TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የአገር መከላከያ ሰራዊት‼️

የአገር መከላከያ ሰራዊት አባላት የመለያ ደንብ ልብስ የቀለምና የዲዛይን ለውጥ ሊደረግበት መሆኑን የመከላከያ ሰራዊት ፋውንዴሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ ሜጀር ጀኔራል #አብዱራህማን_እስማኤል ገለጹ።

የመከላከያ ሰራዊቱን የመለያ ደንብ ልብስ በመልበስ በሰራዊቱ ስም #ወንጀል የሚፈፅሙ አካላትን #ለመቆጣጠር ያስችላልም ተብሏል።

የመከላከያ ሰራዊት ፋውንዴሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ ሜጀር ጀነራል አብዱራህማን እስማኤል ለኢዜአ እንዳሉት፤ የመከላከያ ሰራዊቱን የመለያ ደንብ ልብስ ጥራትና ደረጃውን በጠበቀ የቀለምና ዲዛይን ለውጥ ሊደረግበት ነው።

ፋውንዴሽኑ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 179/2002 በተሰጠው ስልጣን መሰረት ለሰራዊቱ አልባሳትና ሌሎች ወታደራዊ ግብዓቶችን በማምረት ወይም ገዝቶ ያቀርባል ብለዋል።

የመከላከያ ሰራዊት አባላት የሚወዱት፣ በጥራት፣ በቀለምና በዲዛይን የተሻለ የመለያ ልብስ እንዲሆን ከተለያዩ አገሮች ተመክሮ መወሰዱን ገልጸዋል።

የመከላከያ ጥናትና ምርምር ማዕከል ሃላፊ ብርጋዴር ጀኔራል #ተሾመ_ገመቹ በበኩላቸው የመከላከያ ሰራዊቱን አልባሳት መልበስ የሚችለው የሰራዊቱ አባል ብቻ ቢሆንም ተገቢ ቁጥጥር ባለመደረጉ የማይመለከታቸው ግለሰቦች ለብሰውት ተስተውሏል።

አዳዲስ አልባሳት በሚቀርቡበት ወቅት አሮጌዎቹ በአግባቡ ሳይወገዱ በመቅረታቸው ልብሱ በማይመለከታቸው አካላት እጅ ገብቶ የሰራዊቱን ስምና ክብር የሚያጎድፉ የተለያዩ ወንጀሎች እየተፈጸሙበት መሆኑን ገልጸዋል።

በመሆኑም በቀጣይ በሰራዊቱ አልባሳት ላይ የሚደረገው የቀለም ለውጥ እንዲሁም አዲስ አልባሳት ሲሰጥ ችግሩን ለመፍታት የሚያስቸሉ እርምጃዎች እንደሚወሰዱ ነው ያመለከቱት።

የመከላከያ ሰራዊቱን የመለያ ደንብ ልብስ በመልበስ ወንጀል የሚፈጽሙ አካላት ካሉ በወንጀል እንደሚጠየቁ ተናግረዋል።

ኅብረተሰቡም የመከላከያ ሰራዊቱን የመለያ ደንብ ልብስ መልበስ የሚችለው ሰራዊቱ ብቻ መሆኑን ተረድቶ የማይገባውን ልብስ ባለመልበስ ወንጀል እንዳይፈጸም ሊተባበር እንደሚገባ አሳስበዋል።

ምንጭ፦ ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia