TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#Tigray " የህወሓትን ህጋዊነት መመለስ አስመልክቶ ከፌደራል መንግስት እና የአፍሪካ ህብረት ፓነል የሚወያይ ልኡክ እንደ አዲስ ይደራጃል ሲል " በአቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራ ህወሓት ገለጸ። በህወሓት ምክትል ሊቀመንበር የሚመራው ህወሓት ከመስከረም 20 አስከ 22 /2017 ዓ.ም ለሦስት ቀናት ያካሄደውን የማእከላዊ ኮሚቴ እና የከፍተኛ ካድሬዎች ስብሰባ ማጠቃለሉ በማስመልከት የአቋም መግለጫ አውጥቷል። …
#TPLF

" ህዝብ በማደናገር ላይ ይገኛሉ " - በዶ/ር ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል የሚመራው ህወሓት የማዕከላዊ ቁጥጥር ኮሚሽን

በህወሓት አመራሮች መካከል ያለው ክፍፍል ተቀራርቦ ከመፈታት ይልቅ ከቀን ወደ ቀን ይበልጥ እየተካረረ መጥቷል።

" ከህወሓት አባልነት የተባረሩ በማንኛውም ቦታና ጊዜ በህወሓት ስም ፓለቲካዊ ስራና እንቅስቃሴ ማድረግ አይችሉም " ሲል በዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል የሚመራው ህወሓት የማእከላዊ ቁጥጥር ኮሚሽን አሳውቋል።

የቁጥጥር ኮሚሽኑ ባወጣው የአቋም መግለጫ ፥ ጉባኤ ያካሄደው በዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል የሚመራው ህወሓት " ህጋዊ ነው " ብሏል።

" የህወሓት መተዳደሪያ ደንብ አንቀፅ 8 ቁጥር 4 በውሳኔ አሰጣጥ ላይ አነስተኛ ቁጥር ያላቸው በብዙሃን ተገዢ መሆን እንዳለባቸው ያስቀምጣል " ያለው መግለጫው " በዚሁ መሰረት በ14ኛው የህወሓት ጉባኤ ከጠቅላላ ተሳታፊ 83 በመቶ ጉባኤተኛ የተገኘበት " ህጋዊ ነው !! " ብሎታል።   

ስለሆነም " ህጋዊ አለመሆኑን እያወቀ ህጋዊ መስሎ ማደናገር አግባብነት እና ተቀባይነት ያለው አይደለም " ሲል በምክትል ሊቀመንበር አቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራውን ህወሓት ከሷል።

" ከጉባኤ ራሳችን አግልለናል ወይም ወደ ጉባኤ አንገባም ያሉት በድርጅቱ መተዳደሪያ ህገ ደንብ መሰረት ከድርጅት አባልነታቸው እንደተባረሩ እውነት ነው ፤ በተግባር ግን የህወሓት ስም ፣ አርማ ፣ ሎጎ እና የድርጅቱ ሃላፊነት በመጠቀም ህዝብ በማድናገር ላይ ተጠምደዋል " ብሏል የማእከላዊ የቁጥጥር ኮሚሽን መግለጫ።  

" ከጉባኤ በመሸሽ ሁሉም አይነት ክህደት በድርጅቱ ላይ ፈፅመህ ስታበቃ እኔ ህወሓትን ነኝ የሚል የከሰረ የማደናገር  ፓለቲካ ማራመድ ህጋዊ ፣ ፓለቲካዊ ፣ ሞራላዊ እና ታሪካዊ ተጠያቂነት የሚያስከትል ሆኖ አግኝተነዋል " ሲል አክሏል።

" የህወሓት ማእከላዊ ኮሚቴ ከድርጅቱ የተባረሩት አካላት #ከያዙት_ፓለቲካዊ_ስልጣን_እንዲነሱ ፤ በህወሓት ስም የሚያደርጉትን እንቅስቃሴ እንዲያቆሙ የማድረግ ሃላፊነቱን እንዲወጣ እንጠይቃለን " ብሏል።

ቁጥጥር ኮሚሽኑ ፥ " ህዝብ በማድናገር ላይ ይገኛሉ " ሲል ክስ ያቀረበባቸው በአቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራውን የህወሓት ቡድን " ህዝብ እንዲታገላቸው " ሲል ጥሪ አስተላልፏል። 

" ህወሓት ለ2 እንደተከፈለ ተደርጎ የሚቀርበው ተረክ ከህወሓት አልፎ ህዝብ ስለሚጎዳ በፍጥነት መታረም አለበት " ብሏል።

በምክትል ሊቀ-መንበር ጌታቸው ረዳ የሚመራ ህወሓት  መስከረም 23 /2017 ዓ.ም ባወጣው  መግለጫ  " የህወሓት ህጋዊነት መመለስ አስመልክቶ ከፌደራል መንግስት እና የአፍሪካ ህብረት ፓነል የሚወያይ ልኡክ እንደ አዲስ ይደራጃል " ማለቱን መዘገባችን ይታወሳል።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia