TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
" የሩዋንዳ እቅድ (ጥገኝነት ጠያቂዎችን ወደ ሩዋንዳ መላክ) ገና ከጅምሩ ሞቶ የተቀበረ ነው " - አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር

ከሰሞኑን ዩናይትድ ኪንግደም (UK) አዲስ ጠቅላይ ሚኒስትር አግኝታለች።

አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር የሌበር ፓርቲ መሪ ሰር ኪር ስታርመር ናቸው።

ፓርቲው የሪሹ ሱናክን የወግ አጥባቂ (ኮንሰርቫቲቭ) ፓርቲ በከፍተኛ ብልጫ ነው ዘርሮ ያሸነፈው።

በከፍተኛ ብልጫ የተሸነፉት ሱናክ ፥ " የሕዝቡን ቁጣ ሰምቻለሁ። ለዚህ ሥራ ያለኝን ነገር ሁሉ ሰጥቻለሁ። ይሁን እንጂ የዩናይትድ ኪንግደም (UK) መንግሥት መለወጥ እንዳለበት ግልጽ የሆነ መልዕክታችሁን አስተላልፋችኋል፤ የሚተካኝም ሲገኝ ከፓርቲ መሪነት እለቃለሁ " ብለዋል።

በሌላ በኩል የምርጫ ውጤቱን ተከትሎ ስልጣን የተረከቡት አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ኪር ስታርመር ዛሬ የመጀመሪያ መግለጫቸውን ሰጥተዋል።

በዚህም ፥ በጥገኝነት ጠያቂዎች / ስደተኞች ጉዳይ የቀድሞው የወግ አጥባቂ መንግሥትን ፖሊሲ እንደማያስቀጥሉ በይፋ አሳውቀዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፤ " የሩዋንዳ እቅድ (ጥገኝነት ጠያቂዎችን /ስደተኞችን ወደ ሩዋንዳ መላክ) ገና ከጅምሩ ሞቶ የተቀበረ ነው " ብለዋል።

መንግስታቸው ፥ የቀድሞው አገዛዝ በህገወጥ መንገድ ወደ ዩናይትድ ኪንግደም የገቡ ጥገኝነት ጠያቂዎች / ስደተኞችን ወደ ሩዋንዳ ለመላክ የጀመረውን ስራ እንደማይቀጥሉበት ተናግረዋል።

" ከሩዋንዳ ጋር የተደረሰው ስምምነት አይቀጥልም ውድቅም ይሆናል " ያሉት ጠ/ሚ ስታርመር  በዚህ የስደተኞች ጉዳይ ላይ የቀድሞው መንግስት ፖሊስ አይቀጥልም ብለዋል።

#UK
#Rwandascheme

@tikvahethiopia