TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.8K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Sudan

ሱዳን በጋረጠችው የፀጥታ ችግር ሳቢያ በምዕራብ አርማጭሆ አንድ ጋሻ የሚጠጋ የእርሻ መሬት ለ1 ዓመት ያህል ሳይታረስ መቆየቱ ተገልጿል።

የሱዳን ኃይሎች የኢትዮጵያን ድንበር ተሻግረው መግባት ከጀመሩበት ጊዜ አንስቶ ነው መሬቱ ያልታረሰው።

የወረዳው ግብርና ጽ/ቤት ም/ል ኃላፊ ደሴ ዘውዓለ ለአሐዱ በሰጡት ቃል፤ በምዕራብ አርማጭሆ ኢንቨስትመንት ቀጠና በስፋት ጥጥ፣ አኩሪ አተር፣ ማሽላና ሰሊጥ ይመረታል ብለዋን።

በ2013/14 የምርት ዘመን በአካባቢው የእርሻ ስራ ማከናወን ባለመቻሉ በርካታ ገንዘብ ስለመታጣቱን አንስተዋል፡፡

በተመሳሳይ በዞኑ መተማ ወረዳ በሱዳን ኃይሎች ሳቢያ በ2013 ዓ.ም ከእርሻ ስራ የወጡ 76 ባለሃብቶች መኖራቸውን የወረዳው ግብርና ጽ/ቤት ኃላፊ ምህረቱፍቃድ ገላው ተናግረዋል፡፡

የሰሞኑን የጸጥታ መደፍረስ ተከትሎ ግን ከእርሻ ስራቸው የተፈናቀሉ ባለሃብቶች አለመኖራቸውን አስረድተዋል፡፡

በወረዳው ደለሎ በሚባለው የኢንቨስትመንት ቦታ ከሱዳን የሚተኮሰው መሳሪያ በእርሻ ስራ ላይ #ከስጋት ባለፈ ያስከተለው ጉዳት እንደሌለ ገልፀዋል።

የሚተኮሰው መሳሪያ የሚያርፈው ከኢንቨስትመንት ስፍረው በ500 ሜትር ርቀት ላይ መሆኑን ነው የጠቀሱት፡፡

በመተማ ወረዳ በ3 የኢንቨስትመንት ቀጣና 256 ባለሃበቶች ተሰማርተው የቆዩ ቢሆንም ሱዳን ገፍታ በመምጣቷ ሳቢያ በአሁኑ ወቅት 76ቱ ከስራ ውጭ ናቸው፡፡

የሱዳን ኃይሎች የኢትዮጵያን ድንበር ጥሰው ከገቡበት ዕለት አንስቶ እስካሁን በምዕራብ ጎንደር ዞን 276 የሚደርሱ ባለሃብቶች ከስራቸው ተፈናቅለዋል።

መንግስት የጉዳዩን አሳሳቢነት በመመልከት የተለያዩ ዲፕሎማሲያዊ ስራዎችን በመስራት የተስተጓጎሉ የእርሻ ስራዎች እንዲቀጥሉ ማድረግ እንደሚገባው የወረዳው ባለስልጣናት ጥሪ ማቀረባቸውን አሐዱ ቲቪ ዘግቧል።

@tikvahethiopia