቻችን እንዲሁም አባገዳዎች፣ የሐገር ሽማግሌዎች፣ የሐይማኖት አባቶች፣ የጸጥታ አካላት፣ መምህራን እና አስተዳደር ሰራተኞች ወቅቱ የሚፈልገውን በማድረግ ላይ ስለሆናችሁ ምስጋና ይገባችኋል፡፡ ጅማ ዩኒቨርሲቲም በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች የደረሱትን የሞት፣ የአካልና የስነልቦና ጉዳቶች በከፍተኛ ደረጃ እያወገዝን የተሰማንን ጥልቅ ሀዘን ስንገልጽ በርካታ አስተዋይ ልቦና ያላቸው ሰዎች አጠገባችን በመሰለፋቸው እስካሁኗ ሰዓት ድረስ ተማሪዎቻችን ለመመለስ ሌትና ቀን የሐይማኖት ቦታዎችና የተማሪዎች መኖሪያ ድረስ በመግባት ከፍተኛ ስራ በመስራት ላይ እንገኛለን፡፡

ውድ ተማሪዎቻችን በተከታታይ ሲሰሩ የነበሩ ስራዎች እየተጠናቀቁ ስለሆነ በቅርቡ ትምህርት የሚጀመር መሆኑን አውቃችሁ በትዕግስት እንድትጠባበቁ እናሳውቃለን!

(ጅማ ዩኒቨርሲቲ)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#JimmaUniversity

ጅማ ዩኒቨርሲቲ በዛሬው ዕለት ጠዋት ላይ ከሁሉም የተማሪዎች አገልግሎትና የጥበቃና ደህንነት ስራ ከፍሎች ጋር ውይይት ያካሔደ መሆኑን ገልጿል። በከሰዓቱ ክፍል ጊዜ ደግሞ በዩኒቨርሲቲው ውስጥ ከሚገኙ አጠቃላይ አስተዳደር ሰራተኞች ጋር ውጤታማ ውይይት አካሂጃለሁ ብሏል፡፡

በነገው ዕለት (ህዳር 10) ጠዋት ላይ ውይይቱ ቀጥሎ ከሁሉም የዩኒቨርሲቲው መምህራን ጋር በጉዳዩ ላይ ውይይት ይደረጋል ብሏል፡፡ የውይይቶቹ ዋና ዓላማ ለተፈጠረው ችግር ዕልባት ለመስጠት የድርጊት መርሐ-ግብር ለመንደፍ የሚያስችሉ ግብዓቶች መሰብሰብ ሲሆን በዚሁ መሰረት በቀጣይ ሰላምን ለማስፈንና የመማር ማስተማር ሒደቱን ለማስቀጠል የሚያስችሉ ሰራዎች እንደሚሰሩ ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።

(ጅማ ዩኒቨርሲቲ)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#JimmaUniversity

የጅማ ዩኒቨርሲቲ ሴኔት ዛሬ በ11/03/2012 ባደረገው ሁለተኛው አስቸኳይ ስብሰባ አሁናዊ ሁኔታውን በመገምገም ትምህርት ለማስጀመር አስሸኳይ ሁኔታዎች በመፈጠራቸው ከሰኞ 15/03/2012 ጀምሮ ተማሪዎች ትምህርት እንዲጀምሩ ወስኗል።

ሁሉም የቅድመ ምረቃ ተማሪዎች ከአርብ ህዳር 12 እስከ 14/ 2012 ዓ/ም ድረስ በየካምፓሳቸው "ዳግም ምዝገባ" በማካሄድ ሰኞ 15/03/2012 ትምህርት እንዲጀምሩ አሳስቧል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#JimmaUniversity

በጅማ ዩኒቨርሲቲ ጤና ኢንስቲትዩት ሶስቱም ፋካሊቲዎች እና በሆስፒታሉ በማገልገል ላይ ያሉ የአካዳሚክም ሆነ የሆስፒታል ሰራተኞች የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል ለሚደረገው ጥረት በሙሉ አቅማቸው እንዲሳተፉ ተወሰነ።

ሁሉም የኢንስቲትዩቱ ሰራተኞች የኢንስቲትዩቱ አመራር እና የኮሮና ቫይረስ መከላከል ግብረ ኃይል በሚመድባቸው የስራ ቦታ ላይ ይህ ችግር እስኪያልፍ እንዲሰሩ ተወስኗል። ሁሉም ሰራተኛ ለሚደረግለት ጥሪ አፋጣኝ ምላሽ መስጠት ስለሚጠበቅበት እንዲዘጋጅ መልዕክት ተላልፏል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#JimmaUniversity

በትግራይ ክልል የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ወረርሽኝን በመከላከል ስራ ህዝባቸውን ሲያገለግሉ በኮሮና ቫይረስ ተይዘው ህይወታቸው ላለፈው ዶ/ር ፍሳሃየ አለምሰገድ ትላንት በጅማ ዩኒቨርሲቲ የመታሰቢያና የሻማ ማብራት ስነ ስርዓት ተካሂዷል።

ለዶክተር ፍስሃየ አለምሰገድ በተዘጋጀው በዚሁ የመታሰቢያ ስነ ስርዓት የኢፌዴሪ ጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ በzoom ንግግር አድርገዋል። ከዚህ በተጨማሪም እናቱም በzoom ንግግር ማድረጋቸውን የዶክተር ፍሳሃየ የቅርብ ወዳጅ አሳውቀውናል።

በነገራችን ላይ ዶክተር ፍሳሃየ አለምሰገድ በጅማ ዩኒቨርሲቲ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በመምህርነት ፣ በተመራማሪነትና በሙያ እማካሪነት ከ1994 ዓ/ም እስከ 2011 ዓ/ም አገልግለዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopiaB
የተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎቻቸውን እያስመረቁ ይገኛሉ !

#WollegaUniversity

ወለጋ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን 3ሺህ 398 ተማሪዎችን ዛሬ በወለጋ ስታዲየም እያስመረቀ ነው።

የዩኒቨርሲቲው እያስመረቃቸው ካሉት ተማሪዎች የመጀመሪያ ዲግሪ 3013፣ በሁለተኛ ዲግሪ 344፣ በህክምና ዶክትሪት 40 እና የአካዳሚክ ዶክተር በአጠቃላይ 3 ሺህ 398 ናቸው።

#KebridharUniversity

ቀብሪ ደሀር ዩኒቨርሲቲ ለመጀመሪያ ጊዜ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን 612 ተማሪዎቹን እያስመረቀ ነው። ለዚሁ ስነስርዓት የክልሉ ፕሬዜዳንት አቶ ሙስጠፌ ሙሁመድ እና የፌዴራል እንዲሁም የክልሉ ባለስልጣናት ትላንት ወደቀብሪድሃር መጓዛቸው ይታወቃል።

#JimmaUniversity

ጅማ ዩኒቨርስቲ በ2ተኛ ዙር በተለያዩ የትምህርት መስኮች በመጀመሪያ፣ በሁለተኛና ሶስተኛ ዲግሪ ያሠለጠናቸውን 4ሺህ 338 ተማሪዎችን እያስመረቀ ነው።

ከተመራቂዎቹ መካከል 3,950 በመጀመሪያ ዲግሪ ሲሆን ከእነዚህም ውስጥ 1 ሺህ 530 ሴቶች ናቸው። በ2ተኛ ዲግሪ ደግሞ 45 ሴቶች የሚገኙበት 354 ተማሪዎች ተመርቀዋል፡፡ 3 ተማሪዎች በ3ተኛ ዲግሪ እና 4 ተማሪዎች ደግሞ የ 'ሰብ ስፔሻሊቲ' ተመራቂ ይገኙበታል፡፡

#ArsiUniversity

አርሲ ዩኒቨርሲቲ በህክምና ስፔሻሊቲ ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የነበሩ 24 ሰልጣኞቹን በመጀመሪያ ዙር አስመርቋል፡፡

#KotebeMetropolitanUniversity

ኮተቤ ሜትሮፖሊታን ዩኒቨርስቲ 2039 ተማሪዎች እያስመረቀ ነው ፤ 1 ሺህ 104 በመጀመሪያ ዲግሪ፣ 222 በ2ኛ ዲግሪና 711 በዲፕሎማ።

ምንጭ፦ ጅማ ዩኒቨርሲቲ ፣ SRTV፣ ወለጋ ዩኒቨርሲቲ ፣ኤፍ ቢሲ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
* Congratulations !

በዛሬው ዕለት ብቻ ከተለያዩት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የቆዩ ከ30,192 በላይ ተማሪዎች ተመርቀዋል።

የትኞቹ ዩኒቨርሲቲዎች ምን ያህል ተማሪ ? በምን ደረጃ እና የትምህርት ዘረፍ አስመረቁ ? ለጥያቄዎቹ መልስ ይህን አጭር ቁጥራዊ መረጃ አስቀምጠናል።

#HawassaUniversity

- አጠቃላይ 6 ሺህ 793 ተማሪዎችን አስመርቋል።
- ከጠቅላላ ተመራቂዎቹ 2 ሺህ 158ቱ ወይም 32 በመቶ ሴቶች ናቸው።
- ተመራቂዎቹ በመጀመሪያ፣ በ2ኛ እና በ3ኛ ዲግሪ በመደበኛና ተከታታይ መርሃ ግብሮች ትምህርታቸውን ተከታትለው ያጠናቀቁ ናቸው።

#BahirdarUniversity

- አጠቃላይ 5 ሺህ 586 ተማሪዎች አስመርቋል።
- ከተመራቂዎቹ 1 ሺህ 714ቱ ሴቶች ናቸው።
- በመጀመሪያ፣ በ2ኛ እና በ3ኛ ዲግሪ ትምህርታቸውን ተከታትለው ያጠናሰቁ ናቸው።

#JimmaUniversity

- አጠቃላይ 696 ተማሪዎች አሰመርቋል።
- 450 ወንድ እና 246 ሴት ተማሪዎች ናቸው።
- በቅድመ ምረቃና በድህረ ምረቃ መርሃ ግብሮች ትምህርታቸውን የተከታተሉ ናቸው።
- ከተመራቂዎቹ 252 ተማሪዎች በአጠቃላይ ሕክምናና በጥርስ ሕክምና የሰለጠኑ ናቸው።
- ጅማ ዩኒቨርሲቲ በሶማሊላንድ ሀርጌሳ ካምፓሱ በ 'ኒውትሬሽን' የትምህርት ዘርፍ ያስተማራቸውን 19 የ2ኛ ዲግሪ ተማሪዎችንም አስመርቋል።

#AdamaScience_and_TechnologyUniversity (ASTU)

- አጠቃላይ 1 ሺህ 298 ተማሪዎች አስመርቋል።
- ሰባቱ በሦሥተኛ ዲግሪ (ፒኤችዲ) ተመራቂዎች ናቸው።
- 215ቱ በሁለተኛ ዲግሪ የተመረቁ ናቸው።
- 1 ሺህ 76 ተማሪዎች በመጀመረያ ዲግሪ የተመረቁ ናቸው።

#MettuUniversity

- አጠቃላይ 2 ሺህ 262 ተማሪዎች አስመርቋል።
- 116ቱ በሁለተኛ ዲግሪ ትምህርታቸውን የተከታተሉ ናቸው።
- ተመራቂዎቹ በመደበኛ እና በተከታታይ መርሃ ግብሮች በመቱ እና በበደሌ ካምፓሶች ትምህርታቸውን የተከታተሉ ናቸው።

#ArsiUniversity

- አጠቃላይ 831 ተማሪዎችን አስመርቋል።
- በበቆጂ ካምፓስ የሰለጠኑ ናቸው።
- ተመራቂዎቹ በማህበራዊ ሳይንስ ዘርፍ በመደበኛና በተከታታይ መርሃ ግብሮች ትምህርታቸውን የተከታተሉ ናቸው።
- በመጀመሪያ እና በ2ኛ ዲግሪ ከተመረቁት መካከል 392ቱ ሴቶች ናቸው።

#AmboUniversity

- አጠቃላይ 4 ሺህ 524 ተማሪዎች አስመርቋል።
- በመጀመሪያ እና በሁለተኛ ዲግሪ የሰለጠኑ ናቸው።
- ከተመራቂዎቹ 1 ሺህ 980ዎቹ ሴት ተማሪዎች ናቸው።
- ከጠቅላላ ተመራቂዎቹ 450 የሚሆኑት የሁለተኛ ዲግሪ ተመራቂ ሲሆኑ 11 የደቡብ ሱዳን ስደተኛ ተማሪዎች ይገኙበታል።

#JigjigaUniversity

- አጠቃላይ 1 ሺህ 202 ተማሪዎችን አስመርቋል።
- ከጠቅላላ ተመራቂዎቹ 336ቱ ሴት ተማሪዎች ናቸው።
- 233ቱ በሁለተኛ ዲግሪ ትምህርታቸውን ያጠናቀቁ ሲሆን ቀሪዎቹ 969ኙ በመጀመሪያ ዲግሪ ትምህርታቸውን የተከታተሉ ናቸው።

* ከግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መካከል #AdmasUniversity

- አጠቃላይ ከ10 ሺህ በላይ ተማሪዎችን አስመርቋል።
- ከተመራቂዎቹ 67 በመቶ ሴቶች ናቸው።
- በቴክኒክና ሙያ፣ በመጀመሪያ ዲግሪ እና 2ኛ ድግሪ በቀንና በማታ ትምህርታቸውን የተከታተሉ ናቸው።
- ከተመራቂዎቹ መካከል 1 ሺህ 532ቱ በ2ኛ ዲግሪ የተመረቁ ናቸው።

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጉዳዮችን በ @tikvahuniversity ተከታተሉ።

@tikvahethiopia