TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የሰላም ተምሳሌት-ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ!!

በነገው ዕለት ከ3 ዩኒቨርሲቲዎች የተውጣጡ #የTIKVAH_ETHIOPIA ቤተሰብ አባላት ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ይገባሉ። ከሁሉም የሀገሪቱ ክፍል #የተሰባሰቡት እኚህ #ወጣቶች ሀገራችን ኢትዮጵያ ላይ #ፍቅር እንዲነግስ ጥላቻ እንዲወገድ፤ የማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀማችን እንዲታረም መልዕክት ያስተላልፋሉ።

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ አካላት፤ ተማሪዎች ህብረት የተለያዩ ማህበራት እና ክበባት እኚህን የሰላም እና የፍቅር መልዕክተኞች፤ የንፁህ ልብ ባለቤት #ወጣቶችን ለመቀበል እየተዘጋጁ ይገኛሉ።

የኢትዮጵያ ተስፋ እኛ የሀገሪቱ ወጣቶች ነን!!
በፍቅር ተደጋግፈን ሀገራችንን እንገነባለን!!

ቦታ - የአፍሪካ ህብረት አዳራሽ
ሰዓት - ምሽት 12:00

ፍቅር፤ ተስፋ፤ አንድነት!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ኔፓል ሀገሪቱ ላይ " ቲክቶክ " እንዲታገድ ወሰነች። ኔፓል ፤ ማህበራዊ መስተጋብርን የሚረብሹና የቤተሰብን መዋቅር እንዲሁም ማህበራዊ ግንኙነቶችን የሚያውኩ ይዘቶችን ለማጋራት ጥቅም ላይ እየዋለ ነው ያለችውን የቻይናውን " #ቲክቶክ " መተግበሪያ እንዲታገድ ውሳኔ አሳለፈች። ሀገሪቱ ፤ " ቲክቶክ " በማህበራዊ መስተጋብር ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ እያሳደረ ነው ያለች ሲሆን በመተግበሪያው ላይ የሚለቀቁት…
#ቲክቶክ

ለምንድነው ሀገራት " ቲክቶክ " ን ለማገድ እየተንቀሳቀሱ ያሉት ?

ከቅርብ ወራት ወዲህ አሜሪካ፣ አውሮፓ፣ ካናዳ ያሉ የህግ አውጪዎች ከፀጥታ እና ደህንነት ስጋት ጋር በማያያዝ ግዙፉን የአጫጭር ቪድዮዎች ማጋሪያ " ቲክቶክ " ን ለማገድ / ለመገደብ የሚያደርጉትን ጥረት ማጠናከራቸውን ኒውዮርክ ታይምስ አስነብቧል።

ዋይትሃውስ እኤአ በፌብሩዋሪ 27 የፌዴራል  ኤጀንሲዎች አፕሊኬሽኑን ከመንግሥት የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎች ላይ እንዲያጠፉ 30 ቀናት ሰጥቷቸው ነበር ፤ እንዲሁም ኒውዮርክን ጨምሮ የተለያዩ ከተሞች የመንግሥት ሰራተኞች " ቲክቶክ " ን እንዳያወርዱ ከልክለዋል።

በተጨማሪም ባይደን በሀገር ደረጃ ከሁሉም መሳሪያዎች ላይ መተግበሪያው እንዲታገድ እንዲያደርጉ የድጋፍ እንቅስቃሴዎች ነበሩ፤ አሁንም አሉ።

ለምንድነው መንግሥታት ቲክቶክን ለማገድ የሚንቀሳቀሱት ?

በተለይ ምእራባውያኑ ቀጥታ ጉዳዩን #ከቻይና ጋር ያገኛኙታል።

የምዕራቡ ዓለም የሕግ አውጪዎች እና ተቆጣጣሪዎች " ቲክቶክ " / ባለንብረቱ የባይትዳንስ የተጠቃሚ መረጃዎችን በቻይና መንግሥት እጅ እንዲገቡ ያደርጋል የሚል አቋም አላቸው።

ለዚህም እንደማያሳያ የሚያደርጉት የቻይና መንግሥት ለደህንነት ጉዳይ መረጃዎችን ለማሰባሰብ በሚስጥር ከቻይና ኩባንያዎች እና ዜጎች መረጃዎችን መውሰድ የሚያስችለው ህግ እንዳለው በመግለፅ ነው።

ቲክቶክ መሰል ክሶችን ለረጅም ጊዜ ውድቅ አድርጓል።

- ህንድ በ2020 ላይ ነው ያገደችው።
- የብሪታኒያ ፣ የፈረንሳይ፣ የኒውዝላንድ ፣ የአውስትራሊያ፣ ካናዳ #ፓርላማዎች ከአባላት ኦፊሴላዊ መሳሪያዎች እንዲታገድ አድርገዋል።
-  የአውሮፓ ህብረት ምክር ቤት በተመሳሳይ ከአባላት ኦፊሴላዊ መሳሪያዎች ላይ አግዷል። የወረደውንም አስጠፍቷል።
- ካናዳ የመንግሥት መሳሪያዎች ላይ እንዳይሰራ፣ የመንግሥት ሰራተኞችም እንዳያወርዱት አድርጋለች።
- የዴንማርክ መከላከያ ሰራዊት ሰራተኞቹ በሙሉ እንዳይጠቀሙ አድርጓል። ስልካቸው ላይ ተጭኖ የነበረውንም አስጠፍቷል።
- ኖርዌይ በመንግሥት ሰራተኞች ስልክ ላይ እንዳይሰራ አድርጋለች።

በተጨማሪ ፦

* አፍጋኒስታን #ወጣቶችን ከአጓጉል ነገር ለመጠበቅ በሚል 2022 ላይ አድግዳለች።

* ኪርጊስታን በዚህ ዓመት የሀገሪቱን ባህል ወግ እና ስርዓት እየበረዘው ፣ ለልጆች፣ ለወጣቶች የአእምሮ ጠንቅ ነው በማለት አድጋለች።

* ኔፓል እና ሶማሊያም እንዲሁ እንዲታገድ ከወሰኑ ሀገራት መካከል ናቸው።

አሜሪካ ለማገድ እያደረገች ያለችው እንቅስቃሴ አለ ?

ካለፈው ዓመት ህዳር ጀምሮ እጅግ በርካታ ግዛቶች " ቲክቶክ " ን  ከመንግስት መሳሪያዎች አግደዋል።

የዩኒቨርሲቲዎች ለምሳሌ ፦ እንደ ቴክሳስ ፣ ኦውበርን ፣ ቦይስ ስቴት ዩኒቨርሲቲዎች አፕሊኬሽኑ #በዋይፋይ እንዳይሰራ አድርገው አግደዋል።

አሜሪካ ውስጥ ከደህንነት ጋር በተያያዘ ብቻ ሳይሆን ቲክቶክ ሱስ የሚያሲዝ እንደሆነና ወጣቶችን እና ህፃናት ልጆችን አሉታዊ ተፅኖ ያሳድራል በሚል የሚከሱ ግዛቶችም አሉ።

ኮንግረሱ ቲክቶክ እንዲታገድ ይፈልጋል ? እንዲታገድ የሚፈልጉ የኮንግረሱ አባላት አሉ። (ከዚህ ቀደም የቀድሞው ፕሬዜዳንት ትራምፕ የማገድ እንቅስቃሴን እንዲቆም መደረጉ ይታወሳል)

ምንም እንኳን አሜሪካ ውስጥ በመንግሥት መሳሪያዎች ላይ እንዲሁም በአንዳንድ ዩኒቨርሲቲ ካምፓሶች ዋይፋይ ቲክቶክ ቢታገድም 150 ሚሊዮን ነው ተብሎ ከሚገመተው ተጠቃሚ ላይ እንዲታገድ ለማድረግ ረጅም ሂደት ሊጠይቅ እንደሚችል በዘርፉ ላይ ያሉ ፀሀፊዎች ይናገራሉ።

" ቲክቶክ " በየጊዜው የሚነሱበትን በተለይም የደህንነት እና የቁጥጥር ክሶች ውድቅ ሲያደርግ ቆይቷል።

@tikvahethiopia