TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.3K photos
1.47K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ቅጥር

የአዲስ አበባ አስተዳደር የጤና ቢሮ በስሩ ላሉት ተቋማት ሰራተኞችን አወዳድሮ በቋሚ ቅጥር ለማሰራት ይፈልጋል።

መስፈርቶቹን የምታሟሉ ከ8/06/2014 ዓ/ም ጀምሮ ባሉት 10 የስራ ቀናት መመዝገብ ትችላላችሁ ተብሏል።

ሁሉም የስራ መደብ የስራ ልምድ #ዜሮ ዓመት ነው።

ከፍተኛ ባለሞያ የተፈለገበት የስራ መደብ - ጠቅላላ ሀኪም ሲሆን በመጀመሪያ ዲግሪ በ9,056 ብር ደመወዝ አጠቃላይ 150 ሰው ይፈለጋል።

በተጨማሪ በ ዘO (ጤና መኮንን) በተመሳሳይ የመጀመሪያ ዲግሪ በ7,071 ብር ደመወዝ 50 ሰው ይፈለጋል።

እንዲሁም በደረጃ 4 ጤና ኤክስቴንሽን (ዲፕሎማ / ሌቭል 4) በ5,358 ብር ደመወዝ ፣ በደረጃ 4 ነርስ (ዲፕሎማ / ሌቭል 4) በ4,609 ደመወዝ ፣ በሚድዋይፈሪ ፕሮፌሽናል (የመጀመሪያ ዲግሪ) በ6,193 ብር ደመወዝ ፣ በፋርማሲ ፕሮፌሽናል (የመጀመሪያ ዲግሪ) በ7,071 ብር ደመወዝ በተጠቀሱት እያንዳንዱ የስራ መደቦች 30 ሰዎች ይፈለጋሉ።

በሌሎችም የስራ መደቦች ላይ ያሉ ቦታዎችን ፣ የደመወዝ መጠን ፣ የትምህርት ደረጃ ከላይ በተያያዘው ምስል ይመልከቱ።

@tikvahethiopia
#Russia

የሩሲያ ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን ከመካከለኛው ምሥራቅ የሚመጡ እና ፍቃደኛ የሆኑ ሰዎች ለሩሲያ መዋጋት ይችላሉ አሉ።

ፑቲን ፤ " ገንዘብ ሳይከፈላቸው ለሩሲያ መዋጋት የሚፈልጉ ሰዎች አሉ " ካሉ በኋላ፤ " እነዚህን ሰዎች ወደ ጦር ግንባር በመላክ ማድረግ የሚፈልጉትን መተባበር አለብን " ብለዋል።

የሩሲያ መከላከያ ሚኒስትር ሰርጌይ ሾይጉ ከመካከለኛው ምሥራቅ ተነስተው በዶንባስ ግዛት ከሩሲያ ጦር ጎን መሰለፍ የሚፈልጉ 16 ሺህ ሰዎች አሉ ሲሉ ለፑቲን ተናግረዋል።

ፕሬዝዳንቱ ለፀጥታ ምክር ቤታቸው ምዕራባውያን " በግልጽ ዓለም አቀፍ ሕጎችን በመተላለፍ ተዋጊዎችን ለዩክሬን እየቀጠሩ ነው " ሲሉ መናገራቸውን ቢቢሲ ሮይተርስን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል።

ከዚህ ቀደም ዩክሬን በ "አፍሪካ" በተለያዩ ሀገራት በሚገኙት ኤምባሲዎቿ በኩል በ #ቅጥር ለዩክሬን የሚዋጉ ሰዎችን እንደምትፈልግ ማስታወቋ በኃላ ይህ ጥሪው ቁጣን ፈጥሮ እንደነበር አይዘነጋም።

@tikvahethiopia