TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.7K photos
1.44K videos
207 files
3.98K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
🇪🇹 #NationalDialogue 🇪🇹

➡️ " በሃገራዊ ምክክሩ #ሁሉም አካላት ካልተሳተፉ ምክክሩ ውጤት ላያመጣ ይችላል " - የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት

➡️ " ያኮረፉ እና ጫካ የገቡ #ታጣቂዎች በምክከሩ እንዲሳተፉ ከሲቪል ማህበረስብ  እና ከተለያዩ ሀገራት #ኤምባሲዎች ጋር እየሰራን ነው " - ኮሚሽኑ

የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ም/ቤት እየተደረጉ ያሉ ግጭቶች ቆመው ሁሉም አካላት ወደ ንግግር አንዲመጡ ጠይቋል

የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ጫካ የሚገኙት ታጠቂዎች በምክክሩ ላይ እንዲሳተፉ ከለላ እንዲደረግላቸው መንግስትን የመጠየቅ ፍላጎት እንዳለው ገልጿል።

የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ም/ቤት ሰብሳቢ ደስታ ዲንቃ " በሃገራዊ ምክክሩ ሁሉም አካላት ካልተሳተፉ ምክክሩ ውጤት ላያመጣ ይችላል " ብለዋል፡፡

በጫካ ያሉ ታጣቂዎች በምክክሩ አንዲሳተፉ ለዚህ ሁኔታዎች እንዲመቻቹ  ምክር ቤቱ የጠየቀ ሲሆን ፥ " ይህ ካልሆነ ግን የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ስራ ውጤት ላያመጣ ይችላል " ሲል የጋራ ም/ቤቱ ስጋቱን ተናግሯል።

#ሌላው_ስጋት ብሎ ያነሳው ደግሞ የምክክር ኮሚሽኑ የተቋቋመበት አዋጅ  ግጭቶችን የማስቆም ሃላፊነት አልተሰጠውም ግጭት ሳይቆም በግጭት ውስጥ የሚደረግ ምክክር ደግሞ ውጤት ላያመጣ ይችላል ብሏል፡፡

የጋራ ም/ቤቱ ከጅምሩ ጀምሮ " በምክክሩ አንሳተፍም " ያሉ ፓርቲዎችን፣ በተለያየ ክልሎች ያሉ ታጣቂዎች በምክክሩ እንዲሳተፉ እንዲደርግ ኮሚሽኑን ጠይቋል፡፡

የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነር የሆኑት ዶክተር ዮናስ አዳዬ ምክክሩ አሳታፊ እንዲሆን፣ ያኮረፉ እና ጫካ የገቡ ታጣቂዎች በምክከሩ እንዲሳተፉ ከሲቪል ማህበረስብ  እና ከተለያዩ አለም ሀገራት ኤምባሲዎች ጋር እየሰራን ነው ሲሉ ተናግረዋል።

" ጫካ የገቡ አካላት በምክክሩ እንዲሳተፉ በመገናኛ ብዙሃን ተደጋጋሚ ጥሪዎችን እያደረግን ነው " ያሉት ዶ/ር ዮናስ " ሕጋዊ የሆነ መስሪያ ቤት ስለሌላቸው ጥሪ ለማድረግ ተቸግረናል፣ እዚህ ነን  አለን የሚሉ ከሆነ የተመካከሩ ጥሪ ወረቀት ይዘን ለመሄድ ዝግጁ ነን " ብለዋል፡፡

Credit - Sheger FM 102.1

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" በባንክ ስም የሚዘርፉ ግለሰቦች እና ቡድኖች አሉ " - ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) " የኢትዮጵያ የፋይናሻል ስርዓት ጤናማ በሆነ መንገድ እንዳያድግ የሚያበላሹ ግለሰቦች እና ቡድኖች አሉ " ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተናገሩ። እነዚህ አካላት " በባንክ ስም የሚዘርፉ ናቸው " ብለዋል። " ባንኮች ኮሚሽን ስለለመዱ፣ በትክክለኛው ህጋዊ መንገድ ከሚሰራው ይልቅ የትይዩ ማርኬት ውስጥ…
#ብላክማርኬት #ኤምባሲዎች

" ነገር እንዳናበላሽ ነው የታገስናቸው ስራቸው ብላክ ማርኬት ማሯሯጥ የሆኑ ኤምባሲዎች አሉ " - ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር)

ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) በስም ያልጠቀሷቸው ኤምባሲዎች የኢትዮጵያን ሃብት በመዝረፍ እና የውጭ ምንዛሬ ቢዝነስ ላይ የተሰማሩ እንዳሉ ጠቁመዋል።

" አንዳንድ ኤምባሲዎች ቀጥ ብለው የኢትዮጵያን ሃብት የመዝረፍ እና የውጭ ምንዛሬ ቢዝነስ የሚሰሩ ኤምባሲዎች አሉ ስራቸው ይሄ የሆነ " ብለዋል።

" እነሱ ላይ ጥብቅ ክትትል ይደረጋል የማይታረሙ ከሆነ እርምጃ ይወሰዳል። ጤናማ ዝምድና የማያደርግ ማንም ኤምባሲ እኛ አንፈልግም እኛ የምንፈልገው ጤናማ ህጋዊ ስርዓት ያለውን መንገድ የሚከተል ብቻ ነው " ሲሉ ገልጸዋል።

" ያን ስራ (ብላክ ማርኬት) የሚሰሩ ነገር እንዳናበላሽ ብለን የታገስናቸው ስራቸው ግን የብላክ ማርኬት የማሯሯጥ የሆኑ ኤምባሲዎች አሉ " ሲሉ ተናገረዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በብላክ ማርኬት ላይ የተሰማሩትን ኤምባሲዎች ስማቸውን በግልጽ ከመናገር ተቆጠበዋል።

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia