TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
211 files
4.1K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
" ንባብ ለህይወት "

ከሐምሌ 28 ጀምሮ የንባብ ለህይወት የመፅሀፍት እና የምርምር ተቋማት አውደርዕይ በአዲስ አበባ ከተማ ኤግዝቢሽን ማዕከል ውስጥ እየተካሄደ ነው።

እስከ ነሀሴ 2 ድረስም ይቆያል።

የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት አውደ ርዕዩን ተዘዋውረው ተመልክተዋል። የተለያዩ መፅሀፍት በቅናሽ ዋጋ እየተሸጡ እንደሚገኙ ገልፀዋል።

የአሁን እንዲሁም ከዚህ ቀደም የታተሙ የተለያየ ይዘት ያላቸው የሀገር ውስጥ እንዲሁም የውጭ መፅሀፍት የቀረቡ ሲሆን የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትም የምርምር ስራዎቻቸውን አቀርበዋል።

በሌላ በኩል ፤ ከመፅሀፍት አውደ ርዕዩ ጎን ለጎን የተለያዩ የኪነጥበብ ዝግጅቶች እየተዘጋጁ ለታዳሚያን እየቀረቡ ናቸው።

በመፅሀፍ አውደ ርዕዩ ላይ የተገኙ የቤተሰቦቻችን አባላት እየተዘዋወሩ ከተመለከቷቸው የመፅሀፍ ሽያጮች መካከል ጃፋር የተሰኘው የመፅሀፍት መደብር #ከ25_ብር ጀምሮ የተለያዩ መፅሀፍት እንዲሸጡ አቅርቦ ተመልክቷል።

የአዲስ አበባ ቲክቫህ አባላት የሆናችሁ ወላጆች ልጆቻችሁን ይዛችሁ ብትሄዱ ለራሳችሁም ለልጆቻችሁም የሚሆኑ መፅሀፍትን ታገኛላችሁ ለልጆችም የተዘጋጁ አስተማሪ ፕሮግራሞች አሉ።

ወጣቶችም የምትወዷቸውን እና የምትፈልጓቸውን መፅሀፍትን በቅናሽ ከማግኘት ባለፈ መሰል ፕሮግራሞችን በማበረታታ በሀገራችን ያለው የንባብ ባህል እንዲያድግ ከፍተኛ አስተዋፆ ማድረግ ትችላላችሁ።

ቦታ ፦ መስቀል አደባባይ ኤግዥቢሽን ማዕከል

@tikvahethiopia