TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.7K photos
1.49K videos
211 files
4.06K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Update

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ከሰሞኑን ከኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስቲያን ጋር በተያያዘ በተለያዩ ቦታዎች እየተፈጠሩ ያሉ ክስተቶች እና የሰብአዊ መብቶች ሁኔታዎችን በቅርበት በመከታተል እንዲሁም ሁሉንም ወገኖች እና የሚመለከታቸውን አካላት በማነጋገር ለችግሩ እልባት ለማግኘት ጥረት በማድረግ ላይ እንደሚገኝ ዛሬ በላከልን መግለጫ አሳውቋል።

ኮሚሽኑ በመግለጫው ባደረገው ክትትልና ምርመራ አዲስ "ቤተ ክህነት" አቋቁመናል በማለት ያሳወቁት ቅዱስ ሲኖዶስ ማዕረጋቸውን ያነሳባቸው ጳጳሳት በአንዳንድ ቦታዎች በኃላፊዎች ድጋፍ ጭምር በተለያዩ የኦሮሚያ ክልል ከተሞች የሚገኙ ሀገረ ስብከቶችን መያዛቸውን ገልጿል።

ጥር 27/2015 የሻሸመኔ ደብረ ስብሐት ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያንን ለመያዝ ያደረጉትን እንቅስቃሴ ተከትሎ እርምጃውን ለመቃወም የወጡ ሰዎችን ለመበተን በመንግሥት ጸጥታ አባላት በተወሰደ #ተመጣጣኝ_ያልሆነይል እርምጃና ከጸጥታ አባሎቹ ጋር ሲተባበሩ በነበሩ ሰዎች ቢያንስ 8 ሰዎች በጥይትና በድብደባ መገደላቻውን ኮሚሽኑ ማረጋገጡ አሳውቋል።

ኮሚሽኑ የኢ/ኦ/ተ/ቤ ኃላፊዎች በሻሸመኔ የሞቱት ሰዎች ቁጥር 13 መሆኑን እንደገለፁለት አስረድቶ ይህን የማጣራት ሂደቱ እንደቀጠለ ነው ብሏል።  

ቁጥራቸው ገና በትክክል ያልታወቀ ሰዎች ለተለያየ ዓይነትና መጠን የአካል ጉዳት መዳረጋቸውን እንዲሁም በርካታ ሰዎች ለተለያየ ጊዜ መጠን መታሰራቸውን አመልክቷል።

ኮሚሽኑ በተለያዩ ቦታዎች አዲስ " ቤተ ክህነት " አቋቁመናል በማለት ያሳወቁትን ጳጳሳት በተቃወሙ ሰዎችና የሃይማኖት መሪዎች ላይ ድብደባ፣ ማዋከብ፣ ከቤተ ክርስቲያናት ማባረር፣ የመንቀሳቀስ መብትን በኃይል መገደብ እና ከሕግ ውጭ እስራት እንደተፈጸመ ገልጿል።

(ከኢሰመኮ የተላከው ሙሉ መግለጫ ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia