TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.7K photos
1.44K videos
207 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ሰበር_ዜና በደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መ በሚገኙ #ሁሉም ዞኖች፣ ከተማ አስተዳደሮች እና ልዩ ወረዳዎች የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ #ታውጇል#ETHIOPIA

#State_of_emergency

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የደቡብ ክልል ከዛሬ ጀምሮ በኮማንድ ፖስት እንዲመራ ተወስኗል። #state_of_emergency #ETHIOPIA

@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#State_of_Emergency

ለ6 ወራት የታወጀው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የተፈፃሚነት ጊዜ እንዲያጥር የሚኒስትሮች ምክር ቤት ዛሬ ውሳኔ አሳልፋል።

ም/ቤቱ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ማውጣት የግድ አስፈላጊ እንዲሆን አድርጎ የነበረው ሁኔታ የተቀየረ መሆኑን ገልጿል።

አክሎም ስጋቱን በመደበኛ የሕግ ማስከበር ስራ መከላከልና መቆጣጠር የሚቻልበት ደረጃ ላይ መደረሱን በመግለፅ ለ6 ወራት የታወጀውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የተፈፃሚነት ጊዜ ማሳጠር አስፈላጊ ሆኖ መገኘቱን አሳውቋል።

በዚህም አስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የ6 ወር ጊዜው ሳይጠናቀቅ ጊዜውን የማሳጠር ስልጣን ያለው ህ/ተ/ም/ቤት የአዋጁን ተፈጻሚነት ቀሪ እንዲያደርገው የሚጠይቅ የውሳኔ ሃሳብ ለምክር ቤቱ እንዲተላለፍ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ውሳኔ አሳልፏል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#State_of_Emergency

ከሳምንታት በፊት የሚኒስትሮች ምክር ቤት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ጊዜው ከመጠናቀቁ በፊት ቀሪ እንዲሆን ያቀረበውን የውሳኔ ሀሳብ የኢፌዴሪ ህዝብ ተወካዮች ም/ ቤት ምርምሮ ያፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል።

ም/ ቤቱ ውሳኔውን መርምሮ የሚያፀድቀው ነገ በሚያካሂደው አስቸኳይ ስብሰባ ነው።

በውሳኔ ሃሳቡ ላይ ድምጽ ከመስጠቱ በፊት የም/ቤቱ የሕግ፣ ፍትህ እና ዲሞክራሲ ቋሚ ኮሚቴ በጉዳዩ ዙሪያ ማብራሪያ እንደሚሰጥ ኢትዮጵያ ኢንሳይደር በድረገፁ ላይ አስነብቧል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#NewsAlert በአማራ ክልል የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንዲታወጅ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ውሳኔ አሳለፈ። የሚኒስትሮች ም/ቤት በዛሬው ዕለት 23ኛ መደበኛ ስብሰባ አካሂዶ ነበር። በዚህም ስብሰባ ፤ " የሕዝብን ሠላም እና ደህንነት ለማስጠበቅ " በቀረበው የሚኒስትሮች ምክር ቤት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ቁጥር 6 /2015 ላይ መመምከሩ ተነግሯል። ምክር ቤቱ ፤ " በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የሚታየውን…
#State_of_Emergency

ዛሬ የሚኒስትሮች ምክር ቤት በ " አማራ ክልል " የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንዲደነገግ ውሳኔ ማሳለፉ ይታወቃል።

አመሻሹን ደግሞ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ እንዴት ተግባራዊ እንደሚደረግ እንዲሁም የሚወሰዱ እርምጃዎች እና ተከለከሉ ተግባራት ዝርዝር ይፋ ተደርጓል።

በዚህም ፤ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን የሚያስፈፅም በብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ዳይሬከተር ጄነራል የሚመራ የአስቸኳይ ጊዜ ጠቅላይ መምሪያ ዕዝ መቋቋሙ ተገልጿል።

የአስቸኳይ ጊዜ ጠቅላይ መምሪያ ዕዙ አባላት፣ መዋቅር እና አደረጃጀት በጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚወሰን ይሆናል ተብሏል።

የአስቸኳይ ጊዜ መምሪያ ጠቅላይ ዕዙ ተጠሪነት ለኢፌድሪ ጠቅላይ ሚኒስትር እንደሚሆንም ተገልጿል።

በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የሚወሰዱ እርምጃዎችና የተከለከሉ ተግባራት ምንድናቸው ?

- ማንኛውም ሰው በአዋጁ መሰረት የሚወጡ መመሪያዎችን፣ የሚሰጡ ትዕዛዞች እና የሚተላለፉ ውሳኔዎችን የመተግበር እና የማከበር ግዴታ አለበት ተብሏል።

- የአስቸኳይ ጊዜ ጠ/መምሪያ ዕዙን እንቅስቃሴና የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን አላማ #የሚቃረን#የሚቃወም እና በክልሉ የአመጽ እንቅስቃሴን የሚያበረታታ ፣ ሰላማዊ ዜጎችን የሚያሸብር፣ እንዲሁም የፀጥታ መደፍረሱን የሚያባብስ ንግግር፣ የቀጥታም ሆነ የተዘዋዋሪ ቅስቀሳ በማንኛውም መንገድ ማድረግ ወይም ማሰራጭት የተከለከለ መሆኑ ተመላክቷል።

- በየትኛውም መንገድ፣ በቀጥታ ሆነ በተዘዋዋሪ ለታጣቂ ቡድኖች የገንዝብ፣ የመረጃ፣ የቁስም ሆነ የሞራል ድጋፍ ማድረግ የተከለከለ መሆኑ ተገልጿል።

- ከአስቸኳይ ጊዜ ጠቅላይ መምሪያ ዕዙ ፈቃድ ውጪ ማንኛውንም የአደባባይ ስብሰባ ወይም ሰላማዊ ሰልፍ ማድረግ እንዲሁ ተከልክሏል።

- ከአስቸኳይ ጊዜ ጠ/መምሪያ ዕዙ ፈቃድ ውጭ ማናቸውንም የጦር መሳርያ ይዞ መንቀሳቀስ እንደማይቻል ተመላክቷል።

(ተጨማሪ ዝርዝር ጉዳዮችን ከላይ ያንብቡ)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#State_of_Emergency ዛሬ የሚኒስትሮች ምክር ቤት በ " አማራ ክልል " የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንዲደነገግ ውሳኔ ማሳለፉ ይታወቃል። አመሻሹን ደግሞ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ እንዴት ተግባራዊ እንደሚደረግ እንዲሁም የሚወሰዱ እርምጃዎች እና ተከለከሉ ተግባራት ዝርዝር ይፋ ተደርጓል። በዚህም ፤ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን የሚያስፈፅም በብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ዳይሬከተር ጄነራል የሚመራ…
#State_of_Emergency

የአስቸኳይ ጊዜ ጠቅላይ መምሪያ ዕዝ ባወጣው መግለጫ ፤ በ " መጀመሪያ ምዕራፍ " ዕቅድ በትልልቆቹ የአማራ ክልል ከተሞች ፦
- ባሕር ዳር፣
- ደብረ ማርቆስ፣
- ደብረ ብርሃን፣
- ላሊበላ፣
- ጎንደር
- ሸዋ ሮቢት ላይ አስፈላጊውን እርምጃ በመውሰድ " የሕግ የበላይነት እንዲከበር አስደርጌያለሁ " ብሏል።

በእነዚህ ከተሞች " በዘረፋ እና በጥፋት የተሰማራ ቡድንን በመምታት በከተሞቹ ላይ የሕግ የበላይነትን ማስከበር ተችሏል " ሲል ገልጿል።

በአሁኑ ሰዓት ከተሞቹ ከስጋት ነጻ መሆናቸውን የገለፀው ዕዙ  ፤ የመከላከያ ሠራዊቱ እና የክልሉ ህግ አስከባሪ አካላት የማጥራት ስራ እየሰሩ ነው ብሏል።

የመጨረሻውን የማጽዳት እና የመልቀም ተግባር በማከናወን ከተሞቹ በአጭር ጊዜ ወደ ተሟላ ሰላማዊ እንቅስቃሴ እንዲመለሱ ይደረጋል ሲልም አሳውቋል።

የአስቸኳይ ጊዜ ጠቅላይ መምሪያ ዕዙ ፦

- ከነገ ሐሙስ ነሐሴ 4 ጀምሮ ከላይ በተጠቀሱት ከተሞች መደበኛ የአውሮፕላን በረራ እንደሚጀምር፤

- ከባጃጅና ከሞተር ሳይክል በስተቀር ሁሉም ዓይነት የከተማ የትራንስፖርት አገልግሎቶች ወደ  አገልግሎት እንደሚገቡ፤

- የመንግሥት ፣ የማኅበረሰብ አገልግሎት ፣ የንግድ፣ የጤና፣ የፋይናንስ፣ ወዘተ. ተቋማት አገልግሎት እንዲሰጡ እንደሚደረግ አሳውቋል።

በሌላ በኩል ፤ እስካሁን 14 ተጠርጣሪዎችን በአዲስ አበባ ከተማ በቁጥጥር ሥር ማዋሉንና ወደፊትም እንደሁኔታው በቁጥጥር ሥር የሚያውላቸውን ግለሰቦች አስመልክቶ አስፈላጊውን መረጃ ለህዝብ ይፋ እንደሚያደርግ ገልጿል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#State_of_Emergency የአስቸኳይ ጊዜ ጠቅላይ መምሪያ ዕዝ ባወጣው መግለጫ ፤ በ " መጀመሪያ ምዕራፍ " ዕቅድ በትልልቆቹ የአማራ ክልል ከተሞች ፦ - ባሕር ዳር፣ - ደብረ ማርቆስ፣ - ደብረ ብርሃን፣ - ላሊበላ፣ - ጎንደር - ሸዋ ሮቢት ላይ አስፈላጊውን እርምጃ በመውሰድ " የሕግ የበላይነት እንዲከበር አስደርጌያለሁ " ብሏል። በእነዚህ ከተሞች " በዘረፋ እና በጥፋት የተሰማራ ቡድንን…
#State_of_Emergency

ሰዓት እላፊ ገደብ ተጣለ።

በባሕር ዳር ፣ ጎንደር እና ደብረ ብርሃን ጨምሮ በሌሎች ከተሞች የሰዓት እላፊ ገደብ ተጣለ።

የአስቸኳይ ጊዜ ጠቅላይ መምሪያ ዕዝ ትዕዛዝና ክልከላ አውጥቷል።

በዚህም ፤ ባሕር ዳር ፣ ጎንደር ፣ ደብረ ብርሃን ፣ ደብረ ማርቆስ፣ ሸዋ ሮቢትና ላሊበላ እስከ ነሐሴ 17/2015 የሚቆይ የሠዓት እላፊ ገደብ ጥሏል።

- የድንገተኛ ህክምና አገልግሎት ከሚሰጡ ተሽከርካሪዎች፣
- የድንገተኛ ህክምና አገልግሎት ሰጪ ባለሞያዎች
- የፀጥታ አስከባሪ ተቋማት ባልደረቦች ውጪ ለማንኛውም ሰው እና ተሽከርካሪ ከምሽቱ #አንድ_ሰዐት_በኋላ መንቀሳቀስ በጥብቅ ተከልክሏል።

የባጃጅ እና የሞተር ሳይክል እንቅስቃሴ ከነሐሴ 4 እስከ ነሐሴ 17 2015 ድረስ ፈጽሞ መከልከሉ ተገልጿል።

ከባጃጆችና ከሞተር ሳይክሎች በስተቀር ሌሎች የከተማ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪዎች ከነሐሴ 4 ጀምሮ ወደ ሥራ የመመለስ እና አገልግሎት የመስጠት ግዴታ ተጥሎባቸዋል።

ከዚህ ባለፈ ፤ በባሕርዳር፣ ጎንደር፣ ደብረ ብርሃን፣ ደብረ ማርቆስ፣ ሸዋ ሮቢትና ላሊበላ የሕዝብ የአገልግሎት ሰጪ፣ የመንግሥት፣ የማኅበረሰብና የንግድ ተቋማት ከነሐሴ 4/2015 ጀምሮ ክፍት እንዲሆኑ ታዟል።

የአስቸኳይ ጊዜ ጠቅላይ መምሪያ ዕዙ ከፈቃዴ ውጪ በአማራ ብሔራዊ ክልል ከተሞች የአደባባይ ስብሰባ፣ ሰልፍና መሰል እንቅስቃሴዎችን ማድረግ ፈጽሞ የተከለከለ ነው ብሏል።

በማንኛውም መልኩ የህዝብ እንቅስቃሴን የሚያስተጓጉል እና የትራንስፖርት አገልግሎትን የሚያሰናክል ድርጊትም በጥብቅ የተከለከለ ነው ሲል አስጠንቅቋል።

በተጨማሪ ፤ በክልሉ ለጸጥታ ሥራ ከሚንቀሳቀሱ የህግ አስከባሪ አካላት እና ከነዚህ አካላት ፈቃድ ውጭ የጦር መሣሪያ ይዞ መዘዋወር ፈጽሞ ተከልክሏል።

በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ሽፋን ከአስቸኳይ ጊዜ ጠቅላይ መምሪያ ዕዝ ትእዛዝ ውጭ ወቅታዊ ሁኔታን ሰበብ በማድረግ ግለሰቦችን ከመደበኛው ህግ አግባብ ውጪ ማሰር እና ማቆየት፣ የንግድ ቤቶችን ማሸግ እና መሰል እርምጃዎችን መውሰድ በጥብቅ የተከለከለ መሆኑን አሳውቋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#State_of_Emergency ዛሬ የሚኒስትሮች ምክር ቤት በ " አማራ ክልል " የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንዲደነገግ ውሳኔ ማሳለፉ ይታወቃል። አመሻሹን ደግሞ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ እንዴት ተግባራዊ እንደሚደረግ እንዲሁም የሚወሰዱ እርምጃዎች እና ተከለከሉ ተግባራት ዝርዝር ይፋ ተደርጓል። በዚህም ፤ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን የሚያስፈፅም በብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ዳይሬከተር ጄነራል የሚመራ…
#State_of_Emergency

ነገ በአማራ ክልል እንደ አስፈላጊነቱ በየትኛውም የሀገሪቱ አካባቢ ላይ ተግባራዊ እንዲደረግ በሚኒስትሮች ም/ቤት የታወጀው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርቦ የሕዝብ ተወካዮች በሚሰጡት ድምፅ የመጨረሻ ውሳኔ ያገኛል።

ምክር ቤቱ፤ ከቀናት በፊት በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ላይ መርምሮ ውሳኔ ለማሳለፍ ለነገ ሰኞ 8 ሰዓት ለምክር ቤት አባላት አስቸኳይ የስብሰባ ጥሪ ያቀረበ ሲሆን በዚሁ መሰረት አባላት ተሰብስበው ውሳኔ ያሳልፋሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ሕጉ ምን ይላል ?

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሥራ ላይ ባለ ጊዜ የታወጀ ከሆነ በ48 ሰዓታት ውስጥ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንደሚቀርብ፣ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሁለት ሦስተኛ ድምፅ ተቀባይነት ካላገኘ ወዲያውኑ እንደሚሻር የሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 93 ንዑስ አንቀጽ ሁለት (ሀ) ይደነግጋል።

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሥራ ላይ ባልሆነበት ወቅት የታወጀ እንደሆነ በአሥራ አምስት ቀናት ውስጥ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መቅረብ እንዳለበት፣ የምክር ቤቱን ሁለት ሦስተኛ ድምፅ ተቀባይነት ካላገኘም ወዲያውኑ እንደሚሻር የሕገ መንግሥቱ ቀጣይ አንቀጽ ይደነግጋል።

6ኛው ዙር ምርጫ በተለያዩ አካባቢዎች ተከስቶ በነበረ ግጭትና አለመረጋጋት ሳቢያ በተሟላ ሁኔታ ባለመከናወኑ፣ በሥራ ላይ የሚገኘው የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት ካሉት 547 ወንበሮች መካከል የተወሰኑት የተጓደሉ ናቸው።

በአጠቃላይ አሁን በሥራ ላይ በሚገኘው ምክር ቤት መቀመጫ የያዙ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ብዛት 427 መሆኑን ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ መረጃ መረዳት ይቻላል።

በመሆኑም በሚኒስትሮች ምክር ቤት የታወጀውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ም/ ቤቱ በሁለት ሦስተኛ ድምፅ ማፅደቅ ይኖርበታል በሚለው ሕገ መንግሥታዊ ድንጋጌ መሠረት፣ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ሊፀና የሚችለው ከአጠቃላይ የምክር ቤቱ አባላት ማለትም በስድስተኛው ዙር ተመርጠው በምክር ቤቱ መቀመጫ ከያዙት 427 ተወካዮች መካከል 285 የሚሆኑት የድጋፍ ድምፅ ከሰጡ ነው።

ከተጠቀሱት 427 ተመራጮች ውስጥ 142 የምክር ቤት አባላት የተቃውሞ ድምፅ ከሰጡ ግን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ቀሪ ሊሆን ይችላል። 

በም/ቤቱ ወንበር ካገኙ አጠቃላይ 427 አባላት ወስጥ 410 የሚሆኑት በገዢው ፓርቲ ብልፅግና አቅራቢነት ተወዳድረው የተመረጡ የሕዝብ ተወካዮች ሲሆኑ፣ ከእነዚህ ውስጥ ደግሞ 125 ያህሉ በአማራ ብልፅግና ፓርቲ አቅራቢነት የተወዳደሩና የክልሉን ሕዝብ የሚወክሉ ናቸው።

ከብልፅግና ፓርቲ ውጪ በአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) አቅራቢነት ተወዳድረው የተመረጡ አምስት የሕዝብ ተወካዮች ሲኖሩ፣ በኢዜማ አቅራቢነት ተወዳድረው የተመረጡ ሌሎች አራት የሕዝብ ተወካዮች እንደሚገኙም ይታወቃል።

ይሁን እንጂ ከዚህ ቀደም ለምክር ቤቱ በቀረቡ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጆች ላይ ለተሰጠው ድምፅ ሥሌት የተደረገው በዕለቱ የነበረውን የምክር ቤቱ ምልዓተ ጉባዔ መሠረት አድርጎ በመሆኑ፣ የታወጀው አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለምክር ቤት በሚቀርብበት ወቅት የሚኖረው የድምፅ አሰጣጥ ሥሌት በዕለቱ የሚኖረውን ምልዓተ ጉባዔ ታሳቢ የሚያደርግ ይሆናል።

በመሆኑም የሁለት ሦስተኛ ድምፅ ሥሌቱ ከላይ የምክር ቤቱን ጠቅላላ አባላት መሠረት በማድረግ ከተገለጸው ውጤት ያነሰ የድጋፍ እና ተቃውሞ ድምፅ የመከሰት ዕድሉ ሰፊ ነው።

(የሕግ ጉዳይ ማብራሪያ ከሪፖርተር ጋዜጣ)

@tikvahethiopia