TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
Fake News Alert‼️

አፍሪካን ዴይሊ ቮይስ የተሰኘ የሚድያ ተቋም ተስፋ ኒውስ የሚባል የኤርትራ ዜና ድርጅትን ጠቅሶ "አሜሪካ የቀድሞው የደህንነት ሀላፊ የነበሩት አቶ #ጌታቸው_አሰፋን ወደ ህግ ለማቅረብ የሚደረገውን ዘመቻ ተቀላቅላለች" ብሎ ዘግቧል። የAPው ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት ጉዳዩን ሊያውቁ ይችላሉ ብሎ ያሰባቸው ሁለት ግለሰቦች ጋር ደውሎ ያገኛቸው ሁለት መልሶች፦

1. "ስህተት ነው! አንዳንድ የሀገር ውስጥ አክቲቪስቶች የአሜሪካንን ሚና ሆን ብለው ለማጉላት ሲፈልጉ የሚጠቀሙበት ስሌት ነው። "

2. "It is a fabricated story."

@tsegabwolde @tikahethiopia
“በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች የት እንደደረሱ #አይታወቅም
.
.
“አቶ #ጌታቸው_አሰፋን ለመያዝ ተኩስ መግጠም አስፈላጊ አይደለም”

አቶ #ብርሃኑ_ፀጋዬ(የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ)

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የቀድሞውን የብሄራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር #ጌታቸው_አሰፋን በቁጥጥር ሥር ለማዋል ከትግራይ ክልል ጋር እየተነጋገረ መሆኑን የፌዴራል ዐቃቤ ሕግ አስታወቀ፡፡ ዐቃቤ ሕግ እንዳስታወቀው፣ መቀሌ የሚገኙት አቶ ጌታቸው በፖሊስ እንደሚፈለጉ ከታወቀ ቆይቷል፤ የእሥር ማዘዣም ከወጣባቸው ቆይቷል፡፡ አቶ ጌታቸው አሰፋ የተጠረጠሩት በከባድ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ወንጀል ነው፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
"አቶ #ጌታቸው_አሰፋን የተመለከተ አጀንዳ አልነበረም"
.
.
የሕወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ ሰሞኑን የተሰበሰበው መደበኛውን የሥራአፈጻጸም ግምገማ ለማድረግ ሲሆን፣ በዚህም መሠረት የክልሉመንግሥት ካለፈው ሐምሌ ወር 2010 ዓ.ም. ወዲህ ባሉት ጊዜያትያከናወናቸውን ሥራዎች እንዲሁም ፀጥታና ደኅንነትን በተመለከቱጉዳዮች ላይ ግምገማ ማድረጉን የድርጅቱ ሥራ አስፈጻሚ አባል አቶጌታቸው ረዳ ለሪፖርተር ገለጹ።

ሕወሓት ለሁለት ቀናት ያካሄደውን ስብሰባ ባለፈው ዓርብ አጠናቋል።ይህ ስብሰባ የተለየ አለመሆኑን የተናገሩት አቶ ጌታቸው ረዳ፣ በፓርቲደረጃ በመገናኘት የክልሉን መንግሥት የሥራ አፈጻጸምና ወቅታዊሁኔታዎች ከተገመገሙ ቆየት በማለቱ የተጠራ ስብሰባ ቢሆንምየተለመደ የፓርቲ ሥነ ሥርዓት መሆኑንም አመልክተዋል።

በዚህ ስብሰባ የክልሉ መንግሥት ባለፉት ወራት ያከናወናቸው የልማትናየማኅበራዊ ጉዳዮች ሲገመገሙ፣ በተጨማሪም በወቅታዊ የፀጥታናደኅንነት ጉዳዮች ላይ ውይይት መካሄዱን ተናግረዋል።

አቶ ጌታቸው ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ የሕወሓት ዋነኛ መወያያ አጀንዳባይሆንም ከወራት በፊት የተከፈተው የኢትዮ ኤርትራ ድንበር በቅርቡየተዘጋበት ምክንያት ምን እንደሆነ የክልሉ ምክትል ፕሬዝዳንትናየሕወሓት ሊቀመንበር ደብረጽዮን ገብረ ሚካኤል (ዶ/ር) ማብራሪያእንዲሰጡበት ጥያቄ ቀርቦላቸው ነበር።

ጉዳዩ በቀጥታ የፌዴራል መንግሥትን የሚመለከት ቢሆንም፣ ጉዳዩንየክልሉ ምክትል ፕሬዚዳንት እንዲከታተሉት ማዕከላዊ ኮሚቴውመስማማቱን ገልጸዋል።

በክልሉ የፀጥታና ደኅንነት ጉዳዮች እንዲሁም በአገር ደረጃየሚስተዋለው የፀጥታ ችግርን በተመለከተ ውይይት መደረጉን የገለጹትአቶ ጌታቸው ረዳ፣ ምንም እንኳን ሕወሓት በአገር አቀፍ ደረጃ ያለው ሚናትንሽ ቢሆንም ከፌዴራል መንግሥት ጋር በመተባበር ኃላፊነቱንእንዲወጣ መወሰኑን ተናግረዋል።

የፌዴራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ በዚህ ሳምንት ለፓርላማ ባቀረበውሪፖርት በከባድ የሰብዓዊ መብት ወንጀል የተጠረጠሩት የብሔራዊመረጃና ደኅንነት የቀድሞ ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው አሰፋ በቁጥጥርሥር ለማዋል ለትግራይ ክልል ጥያቄ ቢቀርብም ክልሉ ለመተባበርፈቃደኛ አለመሆኑና የክልሉ አመራር አቶ ጌታቸውንም ሆነ ሌሎችተጠርጣሪዎችን ሸሽጓል በማለት ዋና ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ አቶ ብርሃኑጸጋዬ ተናግረው ነበር።

የሕወሓት ስብሰባ ከዚህ ወቀሳ በኋላ የተካሄደ በመሆኑ የአቶ ጌታቸውጉዳይ የውይይቱ አካል ይሆናል የሚል ግምት በበርካቶች ዘንድ ነበር።

የአቶ ጌታቸው አሰፋን ጉዳይ የተመለከተ ውይይት ተካሄዶ እንደሆነየተጠየቁት አቶ ጌታቸው ረዳ፣ በዚህ ጉዳይ ላይ ውይይት አለመደረጉንናፓርቲው በጉዳዩ ላይ ሊወያይም እንደማይችል ተናግረዋል።

አቶ ጌታቸው አሰፋ የሕወሓት ሥራ አስፈጻሚ አባል መሆናቸውይታወቃል። ነገር ግን በዚህ የሕወሓት ስብሰባ ላይ አለመገኘታቸውንሪፖርተር ከአቶ ጌታቸው ረዳ ለማረጋገጥ ችሏል።

በኢሕአዴግ መተዳደሪያ ደንብ መሠረት የኢሕአዴግ ሥራ አስፈጻሚበየሦስት ወሩ፣ ማዕከላዊ ኮሚቴው ደግሞ በየስድስት ወሩ መገናኘትእንዳለበት ቢደነግግም፣ አስቸኳይ ሁኔታዎች ሲኖሩ ሊጠራ እንደሚችልይደነግጋል።

ይሁን እንጂ ሥራ አስፈጻሚው ከተሰበሰበ ቆይቷል። ይህ ጉዳይበሕወሓት የሰሞኑ ስብሰባ ተነስቶ እንደሆነ የተጠየቁት አቶ ጌታቸው፣ ‹‹አልተነሳም። ሕወሓት በዚህ ጉዳይ ለምን ይወያያል? ስብሰባውንመጥራት ያለበት የኢሕአዴግ ሊቀመንበር ነው፤›› ብለዋል።

ነገር ግን የአገሪቱ ወቅታዊ የፀጥታና የደኅንነት ጉዳዮች በኢሕአዴግደረጃ ውይይት ሊደረግባቸው እንደሚገባ የተናገሩት አቶ ጌታቸው ረዳ፣‹‹ኢሕአዴግ በቅርቡ ስብሰባ ካልጠራ በእኛ በኩል ስብሰባ እንዲጠራጥያቄ ልናቀርብ እንችላለን፤›› ብለዋል።

በማኅበራዊ ትስስር ገጾች የሕወሓት ሊቀመንበር ከኃላፊነት ለመልቀቅጥያቄ አቅርበው እንደነበር የሚወራውንም አስተባብለዋል።

ምንጭ፦ ሪፖርተር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"አቶ #ጌታቸው_አሰፋን በተመለከተ ከክልሉ ጋር እየሰራን ነው" ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ
.
.

የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ዛሬ አርብ ጥር 17 ቀን ከሰዓት በኋላ በሰጠው መግለጫ በሶማሌ ክልል ጅግጅጋ እና ሌሎችም አካባቢዎች ተነስቶ ከነበረው ሁከት እና ብጥብጥ ጋር በተያያዘ ሳከናውነው የቆየሁትን ምርመራ #አጠናቅቄያለሁ ብሏል።

በፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ሕግ የተደራጁ፣ ድንበር ተሻጋሪ እና አገራዊ ጉዳት የሚያደርሱ ወንጀሎች ዳይሬክቶሬት ምክትል ዳይሬክተር የሆኑት አቶ #ተመስገን_ላጲሶ በበኩላቸው ለምርመራው መነሻ የሆነው ከሐምሌ 28 እስከ 30 2010 ዓ.ም የተፈፀሙ ወንጀሎች ቢሆኑም በምርመራው ሂደት አቶ አብዲ የክልሉ ፕሬዚዳንት በነበሩበት ጊዜ የተፈፀሙ ወንጀሎችን እንድንመረምር የሚያስችሉ ማስረጃዎችን አግኝተናል ብለዋል።

የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የሕዝብ ግንኙነት እና ኮሙዩኒኬሽን ኃላፊ የሆኑት አቶ #ዝናቡ_ቱኑ ምርመራውን ፌዴራል ፖሊስ፣ የክልሉ ፖሊስና የመረጃ ደህንነት ጽሕፈት ቤት በጋራ ሲያከናወኑ መቆየታቸውን ገልፀዋል።

ኃላፊው ምርመራው አምስት ወራት የፈጀው የክልሉ የቀድሞ ከፍተኛ መሪዎች ሁሉ የተሳተፉበት በመሆኑ ይህ ወንጀሉን ውስብስብ ማድረጉን አስረድተዋል።

ከሶማሌ ብሔር ውጭ የሆኑ ሌሎች ኢትዮጵያውያን ላይ ያነጣጠረ ነበሩ ባሏቸው ጥቃቶች የተሳተፉ ናቸው የተባሉ 46 ተጠርጣሪዎችን ሕገ መንግሥትን ለመናድ በመሞከር፣ በማነሳሳት፣ በአስቃቂ ግድያና በአስገድዶ መድፈር ከሰናል ብለዋል ኃላፊው

ይሁን እንጂ ከተከሳሾቹ መካከል በቁጥጥር ስር ውለው የሚገኙት ስድስት ብቻ ናቸው። ሌሎቹ በአገር ውስጥ እና ከአገር ውጪ ተደብቀው እንደሚገኙ ገልፀዋል።

አቶ ዝናቡ በቀድሞው የክልሉ መንግሥት በተደራጀ እና በተጠና መልኩ ዕቅድ ተይዞ እና አስፈላጊ የሰው ኃይልም ቀርቦ የተከናወኑ ናቸው ባሏቸው ጥቃቶች በርካታ የሰው ሕይወት ጠፍቷል፣ አሰቃቂ ግድያ ተፈፅሟል፣ ከዚህም ውስጥ በእሳት በማቃጠል፣ አንገት በመቅላት መግደል፣ እንዲሁም በህይወት እያሉ መቅበር ተከናውኗል ሲሉ ተናግረዋል።

"የቀድሞው የክልሉ ፕሬዚዳንት አቶ አብዲ መሃመድ ዑመርን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ ኃላፊዎች መሳተፋቸውን ከምርመራ ሪፖርቱ ተረድተናል" ያሉት አቶ ዝናቡ ከፌዴራል የሚመጣ ኃይልን እንመክታለን በሚል የክልሉ ኃላፊዎች ያስተባብሩ እንደነበርም ገልፀዋል።

የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ቃል አቀባይ ጨምረው እንደተናገሩት የ58 ሰዎች ህይወት የጠፋ ሲሆን 50 ሰዎች በጅምላ ተቀብረው ተገኝተዋል ብለዋል። እርሳቸው እንዳሉት አርባ ሁለቱ አንድ ላይ፣ ስምንቱ ደግሞ ሌላ ቦታ በጅምላ ተቀብረው ተገኝተዋል። በተጨማሪ ሌሎች 200 ሰዎች በጅምላ ተቀብረው ቢገኙም የእርሱ ምርመራ ገና አልተጠናቀቀም።

በምርመራ ተደረሰበት በተባለው ግድያም የኦርቶዶክስ እምነት ካህናት እና ምዕመናን በቤተ ክርስትያን ግቢ ውስጥ ተገድለዋል፤ ተቀብረዋል ተብሏል።

እንደ አቶ ዝናቡ 266 ሰዎች የአካል ጉዳት ሲደርስባቸው 10 ሴቶች ሄጎ በሚባለው ጥቃት አድራሽ ቡድን እና በክልሉ ልዩ ኃይል ተደፍረዋል፤ ይሁንና ይህ ቁጥር መደፈራቸውን የደበቁ ሴቶች የሚኖሩ በመሆኑ ከፍ ሊልም ይችላል ተብሏል።

የተዘረፈ እና የተቃጠለ ንብረት ከ421 ሚሊዮን ብር በላይ ይሆናል ብለዋል አቶ ዝናቡ።

በቅርቡ በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር ስለዋሉት አቶ በረከትና አቶ ታደሰን በተመለከተ ለቀረበላቸው ጥያቄ "ምርመራውን የሚያከናውነው የአማራ ክልል ዐቃቤ ሕግ ነው፤ የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ አይደለም፤ ስለዚህ የምንለው የለም" ብለዋል።

አክለውም የቀድሞ የደህንነት ኃላፊ አቶ ጌታቸው አሰፋን በተመለከተም ካልተያዙ ሰዎች መካከል እንደሚገኙ አመልክተው፤ በመሆኑም ይህንን በተመለከተ ከክልሉ መንግሥት ጋር እየሰራን ነው፤ ለመያዝ አስፈላጊ ሒደቶች እየተከናወኑ እንደሆነ አስረድተዋል።

ከጅግጅጋ ብጥብጥ ተጠርጣሪዎች መካከል ደግሞ የተወሰኑት ያለመከሰስ መብት ያላቸው በመሆኑ እርሱን በተመለከተም ከክልሉ ጋር እየሰሩ መሆናቸውን አክለው ተናግረዋል።

አሁን ባለው የምርመራ ሂደት አቶ አህመድ ሽዴ ከተጠርጣሪዎች መካከል እንደማይገኙበትም ጠቁመዋል።

ምንጭ:- BBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የቀድሞ የደህንነት ኃላፊ አቶ #ጌታቸው_አሰፋን በቁጥጥር ስር ለማዋል ከክልሉ መንግሥት ጋር እየሰራ እንደሆነ የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ ዛሬ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ገልጿል። አቶ ጌታቸውን ለመያዝ አስፈላጊ ሒደቶች እየተከናወኑ እንደሆነም ነው የተሰማው።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETH ማጠቃለያ🗞ጥር 17/2011 ዓ.ም.

ዘንድሮ ለሰባተኛ ጊዜ የሚከበረው የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ቀን በአየር ኃይልና በኦሮሚያ ክልል መንግሥት ትብብር #በአዳማ ከተማ እንደሚከበር፣ የኢፌዴሪ መከላከያ ኢንዶክትሪኔሽንና የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት አስታውቋል፡፡ በዓሉም የካቲት 7 ቀን 2011 ዓ.ም. እንደሚከበር ተገልጿል፡፡
.
.
ዛሬ ማለዳ በተካሄደው የዱባይ ማራቶን ጌታነህ ሞላ የቦታውን ፈጣን ሰዓት በማስመዝገብ አሸንፏል። በሴቶች ኬንያውያን እኤአ ከ2006 በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ አሸንፈዋል፡፡
.
.

አቶ #በረከት_ስምዖንና አቶ #ታደሰ_ካሳ በተጠረጠሩበት የጥረት ኮርፖሬት የሀብት ብክነት ጉዳይ ዛሬ በባሕር ዳርና አካባቢዋ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቀርበዋል፡፡
.
.
#የአገር_መከላከያ_ሰራዊት አባላት እና የሶማሌ ክልል #ልዩ_ሀይል አባላት ዛሬ #በጅግጅጋ_ከተማ የፅዳት ስራ አከናውነዋል።
.
.
በነጭ ሣር ፓርክ ላይ ለጊዜው ባልታወቀ ምክንያት እሳት ተነስቶ 1 ሺ ሄክታር የሚሆን የፓርኩ ክፍል ወድሟል።
.
.
በድሬዳዋ ከተማ #የተቀሰቀሰው_ተቃውሞ ዛሬ ጥር 17/2011 ዓ.ም. ቀጥሎ ውሏል። የኢንተርኔት አገልግሎት ተዘግቷል።
.
.
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በ2 ዙር በተካሄደ ነፃ የስራ ዘመቻ 3.5 ሚሊዮን ብር የሚገመት ስራ መሰራቱን ተናግሯል።
.
.
የኢፌዲሪ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የ100 ቀናት እቅዱን በአርባምንጭ ከተማ ገምግሟል።
.
.
በሱማሌ ክልል በተፈጠረው ግጭት እጃቸውን በማስገባት ወንጀል ሰርተው ከሀገር የወጡ ባለስልጣናትን ወደሀገር #በመመለስ በህግ ተጠያቂ ለማድረግ ከተሸሸጉባቸው ሀገራት ጋር ስምምነት ላይ መደረሱን የፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ አስታውቋል።
.
.
በሳኡዲ አረቢያ በተለያየ ምክንያት ታስረው የነበሩ 368 ኢትዮጵያውያን ዛሬ ወደ አገራቸው ገብተዋል።
.
.
በድሬዳዋ ከተማ የተፈጠረው የሰላም መደፍረስ የሕዝቡን አብሮነት እና ተቻችሎ የመኖር እሴት የሚሸረሽር በመሆኑ ሰላምን በማወክ ተግባር የተሰማሩ ግለሰቦች ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ የከተማ አስተዳደሩ አሳስቧል።
.
.
በኢትዮጵያ #የመጀመሪያ የሆነ የሚዲያ ኤክስፖ በኤግዚብሽን ማዕከል ዛሬ ተከፍቷል።
.
.
የቀድሞ የደህንነት ኃላፊ አቶ #ጌታቸው_አሰፋን በቁጥጥር ስር ለማዋል ከክልሉ መንግሥት ጋር እየሰራ እንደሆነ የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ ዛሬ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ገልጿል።
.
.
በጉጂ ዞን ይንቀሳቀሱ የነበሩ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር /ኦነግ/አባላት ከጫካ ወጥተው #በሰላማዊ መንገድ ለመታገል መወሰናቸውን ገልፀዋል።
.
.
የሱማሌ ክልል መሪ--አቶ #ሙስጠፋ_ኡመር-የፌዴራል ገንዘብ ሚኒስትሩን አቶ #አህመድ_ሺዴን-በይፋ በክልሉ መንግስት ላይ "ዓመፃ-ክህደት በመፈፀም" እጅግ ከባድ ወንጀል #ከሰዋል

ምንጭ፦ አዲስ ስታንዳርድ፣ fbc፣ ኢዜአ፣ ኢ.ፕ.ድ.፣ elu፣ ቢቢሲ፣ የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት

.
.
አመሰግናለሁ! ሰላም እደሩ!!
ሀገራችን ቸር ትደር!!
ጥር 17/2011 ዓ.ም.
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update አቶ #ጌታቸው_አሰፋን ጨምሮ በሌሉበት ጉዳያቸው እየታየ ያሉ አራት የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገለግሎት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች መጥሪያ ደርሷቸው እንዲቀርቡ ፍርድ ቤት በድጋሚ ትዕዛዝ ተሰጠ። የፌዴራል ከፍተኛ ደረጃ ፍርድ ቤት 1ኛ ወንጀል ችሎት በድጋሚ ትዕዛዝ የሰጠው ሚያዚያ 30 በተሰጠው ትዕዛዝ መጥርያው ከፍርድ ቤት ወጪ ባለመሆኑ ነው። አሁን ግን ፍርድ ቤቱ የፌደራል ፖሊስ መጥሪያውን ባሉበት እንዲያደርስ ጠቅላይ አቃቢ ህግም ጉዳዩን እንዲከታተል ትዕዛዝ ሰጥቷል። የዚህን ውጤት ለመጠባበቅና በሌሎች ጉዳዮች ላይ ትዕዛዝ ለመስጠት ፍርድቤቱ ለግንቦት 16 ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

Via EBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia