TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.7K photos
1.44K videos
207 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ቡራዩ‼️

መርማሪ ፖሊስና አቃቢ ህግ በቡራዩና አካባቢው በተፈፀው የሽብር ድርጊት ተጠርጥረው በተያዙ 32 ግለሰቦች ላይ ፍርድ ቤቱ የፈቀደው ዋስታና እንዲነሳ #ይግባኝ ጠይቀዋል።

የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ አራተኛ የወንጀል ችሎት በዛሬ ውሎው በቡራዩ እና አካባቢው በተፈፀመው የሽብር ወንጀል ተጠርጥረው የተያዙ 33 ግለሰቦችን ጉዳይ ተመልክቷል።

ፍርድ ቤቱ ከዚህ ቀደም መርማሪ ፖሊስ በተጠርጣሪዎች ላይ ያቀረበው የሰውና የሰነድ ማስረጃ ለአቃቢ ህግ ቀርቦ ተገቢነቱ እንዲጣራ መጠየቁ ይታወሳል።

ይሁን እንጂ መርማሪ ፖሊስ በወቅቱ ጉዳት የደረሰባቸውን ሰዎች የሙሉ ምስክርነት ቃል ለመቀበል እንዲሁም ተጎጅዎችን በአካል ማነጋገር
አስፈላጊ መሆኑን ለፍርድ ቤቱ በማስረዳት፥ ለዚህም 28 ቀን ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ እንዲፈቀድለት ጠይቋል።

የተጠርጣሪ ጠበቆች በበኩላቸው ባለፈው ችሎት መርማሪ ፖሊስ ጉዳዩን አጣርቶ ለአቃቢ ህግ እንዲያቀርብ ቢያዝዝም፥ ፖሊስ ግን ይህን ማስፈፀም አለመቻሉን ለፍርድ ቤቱ አስረድተዋል።

በተጨማሪም መርማሪ ፖሊስ እያቀረባቸው ያለው ሀሳቦች ተደጋጋሚና የተከሳሾችን የዋስትና መበት የሚጋፋ በመሆኑ፥ ፖሊስ የጠየቀው ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ውድቅ እንዲደረግ ፍርድ ቤቱን ጠይቀዋል።

ከዚህ ባለፈም ፍርድ ቤቱ የተከሳሾችን መዝገብ በመዝጋት በነፃ እንዲያሰናብታቸው ወይም ደግሞ የዋስትና መብታቸው እንዲጠበቅ ፍርድ
ቤቱን ጠይቀዋል።

የግራ ቀኙን ክርክር ያዳመጠው ፍርድ ቤቱም በዛሬው ዕለት ቀጠሮ የተያዘው መርማሪ ፖሊስ በተጠርጣሪዎች ላይ ያገኘውን ማስረጃ ሪፖርት ለማድመጥ አለመሆኑን ገልጿል።

ከዚህ ባለፈም አቃቢ ህግ የተጨማሪ ጊዜውን አስፈላጊነት በፅሁፍም ሆነ በቃል መስረዳት ይጠበቅበታል ፤ ይሁን እንጅ አቃቢ ህጉ ይህንን ማድረግ አለመቻሉን አሳውቋል።

ስለሆነም መርማሪ ፖሊስ የጠየቀው ተጨማሪ የ28 ቀን የምርመራ ጊዜ ተገቢ አለመሆኑን በመግለፅ፥ ሁሉም ተጠርጣሪዎች የ 15 ሺህ ብር ዋስትና በማቅረብ #እንዲፈቱ ትዕዛዛ አስተላፏል።

በመጨረሻም መርማሪ ፖሊስና ዓቃቢ ህግ ፍርድ ቤቱ ለተከሳሾች የፈቀደው ዋስታና እንዲነሳ የጠየቁ ሲሆን፥ ፍርድ ቤቱም መርማሪ ፖሊስና ዓቃቢ ህግ በፅሁፍ ያቀረቡትን ይግባኝ መቀበሉ ተገልጿል።

ምንጭ፦ fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia