TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.44K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#የጥንቃቄ_መልዕክት !

አሮጌው 100 ብር ኖት ከአዲሱ 10 ብር ኖት ጋር በቀለም ተመሳሳይነት እያጭበረበሩ ያሉ አካላት ስለመኖራቸው ብሄራዊ ባንክ መረጃ እንዳለው ገልፆ ፣ ህብረተሰቡ ጥንቃቄ እንዲያደርግ አሳስቧል።

ህብረተሰቡ በኖቶቹ ለውጥ ላይ በተለያዩ ቋንቋዎች ግንዛቤ እንዲኖረው እየተደረገ መሆኑ ተገልጿል።

በሌላ በኩል አዲሱን 100 ብር ኖት በአሮጌው 130 ብር ኖትና ከዚያ በላይ የሚሸጡ አንዳንድ ሰዎች መኖራቸውን በመረጃ እንደተደረሰበት ብሄራዊ ባንክ ገልጿል ፤ ህብረተሰቡ ተመሳሳይ ነገር ሲመለከት ለፖሊስ ጥቆማ እንዲሰጥ ጥሪ ቀርቧል።

#ሼር #SHARE

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#የጥንቃቄ_መልዕክት

ሐረማያ ዩኒቨርሲቲና አካባቢው ከፍተኛ ቁጥር ያለው የበረሀ አንበጣ በአሁኑ ሰዓት በዛፎች ላይ በማረፉ ነገ ቅዳሜ ጥቅምት 7 ከጠዋቱ 12፡00 - 2፡00 ባለው ሰዓት በአውሮፕላን የፀረተባይ መድኃኒት ይረጫል።

በመሆኑም ዩኒቨርሲቲው ዙሪያ በ3 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የምትገኙ ነዋሪዎች በተጠቀሰው ሰዓት ከቤታችሁ እንዳትወጡ እና ጥንቃቄ እንድታደርጉ የጥንቃቄ መልዕክት ተላልፏል።

#SHARE #ሼር

(ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#የጥንቃቄ_መልዕክት

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ደንበኞቹ ከሀሰተኛ የብር ኖቶች እንዲጠነቀቁ መልዕክት አስተላልፏል።

አዲሶቹን የብር ኖቶች አስመስሎ በማተም ሀሰተኛ ገንዘብ የማሰራጨት ህገ-ወጥ ተግባር በአንዳንድ አካባቢዎች እየታየ መሆኑን ባንኩ ገልጿል።

አዲስ የታተሙት የብር ኖቶች በአካላቸው ላይ የሚገኙ የደህንነት መጠበቂያ ምልክቶች ያሉባቸው እንደሆነም ተገልጿል፡፡

የደህንነት መጠበቂያ ያላሟሉ ወይም ተመሳስለው የተዘጋጁ ገንዘቦቸን የያዙ ወይም የሚጠቀሙ ግለሰቦች ካጋጠሟችሁ ወዲያውኑ በአቅራቢያ ለሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ/የጸጥታ አካል አሳውቁ ተብሏል።

ህብረተሰቡ ሀሰተኛውን የብር ኖት ከእውነተኛው ለመለየት ያስችለው ዘንድ የአዲሶቹን የብር ኖቶች የደህንነት መጠበቂያ ምልክቶች ልብ ማለት ያስፈልጋል፡፡

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#የጥንቃቄ_መልዕክት

በክረምት ወቅት የአየር ጸባዩ የሚፈጥረውን ከባድ ዝናብ ፣አደገኛ ጎርፍ ፣ጉም እና ጭጋግ ሳቢያ የትራፊክ አደጋ እንዳይከሰት አሽከርካሪዎች ተገቢውን ጥንቃቄ በማድረግ አሽከርክሩ።

- የተሽከርካሪ ክፍሎችን ማለትም ሊሾ ጉማ ገጥሞ ማሽከርከር ፣
- የማይሰራ የዝናብ መጥረጊያ መግጠም ፣
- የማይሰራ መብራቶችን አለማስተካከል ፣
- በጭጋግ ወቅት ስቲከር ለጥፎ ማሽከርከር ፣
- ፍሬን እና ሌሎች የቴክኒክ ክፍሎችን ሳያስተካክሉ ማሽከርከር ለከፋ የትራፊክ አደጋ የሚዳርጉ በመሆኑ ጥንቃቄ ይደረግ።

Credit : DebrMarkos Police

@tikvahethiopia
#የጥንቃቄ_መልዕክት

የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለሥልጣ የምግብ ደኅንነት ኢንስፔክተር መሀመድ ሁሴን ፦

" ሕብረተሰቡ የታሸጉ ምግቦችና መጠጦችን የመጠቀሚያ ጊዜያቸውን እያስተዋለ መግዛት አለበት።

በተለይ መጪዎቹን የበዓል ወቅቶችን አስታኮ በርካታ ጊዜያቸው ያለፋባቸው ምግቦችና መጠጦች በቅናሽ ዋጋ ወደ ገበያ ሊወጡ ስለሚችሉ ጥንቃቄ ሊያደርግ ይገባል።

ከምግብ ጋር  የተለያዩ ባዕድ ነገሮች ጋር በመቀላቀል አላስፈላጊ ትርፍ ለማጋበስ ከሚጥሩ ሕገ-ወጦችም ራስን መጠበቅ ይገባል።

ሕብረተሰቡ የሚገዛቸውን የምግብና የመጠጥ ምርቶች በጤና ላይ ጉዳት ሊያስከትሉ ስለሚችሉ ምርቶቹን ከመግዛቱ በፊት ማን እንዳመረታቸው ? መቼ እንደተመረቱና ? የመጠቀሚያ ጊዜያቸው መቼ እንደሚያልቅ? በአግባቡ ማየት አለበት።

ከእነዚህ ምግቦችና መጠጦች መካከል #ጁሶች ፣  የተለያዩ የታሸጉ #ብስኩቶችና ሌሎች #መጠጦች ላይ ትኩረት ሊያደርግ ይገባል።

በተለይ ሕገ-ወጥ የሆኑና ከባለሥልጣን መ/ቤቱ ወይም በክልል ጤና ቢሮዎች ሥር ባሉ ተቆጣጣሪ የፈቃድ ማረጋገጫ ሳይወስዱ የምግብ ንግድ ላይ ተሰማርተው የሚገኙ ሕገ-ወጦች አሉ።

ባለሥልጣን መ/ቤቱ የራሱን መቆጣጠሪያ ስልቶችን ነድፎ ቁጥጥር ያደርጋል ፤ ሕብረተሰቡ ለዚህ ሥራ የሚሰጠው መረጃ ቀላል ባለመሆኑ የተለመደ ትብብሩን ሊያደርግ ይገባል። "

#ENA

@TIKVAHETHIOPIA