TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.4K photos
1.47K videos
209 files
4.04K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ቀዊተ ሸኖ ⬇️

ከነቀምት ወደ አርጆ በመጓዝ ላይ በነበረ ሚኒባስ ላይ በደረሰ አደጋ የ10 ሰዎች #ህይወት አለፈ።

በትናንትናው ዕለት በምስራቅ ወለጋ #ከነቀምት ወደ #አርጆ ከተማ ሲጓዝ በነበረ የህዝብ ማመላለሻ ሚኒ ባስ ላይ #ቀዊተ_ሸኖ በተባለ ቦታ ላይ በደረሰ አደጋ የ10 ተሳፋሪዎች ህይወት ወዲያውኑ ሲያልፍ ሌሎች 3 ተሳፋሪዎች ላይ ከፍተኛ የአካል ጉዳት ደርሷል።

ሚኒባሱ ኮድ 3 80 85 ኢት 4 ከሆነ ተሳቢ ካለው ሲኖትራክ ጋር የመታጠፊያ ከርብ ላይ የተጋጨ ሲሆን፥ የአደጋውን መንስኤ ፖሊስ እያጣራ እንደሚገኝ የምስራቅ ወለጋ የትራፊክ ደህንነት ሃላፊ ኢንስፔክተር ፍሮምሳ ሰለሞን ለFBC ተናግረዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update አዲስ አበባ⬇️

በአዲስ አበባ ቦሌ ክፍለ ከተማ በተለምዶ ወሎ ሰፈር ተብሎ በሚጠራው አካባቢ አንድ የፌደራል ፖሊስ አባል #በመጠጥ ሀይል ተገፋፍቶ በባልደረቦቹ ላይ #ጥቃት መፈፀሙ ተነግሯል።

የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጀነራል ዘይኑ ጀማል ለfbc እንደተናገሩት፥ የፌደራል ፖሊስ አባሉ በባልደረቦቹ ላይ በፈፀመው ጥቃትም ሁለት የፌደራል ፖሊስ አባላት #ህይወት አልፏል።

ፖሊስ ጥቃቱን ለማስቆም በወሰደው እርምጃም ጥቃቱን የፈፀመው የፌደራል ፖሊስ አባል ህይወቱ ማለፉን ኮሚሽነር ጀነራል ዘይኑ ጀማል አስታውቀዋል።

በአሁኑ ወቅም በስፍራው ተስተጓጉሎ የነበረው የትራፊክ እና ሌሎች እንቅስቃሴዎች ወደ መደበኛ ሁኔታቸው መመለሳቸውን ገልፀዋል።

ምንጭ፦ ፋና ብሮድካስቲንግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update አላማጣ‼️

በአላማጣ የማንነት ጥያቄ ባነሱ ወጣቶችና በጸጥታ ኃይሎች መካከል በተፈጠረ ግጭት የሰዎች #ህይወት ጠፍቷል።

ትናንት በአላማጣ ከተማ በታጠቀ የልዩ ኃይልና በወጣቶች መካከል በተፈጠረው ግጭት አምስት ግለሰቦች #በጥይት ተመትተው መሞታቸው የዓይን እማኞች ተናግረዋል።

ከጥቂት ወራት በፊት ጀምሮ የአላማጣ ከተማ ወጣቶች የማንነት ጥያቄዎችን እንደሚያነሱ የከተማው ነዋሪዎች ይናገራሉ።

አቶ ዝናቡ ማርፌ የአላማጣ ከተማ ነዋሪ ሲሆኑ ትናንት በከተማዋ በተካሄደው ሰልፍ ላይ ተሳታፊ ነበሩ። በስልፉ ወቅት ድብደባ ተፈጽሞብኛል የሚሉት አቶ ዝናቡ ''ካለፉት ሦስት ወራት ወዲህ የከተማዋ ወጣቶች ወረቀት በመበተን ሰላማዊ ሰልፎችን ለማካሄድ ጥረቶችን ያደርጉ ነበር። ለውጡን እንደግፋለን የሚሉ ከነቴራዎችን ያደርጋሉ በእነዚህ ተግባሮቻቸውም ይታሰራሉ ከዚያም ይፈታሉ። የትናንቱ ግን አስከፊ ነበር'' በማለት የትናንቱን ክስተት ያብራራሉ።

ትናንት የእጅ ኳስ ሜዳ ላይ በተጀመረ የተቃውሞ ሰልፍ ለበርካቶች የህይወት መጥፋት እና የአካል ጉዳት ምክንያት ሆኗል። የከተማዋ ነዋሪዎች እንደሚሉት ከሆነ መሰብሰብ አትችሉም የተባሉት የከተማዋ ወጣቶች ከፀጥታ ኃይሎች ጋር #ተጋጭተዋል

ሌላው ለደህንነቱ ሲል ስሙ እንዲጠቀስ ያልፈለገ የከተማዋ ነዋሪ በትናንቱ ግጭት በጥይት ታፋው ላይ ተመትቷል። ''በጥይት የተመታን ልጅ ለማንሳት ስሄድ እኔም ተመታሁኝ'' ይላል። ''በጥይት መመታቴን እንኳ አልታወቀኝም ነበር። አጠገቤ ያሉ ሰዎች ናቸው ስሜን እየጠሩ በጥይት መመታቴን የነገሩኝ። አንገቴ ላይ ደም ስመለከት አንገቴን የተመታሁ መስሎኝ ነበር። አንገቴ ላይ የነበረው ደም ግን የሟቹ ልጅ ነበር'' በማለት ሁኔታውን ያስረዳል።

ይህ ወጣት ትናንት ወደ የእጅ ኳስ ሜዳው ተሰባሰበው በሄዱበት ወቅት እንዲበተኑ በመደረጉ በተፈጠረ ግጭት ጉዳቱ መድረሱን ያስረዳል።

''የሆነ ነገር ያደርጉኛል ብዬ ስለሰጋሁ ወደ የግል ሕክምና እንጂ ሆስፒታል አልሄድኩም። አሁንም የምገኘው በመኖሪያ ቤቴ ነው'' ይላል። የአላማጣ ከተማ ነዋሪው አቶ ዝናቡ እንደሚሉት የሃገር መከላከያ ሠራዊት አባላት በቦታው ቢደርሱም የዜጎችን ደህንነት ማስጠበቅ ግን ተስኗቸዋል ይላሉ። ''የልዩ ኃይሉ የሚፈጽመውን ጥቃት እንዲያስቆሙ ስንጠይቃቸው 'የተዘጋውን መንገድ ብቻ ነው የምናስከፍተው' አሉን'' ይላሉ።

የተጎጂዎች ቁጥር ከአቶ ዝናቡ ማርፌ እና ከሌሎች የከተማዋ ነዋሪዎች እንደተሰማው ከሆነ 5 ሰዎች #ተገድለዋል 15 የሚሆኑ ደግሞ ከባድ እና ቀላል ጉዳት ደርሶባቸዋል። እንዲሁም ከ50 ባለይ ሰዎች ለእስር ተዳርገዋል።

የማንነት አስመላሽ ኮሚቴ ሰብሳቢ የሆኑት አቶ አግዜ ህዳሩ በበኩላቸው የሟቾችን ቁጥር 9 የተጎጂዎችን ደግሞ 16 ያደርሱታል።

የትግራይ ክልል ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ደግሞ በፌስቡክ ገጹ ላይ በአላማጣ ከተማ በማንነት ስም በሚንቀሳቀሱ አካላት እና በፀጥታ ኃይሎች መካከል በተከሰተ ግጭት የሦስት ሰዎች ህይወት አልፏል ብሏል።

ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ የአላማጣ ሆስፒታል ባልደረባ ለቢቢሲ እንደተናገሩት ከሆነ በትናንቱ ግጭት ጉዳት የደረሰባቸው 25 ሰዎች በሆስፒታሉ የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው እንደሆነ እና አንድ ሰው ደግሞ ባጋጠመው ከፍተኛ ጉዳት ለተጨማሪ ህክምና ወደ መቀሌ መላኩን ነግረውናል።

አላማጣ ዛሬ ረፋድ አቶ ዝናቡ እና ሌላ የከተማዋ ነዋሪ እንደሚሉት ከሆነ ዛሬ እስከ ረፋድ ድረስ አላማጣ ውስጥ መንገድ ዝግ ነበር። የሃገር መከላከያ ሠራዊት አባላት መንገድ ለማስከፍት ጥረት ሲያደርጉ ውለዋል።

ትናንት ከተገደሉት 5 ሰዎች የሁለቱ ሰኞ ጠዋት አላማጣ እየሱስ ቤተ ክርስቲያን የቀብር ሥነ-ሥርዓታቸው ተፈጽሟል። ''የሟቾች ሰውነት በከፍተኛ ሁኔታ የተበጣጠሰ ስለሆነ በጠዋት ነው የተቀበሩት'' ሲሉ አቶ ዝናቡ ተናግረዋል።

ከሟቾቹ መካከል የሦስቱ ግለሰቦች አስክሬን ከአላማጣ ውጪ ወደ ሆኑ ቦታዎች የቀብር ሥነ-ሥርዓታቸው ሊፈጸም አስክሬናቸው ወደ ትውልድ ስፍራቸው መላኩን ከከተማዋ ነዋሪዎች ሰምተናል።

የማንነት አስመላሽ ኮሚቴ ሰብሳቢ የሆኑት አቶ አግዜ ህዳሩ በበኩላቸው የአካባቢው ህዝብ ላለፉት ሦስት እና አራት ወራት የማንነት ጥያቄዎችን በሰላማዊ መንገድ ለማቅረብ ጥረት ሲያደርግ ቆይቷል ያሉ ሲሆን፤ ''የትግራይ ክልል መንግሥት ግን ከፍተኛ ቁጥር ያለውን ልዩ ኃይል ወደ አካባቢው በማስገባት የማንነት ጥያቄውን ለማዳፈን ወጣቶችን በማሸማቀቅ ከፍተኛ የሆነ የሥነ-ልቦና ጫና እያደረገ ነው'' ይላሉ።

አቶ አግዜ ጨምረውም ራያ አዘቦ፣ ራያ አላማጣ እና ኦፍላ የማንነት ጥያቄ የሚነሳባቸው ወረዳዎች ናቸው ብለዋል።
የትግራይ ክልላዊ መንግሥት ኮሚኬሽን ጉዳዮች ቢሮ በበኩሉ በፌስቡክ ገጹ ላይ ''የህዝብን የማንነት ጥያቄ በማስመሰል ሌላ የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት እየተደረገ ያለው ሩጫ በማንኛውም መመዘኛ ተቀባይነት የሌለው ተግባር ነው።'' በማለት ተግባሩ ኮንኗል። ''ይህ ሳያንስ የዜጎች ሰላም፣ ፀጥታና ደህንነት ለመጠበቅ ከተሰማራው የፀጥታ መዋቅር ጋር መጋጨትና አነሳስቶ እርምጃ እንዲውስድ መግፋት ደግሞ በፍፁም መደገም የሌለበት ተግባር ነው'' በማለት የክልሉ የኮሚኒኬሽን ቢሮ በመግለጫው አትቷል። መግለጫው በዚህ ተግባር ላይ በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ የተሳተፉትን አካላት በቸልታ አላልፋቸውም ብሏል።

አላማጣ ወረዳን ወክለው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል የሆኑት አቶ ረዳኢ ዝናቡ በበኩላቸው የወረዳው ነዋሪ በርካታ የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄ አለበት ካሉ በኋላ "በመልካም አስተዳደር እጦት ምክንያት እኛ ማንነታችን ራያ ነው፤ ስለዚህም በራሳችን ሰዎች መተዳደርና መዳኘት አለብን ማለት የጀመረ የህብረተሰብ ክፍል አለ" ብለዋል።

በትግራይ ምክር ቤት ውስጥ የወረዳው ህዝብ ተወካይ የሆኑት ወይዘሮ ጃኖ ንጉሰ ደግሞ "እኛ ትግራዋይም አማራም አይደለንም፤ እኛ ራያ ነን የሚሉም አሉ። ይህ ተግባር የፍትህ እና የመልካም አስተዳደር ጥያቄ ያለበትን የህብረተሰብ ክፍል ለማጋጨት እየተደረገ ያለ ነገር ነው። እንደዚህ አይነት ጥያቄ በህጋዊ መንገድ መጠየቅ አለበት።" ብለዋል።

ምንጭ፦ BBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ደኢህዴን‼️

የደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ የ5ኛ ዙር 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 8ኛ መደበኛ ጉባኤን አስመልክተው መግለጫ ተሰጥተዋል፡፡

የደቡብ ብሔሮች፣ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል ምክር ቤት 5ኛ ዙር 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 8ኛ መደበኛ ጉባኤ ከጥቅምት 20 እስከ 24/2011 ዓ.ም ድረስ ያካሂዳል፡፡

ጉባዔውን አስመልክተው የክልሉ ምክር ቤት ዋና አፈ-ጉባኤ የተከበሩ ወ/ሮ #ህይወት_ኃይሉ ዛሬ ለጋዜጠኞች መግለጫ ሲሰጡ በሐምሌ ወር በተደረገው መደበኛ ጉባዔ ውይይት ሊደረግባቸው የሚገቡ አጀንዳዎች ባለፉት ወራት በክልሉ በነበረው የጸጥታ ችግር ምክንያት ውይይት እንዳልተደረገባቸው ጠቁመው በአሁኑ ጉባዔ ውይይት እንደሚደረግባቸው ገልጸዋል፡፡

አፈ ጉባዔዋ አያይዘውም አሁን በክልሉ አንጻራዊ #ሰላም መስፈኑን ተናግረው በየአካባቢው የሚፈጠሩ ችግሮችን ለመፍታት የህዝብ ለህዝብ ትስስርን ለማጠናከር የምክር ቤቱ አባላትሚና የጎላ እንደሆነም አብራርተዋል፡፡

ከጥቅምት 20 እስከ 24/2011 ዓ.ም ምክር ቤቱ በሚያካሂደው ጉባዔ የሚወያይባቸው አጀንዳዎችም፡-

1ኛ የደቡብ ብሔሮች፣ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል ምክር ቤት 5ኛ ዙር 3ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 7ኛ መደበኛ ጉባዔ ረቂቅ ቃለ ጉባኤ መርምሮ ማጽደቅ፣

2. የደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል ምክር ቤት ጽ/ቤት የ2010 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርትና የ2011 በጀት ዓመት ጠቋሚ ዕቅድ፣

3. የክልል መንግስት የ2ዐ10 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርትና የ2ዐ11 በጀት ዓመት ዕቅድ፣

5. የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የ2ዐ10 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርትና የ2011 በጀት ዓመት ዕቅድ፣

6. የክልሉ ዋና ኦዲተር መ/ቤት የ2ዐ10 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርትና የ2011 በጀት ዓመት ዕቅድ፣

7. ልዩ ልዩ አዋጆች፣ ደንብና የውሳኔ ሀሳብን በተመለከተ፡-

ሀ/ የደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መ/ የመንግስት ሰራተኞች ረቂቅ አዋጅ፣
ለ/ የደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መ/ የዋና ኦዲተር መ/ቤት ማቋቋሚያ አዋጅን እንደገና
ለማሻሻል የወጣ ረቂቅ አዋጅ፣
ሐ/ የደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መ /ጠቅላይ አቃቤ ህግን ለማቋቋም የወጣ ረቂቅ አዋጅ፣
መ/ የአስፈጻሚ አካላትን ስልጣንና ተግባር እንደገና ለማቋቋም የወጣ ረቂቅ አዋጅ፣
ሠ/ በክልሉ ውስጥ ተጨማሪ የአስተዳደር እርከኖችን ለማቋቋም የቀረበ የውሳኔ ሀሳብና
ረ/ የደ/ብ/ብ/ህ/ክ/ምክር ቤት የአሰራርና የአባላት ስነ ምግባር ደንብ ለማሻሻል የወጣ ደንብ

8. የክልል ጥያቄን በተመለከተ፣

9. ሹመት እና የዳኞች ስንብት የሚሉ መሆናቸውን አሳውቀዋል፡፡

ምንጭ፦ ደኢህዴን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በቦንብ ፍንዳታ የሰው ህይወት አለፈ‼️

በደባርቅ ወረዳ በቦንብ ፍንዳታ አራት የአንድ ቤተሰብ አባላት #ህይወት አለፈ።

በሰሜን ጎንደር ዞን ደባርቅ ወረዳ በአንድ ግለሰብ መኖሪያ ቤት በህገ ወጥ መንገድ የተቀመጠ የእጅ ቦንብ ፈንድቶ አራት የአንድ ቤተሰብ አባላት ህይወት ማለፉን ፖሊስ አስታወቀ፡፡

የደባርቅ ወረዳ ፖሊስ ጽህፈት ቤት የወንጀል መረጃ ዋና የስራ ሂደት አስተባባሪ ኢንስፔክተር ግርማይ አለባቸው ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
ዛሬ እንደገለፁት አደጋው የደረሰው ጥቅምት 24 ቀን 2011ዓ.ም ከጠዋቱ 3 ሰአት ላይ በወረዳው አደባባይ ጽዩን ቀበሌ በሚገኘው መኖሪያ ቤት ውስጥ በህገ ወጥ መንገድ የተቀመጠ የእጅ ቦንቡን የቤቱ አባወራ በመነካካት ላይ እያሉ እጃቸው ላይ #በመፈንዳቱ ነው፡፡

በፍንዳታውም አባወራውና ባለቤታቸው እንዲሁም የሁለት ልጆቻቸው ህይወት ወዲያውኑ ሲያልፍ በመኖሪያ ቤቱ ውስጥ የነበሩ ሌሎች ሁለት የቤተሰብ አባላት የመቁሰል አደጋ ደርሶባቸዋል፡፡

የመቁሰል አደጋ የደረሰባቸው ግለሰቦች በደባርቅ ሆስፒታል የህክምና እርዳታ ሲደረግላቸው ቆይቶ ወደ ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታል ለከፍተኛ ህክምና መላካቸውን ዋና ኢንስፔክተሩ ተናግረዋል፡፡

ጅምላ ጨራሽ መሳሪያዎችን በቤት ውስጥ ደብቆ ማስቀመጥ ወንጀል ከመሆኑም በላይ ለአደጋ የሚያጋልጥ በመሆኑ ህብረተሰቡ ከእንደዚህ አይነት ድርጊት መቆጠብ እንዳለበትም ዋና ኢንስፔክተሩ አስገንዝበዋል፡፡

ምንጭ፦ ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጋሞ ጎፋ‼️

በጋሞ ጎፋ ዞን ሁለት ወረዳዎች የፀረ-ቢጫ ወባ ክትባት ሊሰጥ መሆኑን የአለም ጤና ደርጅት ገለፀ።

የአለም ጤና ድርጅት ተወካይ ዶክተር #ዮሐንስ_ዳምጠው በቅርቡ የቢጫ ወባ በወላይታ ዞን ኦፋ ወረዳ ተከስቶ የ10 ሰዎች #ህይወት ማለፉን
ገልፀው በሽታው ወደ አጎራባች አካባቢዎች እንዳይዛመት እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በሽታው ወደ ጋሞ ጎፋ ዞን እንዳይዛመት የወላይታ ዞን አጎራባች በሆኑት ቦረዳና ቁጫ ወረዳዎች በቅርቡ የፀረ-ቢጫ ወባ ክትባት እንደሚሰጥ ገልጸዋል፡፡

ቢጫ ወባ በአለም በገዳይነት ከሚታወቁ በሽታዎች ቁጥር አንድ መሆኑን የገለፁት ዶክተር ዮሐንስ መከላከያ ክትባቱን የወሰደ ሰው በበሽታው እንደማይጠቃ ተናግረዋል፡፡

የፀረ-ቢጫ ወባ ክትባት ዕድሜያቸው ከ ዘጠኝ ወር በላይ ለሆኑ የሚሰጥ ስለሆነ የአከባቢው ነዋሪ ክትባቱ በሚሰጥበት ወቅት ወደ ጤና ተቋማት በመሄድ እንዲከተብ የአለም ጤና ድርጅት ተወካይ ዶክተር ዮሐንስ ዳምጠው ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
አሶሳ ዩንቨርስቲ‼️

በአሶሳ ተከስቶ በነበረው #ግጭት የሦስት ተማሪዎች #ህይወት ማለፉን የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

የባለስልጣኑ ሚኒስቴር የሆኑት ዶክተር ሂሩት ወልደማሪያም ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጋር በተያያዘ ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሂደት ምን ይመስላል በሚለው ጉዳይ መግለጫ በሰጡበት ወቅት ነው ይህ የተሰማው፡፡

ዶክትር ሂሩት ባለፉት ቀናት በውስን ዩኒቨርስቲዎች ተፈጥሮ የነበሩ ግጭቶችን አስመልክቶ ስለምክንያታቸም ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

በማብራሪያቸውም አሁን ያለው ሀገራዊ ለውጥ እና ለውጡን ለማደናቀፍ ዩኒቨርስቲዎች ኢላማ መሆን፣ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥ የሚነሱ ሁከቶች ምክንያት ወይም ከግጭቶቹ በስተጀርባ ያለ ጠብ አጫሪ እንቅስቃሴዎች ምንነትና፣ መንግስት ለእነዚሁ ጉዳዮዮች እየሰጠ ያለው ምላሽ በተመለከተ አንስተዋል፡፡

ዶክተር ሂሩት ሀገሪቱ በለውጥ ሂደት ላይ ያለች፣ ባለፉት ሰባት ወራትም የተወሰዱ በርካታ እርምጃ በዓለም አቀፍ ደረጃ አድናቆትን ያተረፉ ቢሆንም፤ አሁንም ግን ከቀድሞ በተለየ መልኩ በተለይ ዩኒቨርስቲዎችን ኢላማቸው አድርገው ለውጡን ለማደናቀፍ እንቅስቃሴዎች እያየን ነው ብለዋል።

ምንጭ:- ፋና ብሮድካስቲንግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ምስራቅ ወለጋ‼️

በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ወለጋ ዞን እና በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አዋሳኝ አካባቢ በተፈጠረ ግጭት የሰው #ህይወትና ንብረት ላይ #ጉዳት መድረሱን የኦሮሚያ ክልል የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ አስታወቀ።

የቢሮው ምክትል ኃላፊ አቶ ዴሬሳ ተረፈ ለfbc አንደተናገሩት፥ በግጭቱ የኦሮሚያ ክልል ፖሊስን ጨምሮ የበርካታ የአካባቢው ነዋሪዎች ህይወት አልፏል።

እንዲሁም ለጊዜው ግምቱ ያልታወቀ በርካታ ንብረት መውደሙንም ነው አቶ ዴሬሳ የተናገሩት።

ችግሩ ያጋጠመውም ባሳለፍነው ማክሰኞ ህዳር 18 2011 ዓ.ም በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ወለጋ ዞን ሊሙ ወረዳ አርቁምቤ በሚባል አካባቢ መሆኑንም ነው የቢሮው ምክትል ኃላፊ ያስታወቁት።

በግጭቱም በአካባቢው ነዋሪዎች እና በኦሮሚያ ፖሊስ አባላት ላይ አሰቃቂ ወንጀል ተፈጽሟል ያሉት አቶ ዴሬሳ፥ በግጭቱ ህይወታቸው ያለፈ እና የተጎዱ ሰዎች ቁጥር በቅርቡ ይፋ ይደረጋልም ብለዋል።

በግጭቱ ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች አስክሬን በትናንትናው እለት ነቀምቴ ከተማ ሲገባ ህዝቡ ሰልፍ በመውጣት #ስሜታዊ በመሆኑ የአንድ ሰው #ህይወት ማለፉንም ተናግረዋል።

ምክትል ኃላፊው አቶ ዴሬሳ ተረፈ፥ በምእራብ ኦሮሚያ አዋሳኝ አካባቢዎች ላይ እየተፈጠሩ ያሉ ግጭቶች ዋነኛ ምክንያት የክልሉን እና የሀገሪቱን ሰላም የማይፈልጉ እንዲሁም አሁን በሀገሪቱ እየመጣ ያለውን ለውጥ ለማደናቀፍ የሚሯሯጡ አካላት ናቸው ብለዋል።

የእነዚህ አካላት እቅድም እንደ ኦሮሚያ ክልል እና እንደ ሀገር እየመጣ ያለውን ለውጥ ማደናቀፍ በመሆኑ፤ ህዝቡ ከስሜታዊነት በመውጣት መንግስት ችግሩን በዘላቂነት ለመቅረፍ የሚወስደውን እርምጃ እንዲደግፍ ጥሪ አቅርበዋል።

ምንጭ፦ ፋና ብሮድካስቲንግ ኮሮፖሬሽን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Fake News Alert‼️

በAASTU(በአዲስ አበባ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የተማሪ #ህይወት_አለፈ በሚል እየተሰራጨ የሚገኘው መረጃ ከእውነት የራቀ (Fake) ነው። የተማሪ ወላጆች ከላይ ያለው መረጃ አለመረጋጋት ለመፍጠር የተቀናበረ እንደሆነ ልታውቁት ይገባል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
"ኢንተርኔት #መዘጋቱ ያስፈለገው የሰዎችን #ህይወት እና ንብረት ከጥቃት ለማትረፍ ነው። ኢንተርኔት ውሀ ወይም አየር አይደለም። ለመዝጋት ምክንያት የሆኑንን ምክንያቶች ካልፈታን ለሳምንት ሳይሆን እስከ ወዲያኛው #ሊዘጋ ይችላል!" ጠ/ሚ ዶ/ር #አብይ_አህመድ

Via Elias Meseret
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ጥንቃቄ

የወገኖቻንን ህይወት እየቀጠፈ ፤ ንብረትም እያወደመ ያለው የጎርፍ አደጋ !

በያዝነው ክረምት በተለያዩ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ በጎርፍ አደጋ የወገኖቻችን ህይወት እያለፈ ንብረትም እየወደመ ነው።

ለአብነት በአዲስ አበባ በተለያየ ጊዜ ህፃናት በጎርፍ አደጋ ህይወታቸው አልፏል ንብረት ወድሟል፣ በአማራ ክልል በተለያዩ ወረዳዎች በደረሰ የጎርፍ አደጋ የሰው ህይወት ጠፍቷል ፣ የአርሶ አደሮች ንብረትም እንዳልነበር ሆኗል።

ከትላንት በስቲያ ደግሞ ከወደ ኦሮሚያ ክልል፣ ጅማ ዞን ማና ወረዳ ሃሮ ቀበሌ እንደተሰማው የአንድ ቤተሰብ አባላትን የሆኑ ወገኖቻችን በጎርፍ ተወስደው ህይወታቸው አልፏል።

ከወረዳዋ ከተማ የቡ ተነስተው ሃሮ ወደተባለች ቀበሌ 3 ልጆቻቸውን ይዘው ሲጓዙ የነበሩ ቤተሰብ አንድ የ13 ዓመት እና ህጻን ልጅ በደራሽ ጎርፍ ሲወሰዱ አንድ ታዳጊ በህይወት ማግኘት ተችሏል።

በጎርፉ ከተወሰዱት የቤተሰብ አባላቱ የአባት አስከሬን በዕለቱ ሲገኝ፤ የሟች እናትና ሁለት ልጆች አስከሬን ትላንት ጠዋት ተገኝቷል።

የቤተሰብ አባላቱ ፤ በጎርፉ የተወሰዱት ዘመዶቻቸውን ለመጠየቅ ወደ ስፍራው ሲያቀኑ በነበረበት መሆኑን ዶቼ ቨለ ሬድዮ ጣቢያ የወረዳውን ኮሚኒኬሽን ዋቢ አደርጎ ዘግቧል።

በአማራ ክልል በአምባሰል ወረዳ ወገኖቻችን በጎርፍ አደጋ እና በመሬት መንሸራተት ከቤታቸው ተፈናቅለዋል ፤ ንብረታቸው ወድሟል።

በአጠቃላይ 150 አባወራዎች እና እማወራዎች ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው በትምህርት ቤቶች፣ በቀበሌ ማዕከል፣ በገበሬ ማሰልጠኛዎችና በዘመድ ቤት ተጠልለው ይገኛሉ ብለዋል።

በወረዳው በቂ ለድጋፍ የሚሆን ሐብት ባለመኖሩ ለተጎጅዎች የሚመለከታቸው አካላት ሁሉ ድጋፋቸውን እንዲያደርጉ ተጠይቋል።

በሌላ በኩል ደግሞ ከሰሞኑን በአፋር ክልል በጎርፍ አደጋ የወገኖቻችን ህይወት ጠፍቷል ፤ ወገኖቻችን ተፈናቅለዋል፤ ከፍተኛ የሀብት ጥፋትም ደርሷል።

በሠመራ ከተማ ብቻ ጎርፍ ባስከተለው አደጋ በትንሹ የሶስት ሰዎች #ህይወት_አልፏል

በኤሊደአር  ወረዳ  ዶቢ ቀበሌ ደግሞ በጎርፍ አደጋ ከ3 መቶ ሺ ኩንታል በላይ የጨው ምርት ሙሉ በሙሉ ወድሟል።

በአካባቢው ላይ ከ300 በላይ የሚሆኑ ባለሀብቶች በጨው ምርት ላይ ተሰማርተው የሚገኙ ሲሆን አሁን ላይ ሁለት መቶ  የሚሆኑት አምራቾች በጎርፉ ምክንያት ኪሳራ ደርሶባቸዋል።

በተጨማሪም ጨው ለማምረት ተዘጋጅተው የነበሩ የጨው ማምረቻ ቦታወችም በጎርፉ ምክንያት ተበላሽተዋል።

አንድ አምራች የምርት ቦታዎችን ለማዘጋጀት ከ200 ሺ ብር በላይ ሊያወጣ ይችላል የተባለ ሲሆን ባጠቃላይ አምራቾች ላይ የደረሰው ኪሳራ ቀላል ሊባል የሚችል አይደለም።

በተጨማሪም ፤ በአሳይታና አፋምቦ ወረዳ ወገኖቻችን በአዋሽ ወንዝ ሙላት ሳቢያ በተከሰተ የጎርፍ አደጋ በቤት እና ንብረቶቻቸው ላይ ጉዳት ደርሶባቸዋል።

አሳይታ በርጋ ቀበሌ የሚኖሩ ወገኖቻችን በጎርፍ አደጋ እንስሳቶቻቸው ሞተውባቸዋል፣ ቤታቸው እንዳልነበር ሆኗል ፣ ሁለት ሺህ ሄክታር መሬት እርሻ ላይ ጉዳት አድርሶባቸዋል።

በአሁን ሰዓት ከቤታቸው ተፈናቅለው መጠለያ ውስጥ ናቸው።

የመንግስት፣ ማህበራዊ አገልግሎት ሚሰጡ ተቋማት በውሃ ውስጥ ናቸው ያሉት።

በተመሳሳይ ፤ በአፋምቦ ወረዳ ወገኖቻችን በአዋሽ ወንዝ ሙላትና በከባንድ ዝናብ ሳቢያ ቤት ንብረታቸው በጎርፍ አደጋ እንዳልነበር ሆኗል እነሱም ተፈናቅለዋል ፤ እንስሳቶቻቸው ሞተውባቸዋል ፤ እነኚህ ወገኖቻችን የመንግስት ድጋፍ እንፈልጋለን ብለዋል።

በዚሁ ወረዳ 6 ሺህ ሄክታር የጥጥ እና ሰሊጥ እርሻ ላይ ከፍተኛ የሆነ ጉዳት ደርሷል።

መረጃዎቹ የተሰባሰቡት ፦ ከአፋር ብዙሃን መገናኛ ፣ ከኤሊዲአር ወረዳ ኮሚኒኬሽን፣ ከዶቼ ቨለ ሬድዮ ፣ ከአምባሰል ወረዳ ኮሚኒኬሽን ነው።

@tikvahethiopia