TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.7K photos
1.44K videos
207 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
በደቡብ ሱዳን የመጀመሪያው ሞት ተመዘገበ! በደቡብ ሱዳን ከኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ጋር በተገናኘ የመጀመሪያው #ሞት መመዝገቡ ተሰምቷል። ከዚህ በተጨማሪ በሀገሪቱ በአንድ ቀን 28 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች 231 ደርሰዋል። @tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#SouthSudan

የደቡብ ሱዳን ጤና ሚኒስቴር ዛሬ በሀገሪቱ የመጀመሪያው የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ሞት በይፋ መመዝገቡን ሪፖርት ከማድረግ ውጭ ስለሟቹ ዝርዝር መረጃ አልሰጠም።

#SSNN ግን ሟቹ የቀድሞ ከፍተኛ ወታደራዊ አዛዥ የሆኑት ብርጋዴር ጄነራል ጆን ማዴንግ ጋታዴል ናቸው ሲል ዘግቧል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#SouthSudan

የደቡብ ሱዳን የኢንፎርሜሽን ሚኒስትር ሚካኤል ማኩዪና የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትር ማርቲን ኤሊያ ሎሞሮ በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ከተረጋገጠ ከፍተኛ ባለስልጣናት መካከል እንደሚገኙበት #SSNN ይፋ አድርጓል።

2ቱም ሚኒስትሮች ባለፈው ወር ናሙና ለመስጠት ፍቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተው ነበር የተባለ ሲሆን በዚህ ወር ግን ምርመራ ሲደረግላቸው ሁለቱም በቫይረሱ መያዛቸው መረጋገጡን #SSNN ስማቸው ካልተገለፀ 'የኮቪድ-19 ታስክ ፎርስ' አባል መረጃ ማግኘቱን ገልጿል።

ሌላ አንድ ስማቸው ያልተገለፀ ምንጭ ደግሞ ሁለቱም (2) ሚኒስትሮች ጤናቸው ጥሩ የሚባል ደረጃ ላይ እንደሚገኝ እና ምልክት እንደማይታይባቸው አሳውቀዋል ሲል #SSNN ዘግቧል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#SouthSudan

የደቡብ ሱዳን የኢንፎርሜሽን ሚኒስትር ሚካኤል ማኩዪ ከጤና ሚኒስትሯ ውጭ #ሁሉም የኮሮና ቫይረስ መከላከያ ግብረ ኃይል አባላት በኮሮና ቫይረስ መያዛቸውን ለቢቢሲ #አረጋግጠዋል

በኮቪድ-19 የተያዙት ሁሉም ሚኒስትሮች በለይቶ ማቆያ የሚገኙ ሲሆን በሙሉ ጤንነትም ላይ ይገኛሉ ተብሏል።

ከዚህም በተጨማሪ የባለስልጣናቱ ጠባቂዎች እንዲሁም ሠራተኞች በኮሮና ቫይረስ ተይዘው በለይቶ ማቆያ ውስጥም ይገኛሉ።

በሌላ በኩል የኢንፎርሜሽን ሚኒስትሩ ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር በኮቪድ-19 ተይዘዋል የሚለውን ሪፖርት #አጣጥለውታል

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የደ/ሱዳን ፕሬዚዳንት አዲስ አበባ ገቡ። የደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር ማያርዲት ለይፋዊ የስራ ጉብኝት አዲስ አበባ ገብተዋል። ፕሬዝዳንቱ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ፣ የሰላም ሚኒስትር ሙፈሪያት ካሚልና የመከለከያ ሚኒስትር ዶክተር ቀነዓ ያደታን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል ተብሏል። በኢትዮጵያ ቆይታቸው…
#Ethiopia #SouthSudan

ወደኢትዮጵያ ለስራ ጉብኝት የመጡት የጎረቤት ሀገር ደ/ሱዳን ፕሬዜዳንት ፥ "ኢትዮጵያ ነጻነቷን እና ሉአላዊነቷን ለማስጠበቅ በምታደርገው የህልውና ዘመቻ እየደረሰባት ያለውን የውጭ ጣልቃ ገብነት አንቀበለም" ማለታቸው ተሰምቷል።

የጠ/ሚ ፅ/ቤት የፕሬስ ሴክሬታሪያት ቢልለኔ ስዩም፥ ሳልቫ ኪር ከጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አህመድ ጋር በትላንትና እለት ከተወያዩ በኋላ ህወሃት እያደረሰ ያለውን ጥቃት ኮንነዋል ብለዋል።

“የጉብኝቱ ትኩረት ቁልፍ በሆኑ የሁለትዮሽ እና የክልል ጉዳዮች ላይ በጋራ መነጋገር ነበር” ሲሉም አክለዋል፡፡

ኪር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቢትሪስ ዋኒ-ኖህን ጨምሮ ወደ ኢትዮጵያ የመጣው የልዑካን ቡድን ጉብኝት ላይ “በተለይ ትኩረት የሰጠው ኢኮኖሚያዊ ግንኙነቶችን እና የጋራ የመሠረተ ልማት ግንባታን ማጠናከር ነበር” ማለታቸውን ሱዳን ፖስት ዘግቧል፡፡

ፕሬዜዳንት ሳልቫኪየር ፥ ህወሃትን በተመለከተ "ከኢትዮጵያ ጎን እንቆማለን" ስለማለታቸው የተገለፀ ሲሆን በሰኔ ወር የተከናወነው ሀገራዊ ምርጫ በስኬት መጠናቁንና በአባይ ወንዝ ላይ እየተገነባ ያለው ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በተመለከተ ለዶ/ር ዐቢይ አህመድ እንኳን ደስ አለዎት ሰሉ መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።

መረጃው የኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 ሬድዮ ጣቢያ ነው።

@tikvahethiopoa
#Somalia #Ethiopia #Sudan #SouthSudan

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን እና የኢጋድ ዋና ፀሀፊ ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ በኢትዮጵያ፣ ሱዳን፣ ደቡብ ሱዳን እና ሶማሊያ ባሉ አሁናዊ ሁኔታዎች ዙሪያ ላይ ተወያይተዋል።

ውይይቱን በተመለከተ አንቶኒ ብሊንከን በይፋዊ ትዊተር ገፃቸው ላይ ፥ ውጤታማ ውይይት መደረጉን ገልፀዋል ።

ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ በበኩላቸው ቀጠናዊ ሰላም እና ደህንነት፣ የአየር ንብረት ለውጥ፣ በኢኮኖሚ እንዲሁም በሌሎችም ቀጠናዊ እና ዓለምአቀፋዊ ጉዳዮች ላይ ከአንቶኒ ብሊንከን ጋር መወያየታቸውን በይፋዊ የፌስቡክ ገፃቸው ላይ ገልፀዋል።

ዶ/ር ወርቅነህ ፥ " በቀጣይም ከአሜሪካ ጋር በበርካታ ዘርፎች አብረን እንሰራለን " ያሉ ሲሆን " አሜሪካ የኢጋድ ወሳኝ አጋር ናት "ብለዋል።

Photo : Secretary Antony Blinken

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የደ/ሱዳን ፕሬዚዳንት 2 ከፍተኛ የሀገሪቱን ባለስልጣናት ከስልጣን አስነሱ። የደቡብ ሱዳን ፕሬዝዳንት ሳልቫ ኪር የሀገሪቱን የገንዘብ ሚኒስትር እና የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር ከስልጣን አስነስተዋቸዋል። ባለስልጣናቱ ለምን ከኃላፊነታቸው እንደተነሱ ፕሬዜዳንቱ የሰጡት ምክንያት የለም። ፕሬዝዳንት ኪር ፥ አትያን ዲንግ አቲያንን ከፋይናንስ ሚኒስትርነት በማንሳት በአጋክ አቹል ሉአል የተኩ ሲሆን ፣ የሀገር…
#SouthSudan

ኢትዮጵያን ለማዳከም የሚደረግ ጥረት ሁሉ በአጠቃላይ በአፍሪካ ላይ እንደተቃጣ ስጋት የሚቆጠር መሆኑን ደቡብ ሱዳን አስታወቀች።

በደቡብ ሱዳን የኢፌዴሪ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ነቢል ማህዲ አዲስ ከተሾሙት የደቡብ ሱዳን የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስተር ማሃሙድ ሰለሞን አጎክ ጋር ተወያይተወል።

በዚህ ወቅት አምባሳደር ነቢል ህውሃት እየፈጸመ ያለውን እኩይ ተግባር ለመመከት መንግሥት እደረገ ያለውን ጥረት ለሚኒስትሩ ገልጸውላቸዋል።

በተጨማሪም የምዕራባዊያን የሚዲያ ተቋማት የሃሰት መረጃን በማሰጨት የመንግሥትን ቅቡልነት አጠያያቂ ለማድረግ እየሰሩ መሆኑን ተናግረዋል።

እነዚህ ሚዲያዎች በኢትዮጵያ ያሉ የተለያዩ አገራትና ዓለም አቀፍ ድርጅቶች እንግልት እየደረሰባቸው መሆኑን በመጥቀስ ላይ መሆናቸውን በማስታወስ፣ ይህ ከእውነት የራቀ መሆኑንና ኢትዮጵያ የዲፕሎማቶችን መብትና ጥቅም የሚያስጠብቀውን የቬይና ስምምነት በጥብቅ እንደምታከብር ገልጸዋል።

ሚኒስትሩ በበኩላቸው ኢትዮጵያዊያን ለደ/ሱዳን ነጻነት የሕይወት መሰዋዕት መክፈላቸውን በማስታወስ፣ ይህንንም እራሳቸው በትግል ወቅት በተግባር ያረጋገጡት ሃቅ መሆኑን መስክረዋል።

አያየዘውም የአፍሪካ ህብረት መቀመጫ የሆነችው ኢትዮጵያን ለማዳከም የሚደረግ ጥረት ሁሉ በአጠቃላይ በአፍሪካ ላይ እንደተቃጣ ስጋት የሚቆጠር መሆኑን ገልጸዋል።

ከዚህ የተነሳ ኢትዮጵያ የግጭት መናሃሪያ ሆና ማየት አንደማይሹ መግለፃቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያሳያል።

NB : በማህሙድ ሰለሞን አጎክ ከቀናት በፊት የተሾሙ የደ/ሱዳን ባለስልጣን ሲሆኑ ፤ ፕሬዝዳንት ኪር ፤ የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር ፖል ማዮም አኬክን ከስልጣን አስነስተው በማህሙድ ሰለሞን አጎክ መተካታቸውን መረጃ መለዋወጣችን አይዘነጋም።

@tikvahethiopia
#SouthSudan

ደቡብ ሱዳን ከምስራቅ አፍሪካ በይነ መንግስታት የልማት ባለስልጣን /ኢጋድ/ አባልነት ታግዳለች።

ኢጋድ ከአባልነት ያገዳት በየዓመቱ ለተቋሙ መክፈል የሚጠበቅባትን መዋጮ ባለመክፈሏ ነው።

የደቡብ ሱዳን የማስታወቂያ፣ የመገናኛ እና የፖስታ አገልግሎት ሚኒስትር ሚካኤል ማኩዌ ሀገራቸው በተባለው ምክንያት ከኢጋድ መታገዷ አረጋግጠዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒሰትሩ ማይክ አዪ ድንግ በካቢኔ ስብሰባው ላይ ለኢጋድ መዋጮ ሚሆን ገንዘብ መጠየቃቸውን አስታውቀዋል።

ካቢኔው ከመከረ በኋላ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ከአዲሱ የገንዘብ ሚኒስትር ጋር እንዲወያዩበት መወሰኑን ገልፀዋል።

ይህም ሁሉንም ውዝፍ ለመክፈል የሚያስችል መንገድ የሚያመቻች ነው ብለዋል።

ምንጭ፦ አልዓይን / ሲጂቲኤን

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ETHIOPIA #KENYA ኢትዮጵያ ከጎረቤት ሀገር ኬንያ ጋር በሰላምና የደህንነት ጉዳዮች ለመተባበር ተስማምታለች። ዛሬ የኢፌዲሪ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድማርሻል ብርሃኑ ጁላ እና የኬንያ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጄኔራል ሮበርት ኪቢቹ ኬንያ፣ ናይሮቢ ውስጥ ተወያይተዋል። ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ከኬንያ አቻቸው ጄኔራል ሮበርት ኪቢቹ ጋር ባደረጉት ምክክር ሁለቱ አገሮች…
#Ethiopia #SouthSudan

በጄኔራል አበባው ታደሰ የተመራ ልዑክ ቡድን በደቡብ ሱዳን የሥራ ጉብኝት እያካሄደ ነው።

የኢትዮጵያ የጦር ኃይሎች ምክትል ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጀኔራል አበባው የሚመሩት ልዑክ በደቡብ ሱዳን ጁባ የስራ ጉብኝት እያደረገ ይገኛል።

በዚህ የስራ ጉብኝት ጀነራል አበባው ታደሰ ከደቡብ ሱዳን አቻቸው ሉ/ጄኔራል ቶይ ቻኒይ ሬይት ጋር ውይይት አድርገዋል።

በሎጂስቲክስ እና በአቅም ግንባታ ጉዳዮች ለደቡብ ሱዳን ድጋፍ ለማድረግና ተሞክሮ ለማጋራት እንዲሁም የሁለቱ አገራት #የድንበር_አካባቢ ፀጥታና ደህንነትን ለማረጋገጥ በትብብር ለመሥራት ከስምምነት መደረሱ ተገልጿል።

ትላንትና የኢትዮጵያ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ፤ በናይሮቢ ከኬንያ አቻቸው ከጄኔራል ሮበርት ኪቢቹ ጋር ውይይት ካደረጉ በኃላ ሁለቱ ሀገራት በሰላም እና የደህንነት ጉዳዮች ላይ ለመተባበር ስምምነት ማድረጋቸው አይዘነጋም።

@tikvahethiopia
#SouthSudan

የጎረቤታችን የደቡብ ሱዳን ተቀናቃኝ የፖለቲካ እና ወታደራዊ ኃይሎች በመካከላቸው የነበረውን የተካረረ መቃቃር ለመፍታት በዋና ከተማቸው ጁባ ስምምነት ተፈራርመዋል።

ስምምነት ላይ የደረሱት በሌላኛዋ ጎረቤታችን ሱዳን አሸማጋይነት ነው።

የፖለቲካ ኃይሎቹ የተካረረ መቃቃር ውስጥ ገብተው ነበር የተባለ ሲሆን ይህንን ችግር ለመፍታት ተስማምተዋል።

ስምምነቱ ከሁሉም የተውጣጣና ጠንካራ ብሔራዊ ጦርን ለመመስረት የሚያስችል ሲሆን ይህን ለማጽናት የሚያስችል ሰነድ ተዘጋጅቶም ተፈራርመዋል፡፡

ፊርማው የፓለቲካ ኃይሎቹን የማሸማገሉን ሚና በወሰዱት የሱዳን ሉዓላዊ የሽግግር ምክር ቤት ምክትል ፕሬዝዳንት ጄ/ል መሃመድ ሃምዳን ደገሎ በተገኙበት የተፈረመ ነው።

ለመገንባት በታሰበው ብሔራዊ ጦር ወጥነት ያለው እዝን ለመፍጠርና ስልጣን ለመከፋፈል እንደሚያስችል ተነግሮለታል።

ጄ/ል መሃመድ ሃምዳን ደገሎ (ሄሜቲ) ፥ " በፕሬዝዳንት ሳልቫ ኪር እና በምክትላቸው ሬይክ ማቻር (ዶ/ር) በሚመሩ ኃይሎች መካከል የተፈጠረውን መቃቃር በማርገብ ለማስማማት ያደረግነው ጥረት ተሳክቶልናል " ያሉ ሲሆን " ወንድሞቻችን የሃገራቸውን ሰላምና ደህንነት ለማስቀጠል በሚያስችል ትክክለኛ መንገድ ላይ በመገኘታቸው ደስተኞች ነን " ሲሉ መሪዎቹን አመስግነዋል፡፡

(አል ዓይን ኒውስ)

@tikvahethiopia