TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
የሚኒስትሮች ም/ቤት 👆 የሚንስትሮች ምክር ቤት ዛሬ 'ሕወሓት' እና 'ሸኔ' ድርጅቶች በሽብርተኛ ድርጅትነት እንዲሰየሙ የውሳኔ ሐሳብ አቅርቧል። የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት በጉዳዩ ላይ ከላይ ያለውን ዝርዝር መግለጫ ሰጥቷል። በተጨማሪም መንግለጫውን በዚህ ማስፈንጠሪያ ማንበብ ትችላላችሁ https://telegra.ph/PM-Office-05-01 @tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
'ሸኔ' እና 'ህወሓት'

የህግ ምሁራንና ባለሞያዎች አስተያየት እና የህ.ተ.ም/ቤት ጥሪ ፦

ዛሬ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባስተላለፈው ማስታወቂያ "ህወሓት" እና "ሸኔ" የሚባሉት ድርጅቶች በአሸባሪነት እንዲፈረጁ ሚንስትሮች ምክር ቤት ባቀረበው ውሳኔ ሃሳብ ላይ የተቃውሞ ማስረጃ ካላቸው በአካል እንዲያቀርቡ ጥሪ አቅርቧል።

የምዑራን አስተያየት በሚኒስትሮች ምክር ቤት ውሳኔ ላይ ፦

• የህግ ጠበቃ እና አማካሪው አቶ አመሃ መኮንን ፡

"እነዚህ ድርጅቶች በረጅም ጊዜ ሂደት ውስጥ ስጋት፣ ለህዝቡ ፀጥታ ስጋት ፣ለሀገር ሰላም ስጋት የሚሆኑበት መንገድ በእጅጉ ይቀንሳል ብዬ ገምታለሁ።
በሽብረትኝነት የመሰየሙ ውጤት ፦
- እነዚህን ድርጅቶች መምራት የሚያስጠይቅ ይሆናል።
- የድርጅቶቹ አባል መሆን ያስጠይቃል።
- ድርጅቶቹን ባማቸውም ሁኔታ መደገፍ እና መተባበር የሚያስጠይቅ ነው የሚሆነው።
ስለዚህ በእጅጉ አቅም የሚያሳጣቸው ነው የሚሆነው።"

• በአምቦ ዩኒቨርሲቲ የህግ መምህሩ አቶ ሚኪያስ በቀለ :

"...አሁን አጠያያቂ የሆነው አንዱ ጉዳይ ፥ ሸኔ የሚባል ድርጅት አለ ወይ ? የሚለው ነገር ነው። እራሱን "ሸኔ" ብሎ የሚጠራ ቡድን አይታወቅም። ስለዚህ መንግስት ማለት የፈለገው የኦነግ የወታደራዊ ክንፉን ለማለት ይመስለኛል። 

ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በደንብ አድርጎ መርምሮ እነዚህን ድርጅቶች እራሳቸውን እንዲከላከሉ እድል ሰጥቶ ሽብርተኛ ድርጅት ነው የሚለውን ስያሜ ሊሰጥ ይችላል።

ውሳኔው በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሚፀድቅ ከሆነ በተለይ ህወሓት በትግራይ ፣ ሸኔ በኦሮሚያ መሰረታቸውን ያደረጉበት ህዝብ ላይ እንግልት እንዳይኖር ፍርድ ቤቶች ከፍተኛ ኃላፊነት ይጠብቃቸዋል።"

• ስማቸውን ያልተገለፀ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ምሁር :

“በሽብርተኝነት ሊፈረጅ የሚችል አካል ለቁጥጥር ያስቸገረ ጠንካራ መዋቅር ያለው ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ መከላከያው ጭምር ህወሓት ስጋት ሊሆን በማይችልበት ደረጃ መመታቱን እና መዳከሙን ደጋግመው በአደባባይ በተናገሩ ማግስት እንዲህ መባሉ ምን ለማለት ተፈልጎ ነው የሚል ጥያቄ ያስነሳል።

‘አጥፍተነዋል’ በሚል ሲነገር የነበረው ፕሮፓጋንዳ እንደነበር እና ህወሓት አሁንም ስጋት እንደሆነ የሚያሳይ ነው። የመንግስትን ተዓማኒነት 'ይበልጥኑ የሚጎዳ' ነው።

• የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሕግ እና ፌደራሊዝም መምህሩ ዶክተር ሲሳይ መንግስቴ :

“ውሳኔ እንዲያውም ቢዘገይ እንጂ የሚጎዳ አይደለም።

ህወሓትን ሽብርተኛ ብሎ ለመፈረጅ በሰሜን እዝ ላይ ያደረሰው ጉዳት ብቻ በቂ ነው።

ህወሓት ባለፉት 3 ዓመታት በግልጽና በስውር በርካታ ጥፋቶችን አድርሷል። የዘገየ ግን ትክክለኛ የውሳኔ ሀሳብ ቀርቧል።

መንግስት በውሳኔ ሃሳቡ ኦነግ ሸኔ ከማለት ይልቅ ‘ሸኔ’ ማለቱ ምናልባት ለሌላ ትርጉም እንዳይጋለጥ በማሰብ ሊሆን ይችላል እንጂ ‘ሸኔ’ በሚል በኦሮሚያ ክልል ባለስልጣናትን እና ሌሎች በክልሉ የሚኖሩ ማንኛውንም ማህበረሰብ እንደፈለገ እየገደለ ነው ይሄንን የሚያደርገው ደግሞ "ኦነግ ሸኔ" ነው።

ያንብቡ 👇
https://telegra.ph/SHANE--TPLF-05-03

#AL_AIN #Deutsche_Welle #SolomonMuchie #HoPR
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የፀጥታው ምክር ቤት ስብሰባ በ #ኢትዮጵያ ጉዳይ ፦

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ም/ቤት (UNSC) በትግራይ ክልል ግጭት ዙሪያ ትላንት ውይይት አድርጓል።

በውይይቱ የድርጅቱ ዋና ፀሃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬስ የተገኙ ሲሆን፤ በጦርነቱ የተካፈሉ አካላት በሙሉ የተኩስ አቁም እንዲያደርጉ ጠይቀዋል።

ምንም እንኳን የኢትዮጵያ መንግስት የተናጥል ተኩስ አቁም በማወጅ ከትግራይ ቢወጣም የህወሓት ሀይሎች ወደ ጎረቤት አፋር እና አማራ ክልሎች ጥቃት በመክፈታቸው አጠቃላይ የተኩስ አቁም ላይ መደረስ እንደልተቻለ ገልጸዋል።

ከወራት በፊት በትግራይ ክልል የተከሰተው ግጭት አሁን ላይ እየተስፋፋ መሆኑን እና በርካታ ሰብአዊ ኪሳራዎች እያስከተለ መሆኑን ተናግረዋል።

በጦርነቱ ሳቢያ፦
- የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር በየእለቱ እያሻቀበ መሆኑን
- ከ2 ሚሊየን በላይ ኢትዮጵያውያን ግጭቱን ተከትሎ መፈናቀላቸውን
- ከትግራይ ክልል በተጨማሪም ወደ አማራ እና አፋር ክልል በተስፋፋው ግጭት ከ300 ሺህ በላይ ሰዎች መፈናቀላቸውን፤
- ከሰብአዊ ቀውስ በተጨማሪም የሀገሪቱን ኢኮኖሚ ክፉኛ እየተጎዳ መሆኑን
- የበሀገሪቱ የብድር ጣራ እየጨመረ መሆኑን
- ሀገሪቱ እዳ የመክፈል አቅሟ እየተዳከመ መምጣቱን፣
- የኑሮ ውድነቱ በከፍተኛ ሁኔታ እያሸቀበ መምጣቱን ገልፀዋል።

ገተሬስ ፥ የኢትዮጵያ አንድነት እና የቀጠናው መረጋጋት ወሰሳኝ ናቸው ያሉ ሲሆን አሁን ላለው ሁኔታ ወታደራዊ መፍትሄ የለም ሲሉ ተናረዋል።

በጦርነቱ የተካፈሉ አካት በሙሉ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ የተኩስ አቁም እንዲያድርጉ፣ የውጭ ሀገራት ሀይሎች ሀገሪቱን ለቀው እንዲወጡ፣ ለሰብአዊ ድጋች መተላለፊያ መንገዶች እንዲከፈቱ እና ችግሩን ለመቅረፍ #በኢትዮጵያ_የሚመራና ሁሉንም አካታች የሆነ ውይይት እንዲካሄድ ጥሪ አቅርበዋል።

#Al_AIN

@tikvahethiopia
" ሁለቱም ወገኖች ሰላም፣ ጸጥታና የኢትዮጵያ መረጋጋት ምኞታቸው መሆኑን ገልፀውልኛል " - ኦሊሴጉን ኦባሳንጆ

በአፍሪካ ህብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ኦሊሴጉን ኦባሳንጆ የመንግስትን እና የህወሃትን አመራሮችን ማነጋገራቸውን ካስታወቁ በኋላ መግለጫ አውጥተዋል፡፡

ኦባሳንጆ ሁሉም ወገኖች ወታደራዊ ፍልሚያውን እንዲያቆሙ ጠይቀዋል፡፡

ከመንግስትም ሆነ ሽብርተኛ ተብሎ ከተፈረጀው ህወሃት በኩል የሰላም ፍላጎቶች መኖራቸውን የገለጹት ከፍተኛ ተወካዩ ‘የሰላም መንገዱ ምን ይሁን’ የሚለው ግን ልዩነታቸው እንደሆነ ጠቅሰዋል።

የአፍሪካ መሪዎችና ዓለም አቀፍ ማህበረሰቡ ሕብረቱ የጀመረውን የማሸማገል ጥረት እንዲደፉ እና ግጭቱን ሊያባብሱ ከሚችሉ ነገሮች እንዲቆጠብም ኦባሳንጆ ጥሪ አቅርበዋል።

ኦባሳንጆ፥ "ሆን ተብሎም ይሁን ባለማወቅ ግጭቱን የሚባብሱና ወደከፋ ደረጃ ከሚያደርሱ ንግግሮች መቆጠብ ያስፈልጋል" ብለዋል ።

ኦባሳንጆ፤ ውጊያው ከቆመ የንግግር ዕድል እንደሚኖር የገለጹ ሲሆን አሁን ባለው ሁኔታ ውጊያ እየተደረገ ግን ለመነጋጋር የሚመች እንዳልሆነ ተናግረዋል፡፡

ኦባሳንጆ ፥ የኦሮሚያ እና አማራ ክልል አመራሮችን ማግኘታቸውን በመግለጫቸው ላይ የገለፁ ሲሆን በቀጣይ ወደ ኢትዮጵያ ሲመለሱ የአፋር ክልል አመራሮችን እንደሚያገኙ አሳውቀዋል።

ኦባሳንጂ ይህ የማሸማገል ስራ እንዲሳካ ቁርጠኛ እንደሆኑ የገለጹ ሲሆን ፦
- #የኬንያ
- #ኡጋንዳ
- #ጅቡቲ
- #ደቡብ_ሱዳን
- #ሶማሊያ እና ሱዳን መሪዎችን ማግኘታቸውን አስታውቀዋል፡፡

ግጭቱን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት አስማሚ ሁኔታ ይፈጠራል ብዬ አስባለሁ ያሉት ኦባሳንጆ ሁለቱም ወገኖች ሰላም፣ ጸጥታና የኢትዮጵያ መረጋጋት ምኞታቸው መሆኑን እንደገለጹላቸው አሳውቀዋል።

Credit : #Al_AIN
Pic : AU

@tikvahethiopia