TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.44K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ሀገር መከላከያ ሚኒስቴር‼️

አሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታ #አልሸባብ ከጸጥታ ሃይሉ አቅም በላይ ሆኖ በሶማሌ ክልል ችግር ሊፈጥር እንደማይችል የአገር መከላከያ ሚኒስቴር አስታወቀ።

መከላከያ ሰራዊቱ በአገሪቷ አንዳንድ አካባቢዎች የሚከሰቱ የጸጥታ ችግሮችን ከህዝቡና ከጸጥታ ሃይሎች ጋር በመሆን እያረጋጋ መሆኑን ገልጿል።

የመከላከያ ኢንዶክትሪኔሽንና የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተሩ ሜጄር ጄኔራል መሐመድ ተሰማ ዛሬ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ አልሸባብ ቀደም ሲል በተለይ በምስራቁ የአገሪቷ ክፍል በጸጥታና በልማት እንቅስቃሴው ላይ ስጋት ሲፈጥር መቆየቱን አስታውሰዋል።

መከላከያ ሰራዊት ከፌዴራል የጸጥታ ሃይሎች፣ ከክልል የጸጥታ ሃይሎችና ከህዝቡ እንዲሁም ከጎረቤት አገሮች ጋር በመተባበር የአልሸባብን ጥቃት መመከት የሚችልበት ደረጃ ላይ መሆኑንም ነው ያመለከቱት።

”እንደ ወታደር አልሸባብ ጥቃት ከማድረሱ በፊት ክትትልና ስምሪት መደረግ አለበት” ያሉት ሜጄር ጄኔራሉ ሶማሌ ክልል አሁን ካለው ያለመረጋጋት ጋር ተያይዞ ምቹ ሁኔታ እንዳይፈጥርለት በትኩረት እየተሰራ ነው ብለዋል።

በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አካባቢ የሀሰት ወሬዎችን በማቀናበር የተረጋጋ የመማር ማስተማር ሂደት እንዳይኖር የሚያደርጉ አካላትን የህግ ተጠያቂ ለማድረግ መከላከያ ሰራዊት ከሌሎች የጸጥታ አካላት ጋር በቅንጅት እየሰራ መሆኑን ነው የገለጹት።

በኦሮሚያና ቤንሻንጉል ጉምዝ ክልሎች አዋሳኝ ያለውን የጸጥታ ችግር ለመፍታት መከላከያ ሰራዊቱን ጨምሮ ከብሄራዊ ደህንነትና መረጃ፣ ከክልል አመራሮችና ከፌዴራል ፖሊስ የተወጣጣ ኮማንድ ፖስት ተቋቁሞ ወደ ስራ መግባቱንና በአጭር ጊዜ ወደ እያንዳንዱ ቀበሌ በመግባት የማረጋጋቱን ስራ እንሰራለን ብለዋል።

የጸጥታ ሃይሉ ዋና ስራ ሰላም በሌለባቸው አካባቢዎች ሰላም ማስከበርና ማረጋጋት በመሆኑ ህዝቡ ለሚያነሳቸው ፖለቲካዊ ጥያቄዎች የፖለቲካ አመራሮች ፈጣን ምላሽ ካልሰጡ ችግሩ መልሶ ሊያገረሽ ይችላል ሲሉም መልዕክት አስተላልፈዋል።

ምንጭ፦ ena
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሰበር ዜና‼️

ምሽቱን #በሞቃዲሾ ህዝብ በሚበዛበት ቦታ በተፈፀመ #የቦንብ_ጥቃት በትንሹ የ15 ሰዎች ህይወት አለፈ። ለጥቃቱ #አልሸባብ የተባለው የሽብር ቡድን #ሀላፊነት መውሰዱ ነው የተሰማው።

ፎቶ፦ Harun Maruf
@tsegabwolde @tikvahethiopia
" አብዲአዚዝ ለሀገሩ፣ ለወገኑና ለሃይማኖቱ በድፍረት እና ያለ እረፍት የሰራ ታታሪ ጋዜጠኛ እና የሀገር ጀግና ነበር " - ጠቅላይ ሚኒስትር መሀመድ ሁሴን ሮብሌ

አልሸባብን በመተቸት የሚታወቀው ሶማሊያዊ ጋዜጠኛ ትላንት ሞቃዲሾ ውስጥ በተፈጸመ የአጥፍቶ ጠፊ ጥቃት ተገደለ።

አብዲአዚዝ መሀሙድ ጉሌድ ወይም አብዲአዚዝ አፍሪካ በመባል የሚታወቀው ይህ ጋዜጠኛ ትላንት ከቀትር በኋላ በከተማው ከሚገኝ ሬስቶራንት ሲወጣ ኢላማ ተደርጎ ነው የተገደለው።

ከጋዜጠኛው በተጨማሪ በአካባቢው የነበሩ ሁለት ሰዎች በፍንዳታው ቆስለው ወደ ሆስፒታል ተወስደዋል።

በሬድዮ ሞቃዲሾ ይሰራ የነበረው ይህንን ጋዜጠኛ ኢላማ እንዳደረገውና ጥቃቱንም እንዳቀነባበረ #አልሸባብ አስታውቋል።

የአጥፍቶ ጠፊ ቦምብ ጥቃቱ የደረሰው ጉሌድ ከሶማሌ ብሄራዊ ቴሌቪዥን ዳይሬክተር እና አንድ ሹፌር ጋር ሬስቶራንቱ አቅራቢያ በሚገኝ አንድ መኪና ፊት ለፊት መሆኑን የሬድዮ ሞቃዲሾ ድረገፅ የፖሊስ ምንጮችን ጠቅሶ ዘግቧል።

የጋዜጠኛውን ግድያ ተከትሎ የሶማሊያው ጠቅላይ ሚኒስትር መሀመድ ሁሴን ሮብሌ ሃዘናቸውን ለጉሌድ ቤተሰቦች መግለፃቸውን ተዘግቧል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፥ "አብዲአዚዝ ለሀገሩ፣ ለወገኑ እና ለሃይማኖቱ በድፍረት እና ያለ እረፍት የሰራ ታታሪ ጋዜጠኛ እና የሀገር ጀግና ነበር" ብለዋል።

ጉሌድ በአልሸባብ ታስረው ከተፈቱ ተጠርጣሪዎች ጋር ባደረገው ቃለ ምልልስ የሚታወቅ ሲሆን የሚያቀርበው ስርጭቱም በርካታ ታዳሚዎችን ይስባል።

መረጃውን ሬድዮ ሞቃዲሾን ዋቢ አድርጎ ያስነብበው ቢቢሲ ነው።

@tikvahethiopia
አልሸባብ ?

ሶማሊያ ውስጥ ያለው ውጥረትና በፕሬዜዳንቱ እና ጠቅላይ ሚኒስትሩ መካከል ያለው ቅራኔ ለአልሸባብ የሽብር ቡድን በር እንዳይከፍት ተሰግቷል።

ዛሬ ጥዋት ላይ የ #አልሸባብ ታጣቂዎች ከዋና ከተማይቱ ሞቃዲሾ በስተሰሜን በምትገኝ ከተማ ላይ ጥቃት ሰንዝረው ከተማውንም ለመቆጣጠር ሞክረው እንደነበር ተዘግቧል።

አልሸባብ ጥቃቱን የከፈተው ከሞቃዲሾ 30 ኪ.ሜ ያህል በምትርቀው ስትራቴጂክ ከተማ #ባላድ እንደሆነ የተሰማ ሲሆን በጥቃቱ ሰዎች ተገድለዋል።

እንደ ቪኦኤ ዘገባ ከሆነ ፥ የሶማሊያ ጦር ኃይል በወሰደው የመልሶ ማጥቃት እርምጃ የሽብር ቡድኑን ባላድን የመያዝ ሙከራውን አክሽፏል።

በአሁን ሰዓት ከተማዋ ሙሉ በሙሉ በመንግስት እጅ ስር እንዳለችም ገልጿል።

በዛሬው ጥቃት 4 የመንግስት ወታደሮች እንደተገደሉ ቪኦኤ ሲዘግብ የሶማሊያ መንግስት ሚዲያ በበኩሉ በጥቃቱ 9 የአልሸባብ ታጣቂዎች መገደላቸውን እና በአሸባሪዎች በተተኮሰ ሞርታር 5 ንፁሀን ዜጎች መሞታቸውን ዘግቧል።

@tikvahethiopia